2013-10-26 09:03:48

በቅድስት መንበር ለተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ልኡከ መንግሥት


RealAudioMP3 ለተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በቅድስት መንበር አዲስ ልኡከ መንግሥት በመሆን ከአገሪቱ መንግሥት የተላኩት ልኡከ መንግሥት ከንት ሃከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ትራስይ መክክሉረ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “ሰብአዊነት ለማነቃቃት ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር መተባበር” የልኡከ መንግሥት መርሃ ግብራቸው መሆኑ ጠቅሰው እኚህ ከ 1972 ዓ.ም. እስከ 2012 ዓ.ም. የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የእርዳታ አገልግሎት ማኅበር ሊቀ መንበር እንዲሁም ከ 1996 እስከ 2004 ዓ.ም. የተለያዩ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበራት ለሚያቅፈው ካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ ምክትል ሊቀ መንበር በመሆን ያገለገሉት ልኡከ መንግሥት አክለው፣ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ልኡከ መንግሥት ሆነው ከመሾማቸው በፊት በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን በነበራቸው የተለያየ የአገልግሎት ኃላፊነት ከተለያዩ የቤተ ክርስቲያን አበይት አካላት ብፁዓን ካርዲናሎችና ጳጳሳት ምእመናን ጋር የተገናኙ ቢሆንም ቅሉ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር ር.ሊ.ጳ. ሆነው ከመሾማቸው በፊት አለ መገናኘታቸ ገልጠው፣ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ ማረጋገጥ በሚለው ዓላማ መሠረት ከቅዱስት መንበር ጋር በመተባበር ሰባአዊነት በማነቃቃቱ ረገድ በመተባበር ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸው ገልጠው፣ በነበረኝ የቆየው ኃላፊነት በቤተ ክርስቲያን የተለያዩ ብርቱ ምእመናን የቤተ ክርስቲያን አካላት ጋር መገናኘታቸው አስታውሰው በተላኩበተ አዲስ የመንግሥት ኃላፊነት አማካኝነት ከቅድስት መንበር ጋር በቅርብ ሆነው ለመሥራት እድል ማግኘታቸውና በተለይ ደግሞ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሙሉ ሰብአዊ እድገት ሰላም ፍትህ ወንድማማችነት ዓለማዊነት ቅርጽ ይኖረው ዘንድ በሚያደርጉት ኵላዊ ጥረት መተባበር እድል ነው በማለት የሰጡት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.