2013-10-26 08:35:12

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ክርስትያኖች እምነታቸውን በእውነትና ከምር እንዲኖሩት አደራ


RealAudioMP3 ምሥጢረ ጥምቀት የተቀበለ ሁሉ በቅድስና መንገድ እንዲጓዝ እንጂ የፈረቃ ወይንም የግማሽ መንገድ ተጓዥ መሆን አይችልም በሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ ስብከት በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት እ.ኤ.አ. ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ባሰሙት ስብከት፣ ከኢየሱስ በፊትና በኋላ የሆነው ሕይወታችን ክርስቶስ ያረጋገጠው ዳግም መፈጠራችን በዕለታዊ ሕይወትን የሚኖር ክርስቲያናዊ ግዴታችን መሆኑ እንዳብራሩ የቅዳሴው ሥነ ሥርዓት የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አስታወቁ።
ቅዱስ አባታችን በዕለቱ አንደኛው ምንባብ ቅዱስ ጳውሎስ ለሮማውያን በጻፈው መልእክት ዘንድ በተመለከተው፣ የድኅነታችን ምሥጢር ሕይወታችን ከኢየሱስ በፊት ከኢየሱስ በኋላ በሚል ቲዮሎጊያዊ አመክንዮ ሲያስረዳ ከኢየሱስ በፊት ሕይወታችን ቆሻሻና ውዳቂ ከኢየሱስ በኋላ ዳግም ፍጥረት (ዳግም የተፈጠረ ሕይወት) በማለት ከኢየሱስ በኋላ በሆነው አመክንዮ እንድንኖር ሲያሳብ፦ “በክርስቶስ ዳግም ተፈጥረናል፣ ስለዚህ ክርስቶስ በእኛ የፈጸመው አዲስ ወይንም ዳግም መፈጠርን ነው። ከኢየሱስ በፊት የነበረው መላ ሕይወታችን በጠቅላላ በኃጢኣት ጎዳና ይመላለስ የነበረ ሲሆን፣ ከዳግም መፈጠራችን በኢየሱስ በኋላ በፍትህ በቅድስና ጎዳና ለመጓዝ ነቅተን መጣጣር እንዳለብን የሚል ነው። ቅድስና የሚለው ቃል… ሁላችን ጸጋ ምሥጢር ጥምቀት የተቀበልነው…. ወላጆቻችን በተአምኖተ እምነት ኃጢአታችንን ይቅር ባለልን ‘በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ’ በሚለው እምነት ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ!” በመቀጠልም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ይኽ በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ የሚለው የምንደግመው ተአምኖተ እምነት እንዳሻኝ ሳይሆን አሜን ያልነውን እምነት በዕለታዊ ሕይወታችን መኖር ያለው አስፈላጊነት ሲያሳስቡ፦ “ደካሞች ኃጢአተኞች ኢፍጹማን ነን፣ ኃጢአት ተላምዶ መኖር ያስፈራል፣ በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ ሆኖም ግን እኔ እንደፈልግሁት ነው የምኖረው የሚለው የማይለወጥ ሕይወት መኖር አይገባም፣…እኔ ኃጢአተኛ ነኝ፣ ደካማ ነኝ ቢሆንም ግን ሁሌ ወደ ጌታ መሄድ፣ ‘ጌታ ሆይ አንተ ኃይል አለህና እምነት ስጠኝ እንተ እንደምትፈውሰኝ አምናለሁ’ በምሥጢረ ንስኃ ይፈውሰናል፣ ኢፍጹምነታችን በቅድስና መንገድ ለመጓዝ የሚደግፍ ነው፣ ይህ ለቅድስና የሚደረገው ጉዞ በመጀመሪያም በኋላም የሕይወታችን ጥሪ ነው” እንዳሉ ጂሶቲ ገለጡ።
ቀዳሚወ የተአምኖተ እምነት ተግባር ማለትም በደሙ ዳግም ፈጥሮ ያዳነን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመቀበላችን በፊት በኢፍትሃዊው ጎዳና ነበር እምንመላለሰው፣ ከኢየሱስ በኋላ ጎዳናችን ግን የቅድስና ጎዞ የተመለከተበት ሲሆን፣ ስለዚህ ይኸንን ሁነት መሆናችንን በተናንሽ ተግባሮች አማካይነት ፍትህ የሚኖርና የሚመስከር፣ እግዚአብሔርን በማምለክ የሚኖር እርሱ አልፋና ኦሜጋ ነው። እግዚአብሔርነት ዘወትር ዘለዓለማዊ ነው፣ ኢየሱስ ያለው በመፈጸም የሚኖረው የፍትህና የዳግም መፍጠር ተግባር ተካፋዮች ለመሆን የተጠራን ነን ለምሳሌ ለተራበ እንጀራ ስንሰጥ በኢየሱስ ዳግም መፈጠር ተስፋን በማቅረብ እንሳተፋለን፣ ሆኖም ግን እምነትን ተቀብለን ስናበቃ እምነትን ሳንኖር ስንቀር የተዘክሮ ክርስቲያኖች ሆነን የምንቀር መሆናችን ቅዱስ አባታችን ሲያስተምሩ፦ “ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚለን ከኢየሱስ በፊትና በኋላ ስለ ሆነው ሕይወታችን ግንዛቤው ከሌለን ክርስትናችን ለማንም እርባና አይኖረውም፣ ክርስቲያን ነኝ እላለሁ ሆኖም ግን በአስመሳይነት ጎዳና ስጓዝ እንደ ኢአማንያን ስኖር ወይንም የፈረቃ ክርስቲያናዊ ሕይወት ተጓዥ ሆኜ ስገኝ በእውነቱ ክርስትያናዊ እምነኔ በእውነትና ከምር የምኖረው ሳይሆን ተረስተዋል ማለት ነው። ለብ ያለ ክርስትና፣ ክርስትና በትምህርተ ክርስቶስ የሚቀባ የቀለም ዓይነት እውነተኛ መለወጥ የሌለው ሳይሆን፣ የሚኖር ሕይወት ነው። ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚለውም ‘ሁሉንም ነገር ስለ ክርስቶስ ስል እርሱን ለመቀዳጀትና በእርሱ እገኝ ዘንድ እንደ ጥራጊ ቆጠርሁት’ ይላል። ይኽ ደግሞ የጳውሎስ ሞቅ ያለው ስሜትና አመክንዮ አዘሉ ክርስቲያናዊ ሕይወት ነው። ከክርስቶስ የሚያርቀን ሁሉ ትተን ሁሉን ነገር በክርስቶስ አዲስ አድርገው” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ በማያያዝ ክርስቶስ ልንኖረው የሚፈልገው ክርስትና እንዲህ ባለ ሕይወት የሚኖር መሆኑና ጳውሎስ እንዳደረገው ቅዱሳን ብቻ ሳይሆኑ ብዙ የማይነግርላቸው ክርስትናን በእውነትና በምር የኖሩት ክርስቲያኖች መኖር የሚቻል መሆኑ ቅዱስ አባታችን በማበረታታት እውነትኛው ክርስትና ለመኖርና የምር ክርስቲያኖች እንሆንና በኢየሱስ ክርስቶስ ደም የተቀደሰ ክርስትና ሕይወት ለመኖር እንችል ዘንድ ቅዱስ ጳውሎስ ጸጋ ያማልድልን ብለው ባሰሙት ጸሎት ሥልጣናዊ ስብከታቸውን እንዳጠቃለሉ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.