2013-10-21 16:14:18

የቶሪኖ የመንፈሳዊ ፊልም ፌስቲቫል


RealAudioMP3 ሃይማኖት ዛሬ የተሰየመው በየዓመቱ በኢጣሊያ ቶሪኖ ከተማ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የመንፈሳዊ ፊልም በዓል መግለጫ ዘንድሮ ባካሄደው አስራ ስድስተኛው ክፍለ መግለጫው አንድ ቀን ከሰላም መረጋገጥ በኋላ” የተሰየመው ሰነዳዊ ፊልምና “በእምነት መንፈስ” የተሰየሙት ፊልም ለአቢይ የቶሪኖ መንፈሳዊ ፊልም ፈስቲቫል ሽልማት መብቃታቸው የቫቲካን ረድዮ ልእክት ጋዚጠኛ ማሪያአንጀላ ብሩነት ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
አንድ ቀን ከሰላም መረጋገጥ በኋላ የተሰኘው የኤረዝና የሚሩ ላኡፈር ፊልም በአንዲት የደቡብ አፍሪቃ ትውልድ ዘር ያላቸው እናት አንድ ልጃቸውን ለሞት በዳረገው ፍልስጥኤማዊ ዜጋ መካከል የሚደረገው ውይይት ይኽም ምኅረት ላይ ያነጣጠረ በደቡብ አፍሪቃ ከአፓርታይድ መወገድ በኋላ የተረጋገጠው የእርቅና የምኅረት መንፈስ በመከተል የደቡብ አፍሪቃው የእርቅና ምህረት መርሃ ግብርን ለእስራኤልና ፍልስጥኤም ግጭት መፍትሔ ሊሆን እንደሚችል እንደ አብነት ለማቅረብ ያነጣጠረ ፊልም መሆኑ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ብሩነት አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.