2013-10-21 16:09:19

ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ፦ ስፖርት መላይቱን ዓለም ለማገልገል ተብሎ የተፈጠረ ቋንቋ ነው


RealAudioMP3 በዚህ እየትኖረ ባለው በእምነት ዓመት ምክንያት የባህል ጉዳይ ተንከባካቢው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያነቃቃው የስፖርት በዓል ቀን እ.ኤ.አ. ጥቅምት 20 ቀን 2013 ዓ.ም. ተከብሮ መዋሉ ሲገለጥ፣ የዚህ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ ቀኑን ምክንያት በማድረግ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “ስፖርት መላውን ዓለም ለማገልገል ተብሎ የተፈጠረ ኵላዊ ቋንቋ ነው። በተለያዩ አገሮች ልዩ ከባህልና ካካባቢ ጋር የተጣመረ የተለየ የስፖርት ዓይነት ውደራ ቢኖርም ቅሉ፣ ስፖርት የሚለው ቃል ኩላዊ ነው። የሰው ልጅ የመፍጠር ብቃቱ ዘንድ የተቀረጸ ባህል ነው” ካሉ በኋላ የስፖርት አስተዋጽኦ በእምነት ምስክርነት ዘንድ ምን እንደሚመስል ሲያብራሩ፦ “በስፖርት የመሳተፉ ሂደት ጥቅማ ጥቅሞች ላይ የተመሰረተ ብቻ ሳይሆን የላቀው የሰው ልጅ በፈቃደኝነት በፍላጎቱ በነጻ የሚሰጠው የጥቅል አገልግሎት መግለጫ ነው። እምነት ምንም’ኳ ጸጋ የሚለመንበት ተማጽኖ የሚቀርብበት አቤት የሚባልበት ቢሆንም ቅሉ አንድ ነገር ለማግኘት ተብሎ የሚኖር ወይንም ከጥቅም ጋር የተቆራኘ አይደለም፣ ስለዚህ እምነት በመሠረቱ የሚኖረው እግዚብሔርን ለመከተል ነው። በመሆኑም የፍቅር መግለጫ ነው። በዚህ አመለካከት ሥር ስፖርትን ከእምነት ጋር ውስጣዊ ተወያይነት እንዳለው እንገነዘባለን” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.