2013-10-21 16:04:24

ብፁዕ አቡነ ኵወረብ፦ የቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ፍቅር ለተፈጥሮ


RealAudioMP3 የቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ልዩ ዋና ጸሓፊ በመሆን ያገለገሉት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የግል ልዩ ዋና ጸሐፊ እንዲሆንዋቸው በዚሁ አገልግሎት እንዲቀጥሉ ተሹመው በማገልገል ላይ የሚገኙት ብፁዕ አቡነ አልፍረድ ኵወረብ “ለአንድ ሰብአዊ ሥነ ምኅዳር” በሚል ርእስ ሥር ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ባገለገሉትበት ዓመታት የእግዚአብሔር የእጅ ሥራ ስለ ሆነው ፍጥረቱ ሁሉ በተለያየ ወቅት ያስትላለፉት መልእክት የሰጡት ሥልጣናዊ አስተምህሮና ምዕዳን ያሰባሰበ ለተፈጥሮ ያላቸው ፍቅር የሚያወሳ መጽሓፋቸው በተሳተፉበት የቫቲካን ማተሚያ ቤተ በፐርደኖነ፦ ማዳመጥ ማንበብ ማደግ” በሚል ርእስ ሥር በመካሄድ ላይ ባለው ሰባተኛው ባህላዊ መግለጫ ለንብባብ እንደበቃ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሉካ ኮሎዲ አስታወቁ።
ብፁዕ አቡነ ኵወረብ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ በዚህ መግለጫ እዲሳተፉ ለቀረበላቸው ጥሪ በማመስገን፣ ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሰጡት የእምነት የሥነ እውቀት የቲዮሊጊያ የፍልስፍና የሥነ ቅዱስ መጽሓፍ ጥልቅ አስተምህሮና ምስክርነት ዙሪያ አስተዋጽኦ ለማበርከት የነበራቸው ፍላጎት የቆየ መሆኑ ገልጠው፣ በእውነቱ በቅርብ እንዲያውቁዋቸው እድል ያገኙና ጸጋም መሆኑ ዘክረው ስለ ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በተባለ በማጠጋጋት በይምሰል ከሚባለው ብዙ አስተያየት መላቀቅ ካለው አስፈላጊነት በመንደርደር ጭምር የደረሱት መጽሐፍ መሆኑ ገልጠው፣ እያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያን አባል ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አስተዋጽኦ ሊያበረክት የተጠራ ነው። ስለዚህ ከዚህ አኳያ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ለሚያገለግለው የቫቲካን ማተሚያ ቤት የሚያትማቸው መጽሕፍት በአንባቢያን ዘንድ እንዲደርሱ ማድረግ የሁላችን ተሳትፎ ይጠይቃል፣ ይኸንን ሁሉ እግምት ውስጥ በማስገባት፣ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሥልጣናዊ ትምህርት በተለያየ የሥነ ምርምር ዘርፍ ሥር በማንበብ ለአንባቢያን የማቅረቡ ኃላፊነት የሁሉም ማኅበረ ክርስቲያን በተለይ ደግሞ ክርስቲያን የሥነ ባህል አካላት ጥሪ ነው በማለት የሰጡት ቃለ መጠይቅ እዚህ ላይ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.