2013-10-21 16:01:25

በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የተሾሙት የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ቀዳሜ መልእክት


RealAudioMP3 የቅድት መንበር ዋና ጸሐፊ በመሆን እንዲያገለግሉ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሾሙዋቸው ብፁዕ አቡነ ፔትሮ ፓሮሊን እንደ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ፊርማቸው የተኖረበት ቀዳሚ መልእክት ለአውስትራሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።
ቅዱስ አባታችን የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ፓሮሊን ፊርማ የተኖረበት ባስተላለፉት መልእክት በአውስትራሊያ ደቡባዊ ምስራቅ ክልል ተከስቶ በነበረው መጠነ ሰፊ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ያስከተለው የሰውና ንብረት ምክንያት ለአገሪቱ ሕዝብ ቅርበታቸውና ጸሎታቸው ለማረጋገጥ ብሎም ሐዋርያዊ ቡራኬአቸው ለማስተላለፉ ለአውስትራሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የእኚህ አዲሱ የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ፍሪማ የተኖርበት ባስተላለፉት መልእክት የሞት አደጋ ያጋጠማቸው እግዚአብሔር በመንግሥቱ እንዲቀበላቸው የቆሰሉት ፈጣን ፈውስ ቤትና ንብረታቸው ላጡት ለሥራ አጥነት አደጋ ለተጋለጡት የሁሉም ድጋፍ እንዳይለያቸው ጥሪ ማቅረባቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ጉዳይ ካሰራጨው መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.