2013-10-21 16:06:45

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ ፖሊቲካ ግልጽና ታዋቂ የሚሰዋ ፍቅር የመኖር ቅርጽ ነው


RealAudioMP3 የመንግሥታትና የፖለቲካ አካላት ጠባቂ ቅዱስ ቶማስ ሞሮ ቅዱስ መቃብር ለመሳለም ወደ ካንተርበርይ መንፈሳዊ ንግደት ለሚፈጽሙት የተለያዩ የኢጣሊያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የሕግ መወሰኛው የበላይ ምክር ቤት አባላት የተለያዩ የአገሪቱ የፖለቲካ ሰልፎች አባላት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅድስት መንበር ጠቅላይ ጉዳይ ተተኪ ዋና ጸሓፊ አንጀሎ በቺዩ ፊርማ የተኖርበት “የቅዱስ ቶማስ ሞሮ ዱካ መከተል ማለት ፖሊቲካ ግልጽና ታዋቂ የሚሰዋ ፍቅር መኖር የሚለው የላቀው ባህርዩ መኖር ማለት ነው” በሚል ቋሚ ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
በዚህ በተካሄደው መንፈሳዊ ንግደት የኢጣሊያ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕንጻ ቤተ ጸሎት መንፈሳዊ መሪ ብፁዕ አቡነ ሎረንዞ ሌውዚ የሚሳተፉም ሲሆን፣ ቅዱስ ቶማስ ሞሮ የመንግሥታትና የፖለቲካ አካላት የሁሉም የፖሊቲካ ሰልፍ አባላትና የጠበቆች ጠባቃ ቅዱስ በማለት በይፋ ውሳኔውን ያወጁት ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ መሆናቸው ያስታወሰው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ ይኽ ዓይነቱ መንፍሳዊ ንግደት ፖለቲካ ያለው የላቀው ክብሩን የሚያስገንዘብና ፖለቲካ የሚሰዋ ፍቅር አብነት የሚከተል ለማኅበራዊ ጥቅም አገልግሎት ጥበብ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባስተላለፉት መልእክት ገልጠው፣ ፖሊቲካ ያለው የላቀው ክብሩ በማንም እንዳይዘነጋ አደራ እንዳሉና በርግጥ እምነት ፖሊቲካ መፈጸም የሚገባው ጉዳይ ወይንም ደንብ መመሪያ የሚያመለክት ሳይሆን ፖለቲካ የላቀው ክብሩ እንዲኖር የሚደገፍ ሲሆን፣ ይኽንን መገንዘብ በጥልቅ መኖር ለማኅበራዊ ጥቅም ማገልገል እንደሚያግዝና እውነተኛው የአገርና የሕዝብ ፍቅር እንዲኖር የሚደግፍ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባስተላለፉት መልእክት በጥልቅና በስፋት ማብራራታቸው ይጠቁማል።







All the contents on this site are copyrighted ©.