2013-10-21 15:58:53

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ለሥነ ጥበብ ሃብት ጠባቂ ማኅበር፦ ቤተ ክርስቲያን የእምነት ውበት ለመግለጥ ሥነ ጥበብ ትጠቀማለች


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 19 ቀን 2013 ዓ.ም. 30ኛው ዓመተ ምሥረታው ላከበረው ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ ለቫቲካን ቤተ መዘክር የሥነ ጥበብ ሃብት ለተገቢ እቃቤ ዓላማ የኤኮኖሚያዊ ድጋፍ አቅራቢ “Patrons of Arts-የሥነ ጥበብ ጠባቂያን” ማኀበረሰብ ባስተላለፉት መልእክት፣ ይኽ ማኅበረሰብ የቫቲካን ቤተ መዘክር የሥነ ጥበብ ሃብት ኅዳሴአዊ እንክብካቤና እቃቤ ዓለማ በማድረግ የሚሰጠው ድጋፍ በማመስገን የሰብአዊ መንፈሳዊ አስተንፍሶ ምስክር መሆናቸውም ጠቅሰው ቤተ ክርስቲያን ይላሉ ቅዱስ አባታችን የእምነት ውበት ለመመስከር ሥነ ጥበብ ትየከሳለች እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መልእክት፦ “በተለያየ ዘመን ቤተ ክርስቲያን የተቀበለችው የእምነት ሃብትና ዕጹብ ድንቅ የሆነው የእግዚአብሔር ፍጥረት ወንጌላዊው መለእክቱን እግዚአብሔር በአርአያውና አምሳያው የፈጥረው በአሳከፊው ሐጢአት በሞት ፍጻሜ የተነካውን ሰብአዊ ፍጡር የላቀው ሰብአዊው ክብሩን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ዳግም የተጎናጸፈውን ድህነትና መወለድን ለማበሰር ሥነ ጥበብ ትየከሳለች” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ በመቀጠል፦ “የቫቲካን ቤተ መዘክር በአይነቱና በታሪኩ ልዩ በሆነው ባለው የሥነ ጥበብ ሃብት ለጎብኚዎችና ለመንፈሳውያን ነጋድያን መስኅብ በመሆን ሥነ ጥበብ አማካይነት የሰብአዊ መንፈሳዊ አስተንፍሶ እንደሚመሰከር” ቅዱስ አባታችን ገልጠው፣ “እናንተ የዚህ ማኅበረሰብ አባላት በምትሰጡት አገልግሎት በቤተ ክርስቲያን ተልእኮና ሕይወት ያላችሁ ውስጣዊው ሱታፌ ትመሰክራላችሁ፣ እናንተ የምትሰጡት አገልግሎት የዚያ የሁሉም ሰው ልጅ ልባዊ መጠባበቅ ለሚያደርግበትና የላቀው የሰው ልጅ አስስተንፍሶ መግለጫ የሆነው ሥነ ጥበብ የመጣው ገና ለሚገለጠው የእግዚአብሔር መንግሥት ውበቱ መልካም የውሁድ ቅኝቱና ሰላሙ የምትኖሩት ገጠመኝ መግለጫ ይሁን” በማለት ያስተላለፉት መልእክት እንዳጠቃለሉ ጂሶቲ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.