2013-10-18 16:30:24

ቫቲካን፦ ቅድስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የፍልስጥኤም መንግሥት ርእሰ ብሔር ተቀብለው አነጋገሩ


እ.ኤ.አ. ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለይፋዊ ጉብኝት አገረ ቫቲካን የገቡትን የፍልስጥኤም ርእሰ ብሔር ማህሙድ ኣባስን (ኣቡ ማዘን) በቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ሕንጻ ተቀብለው ማነጋገራቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳድሮ ጂሶቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
በተካሄደው ግኑኝነት ስለ መካከለኛው ምሥራቅ ሁኔታ ለየት ባለ መልኩም የእስራኤልና ፍልስጥኤም የሰላም ድርድር ጅማሬ ርእሰ ሥር ጥልቅና ሰፊ ውይይት መደረጉ የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ሕትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮና አቡ ማዘን የእስራኤልና ፍልስጥኤም የሰላም ድርድር መርሃ ግብር አስችኳይና ተገቢ መፍትሄ የሚያሻው እጅግ አንገብጋቢ የሆነው ግጭት በሁሉም በጉጉት የሚጠበቀው ቅንና ዘላቂ መፍትሔ ያስገኝ ዘንድ ተስፋቸው በማኖር ስለዚሁ ሁለቱ የሰላም ተደራዳርያን አገሮች በዓለም አቀፍ ማኅበርሰብ ተደግፈው ለሰላም መረጋገጥ ወሳኝ የሆነ ቆራጥ ውሳኔ ያረጋገጡ ዘንድ ጥሪ በማቅረብ ከዚሁ ጋር በማያያዝም በሶሪያ ስላለው ወቅታዊው ሁኔታ ርእስ ዙሪያ በመወያየት የአመጽ አመክንዮ በማግለል እርቅና ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችል ሁኔታ ይመቻችም ዘንድ በተካሄደው ግኑኝነት ጥሪ መቅረቡ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ካሰራጨው መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።
የቅድስት መንበርና የፍልስጥኤም ክሌአዊ ግኑኝነት አመርቂ መሆኑና ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በፍልስጥኤም ጠቅለል ባለ መልኵ ህልውናዋና የምታከናውነው እንቅስቃሴ በተመለከተ የተደረሱት ስምምነቶች አርኪ መሆኑ በተካሄደው ግኑኝነት እንደተሰመረበት የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅተመት ክፍል መግለጫ አክሎ፣ በመጨረሻ ቅዱስ አባታችንና አቡ ማዘን በፍልስጥኤም ክሎሎችና ጠቅላለ ባለ መልኩም በመካከለኛው ምስራቅ የማኅበረ ክርስቲያን ህልውና በሚል ርእሰ ጉዳይ በመወያየት ማኅበረ ክርስቲያን በመካከለኛው ምሥራቅ ለጋራው ጥቅም መረጋገጥ የሚሰጠው አስተዋጽኦ ወሳኝ መሆኑ እንደተረጋገጠም አስታውቀዋል።
ከግኑኝነቱ ፍጻሜ በኋላ አቡ ማዘን ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቅድስት መሬትን ይጎበኙ ዘንድ ይፋዊ ጥሪ እንዳቀረቡላቸው አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.