2013-10-11 15:56:59

ብፁዕ አቡነ ፓሊያ፦ ልዩ ሲኖዶስ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለቤተሰብ ያላቸው ግብረ ፍቅር ነው


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአገረ ቫቲካን እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 5 ቀን እስከ ጥቅምት 19 ቀን 2014 ዓ.ም. እንዲካሄድ የጠሩት ሦስተኛው ጠቅላይ ጉባኤ የመላ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ የሚከተለው ርእሰ ጉዳይ፦ የቤተሰብ ሃዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተጋርጦ በአስፍሆተ ወንጌል ይዘት የሚል እዲሆን ውሳኔ ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ ኣባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ባለፈው ሳምንት በቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ሕንፃ ባለው የጉባኤ አዳራሽ ተገኝተው በሰጡት ጋዜጠዊ መግለጫ በማሳወቅ፦ “ይኽ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የጠሩት ልዩ ሲኖዶስና የሚከተለው ርእሰ ጉዳይ ቅዱስነታቸው የማኅበረ ክርስቲያን ሂደትና አስተንትኖ ይኽም ሁሉም በቤተ ክርስቲያን እንደየ ጥሪው የተሳታፊንነት ኃላፊነት እንዳለው የሚያረጋግጥ ነው” እንዳሉም የሚታወስ ሲሆን ስለዚሁ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በ 2014 ዓ.ም. ሊካሄድ የጠሩት ልዩ የመላ ካቶሊካውያን ብፅዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ፦ “ቤተሰብ አጅግ አስፈላጊ ሃብት ወይንም ጸጋ ነው። በአሁኑ ወቅት እኔነት ከፍ ከፍ የሚያደርገ ባህል እኛ የሚለውን መለያ ከፍ ከፍ የሚያደርግ እንዲሆን ማድረግ ያለው አስፈላጊነት ለማስገንዘብ” መሆኑ የቤተሰብ ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ቪንቸስንዞ ፓሊያ እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 23 ቀን እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም. ይኽ በሳቸው የሚመራው ጳጳሳዊ ምክር ቤት የሚያካሂደው ዓመታዊ ምሉእ ጉባኤ ምክንያት በቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ ተገኝተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሰመሩበት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፓውሎ ኦንዳርዛ አስታወቁ።
በዚህ አጋጣሚም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ገና የቦኖስአይረ ሊቀ ጳጳሳታ እያሉ ግና የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከመመረጣቸው በፊት እ.ኤ.አ. ከ 1999 ዓ.ም. እስከ 2013 ዓ.ም. ቤተሰብ ስለ ሕይወት ርእስ ዙሪያ የጻፉትና ያቀረቡት ሓሳብ በማጠቃለል ታትሞ ለንባብ የበቃው ብፁዕነታቸው ጠቅሰው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በእምነት ዓመት ምክንያት እ.ኤ.አ. ጥቅምት 26 ቀንና ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ለመሳለምና መፍንፈሳዊ ንግደት ለመፈጸም ከቅዱስነታቸው መሪ ቃል ለመቀበል ከዓለም ከተወጣጡት የቤተሰብ ጉባኤ ጋር እንደሚገናኙ ጠቅሰው ይኽም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ከቤተሰብ ጉባኤ ጋር ሲገናኙ የመጀመሪያቸው እንደሚሆን ማሳወቃቸው ፓውሎ ኦንዳርዛ አመለከቱ።
ብፁዕ አቡነ ፓሊያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፦ ቤተሰብ፦ ቤተሰቦች ለሕበረተሰብ ዓቢይ ሃብት ናቸው፣ እግዚአብሔር ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠረ ይኽም እኔነትና እኛነት ያጣመረ ሱታፌ እንዲሆንም አደረገ፣ ሆኖም በአሁኑ ወቅት እኔነትን የሚያስተጋባ ከፍ ከፍ የሚያደርግ ባህል እየተስፋፋ ባለበት ወቅት በእውነት እኛነት ከፍ ከፍ ማድረግ ወሳኝ ነው። ቤተሰብ የሕብረተሰብ መሠረት ነው” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ኦንዳርዛ በማያያዝ፦ “ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የጠሩት ሦስተኛ ልዩ የመላ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ከእሳቸው ጋር በመሆን ተጋብተው ስለ ተፋቱ ቃል ኪዳንስ ስላፈረሱት በቤተክርስቲያን ሱታፌአቸው ምን እንደሚመስል እንዴት ባል መልኩ እንዲኖሩት አነዚህን የቤተ ክርስቲያን ልጆች በተመለከተ ልንከተለው የሚገባ መንገድ በጥበብና በጥንቃቄ ምን መሆን እንዳለበትና ቤተሰብ ጽንስ ማስወርድ አለ ቃል ኪዳን ስል ሚጸናው ጋብቻ ጽንስ የመከላከል ስለ ተባሉት ጉዳዮች በቅርቡ ቺቪልታ ካቶሊካ ከተሰየመው መጽሔት በኩል ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ ቤተሰብ እንዲህ ባለ ጥያቄ ማጠቅላለ ቤተሰብ ያለው ትርጉም ማሳነስ ይሆናል፣ ስለዚህ ከጥያቄው ባሻገር መለመልከት ያሉትን ሃሳብ አስታውሰው በዚህ በንገድም በጥበብ በሳቸው መርህነት ከሳቸው ጋር መራመድ የሚያሳስብ ነው” ካሉ በኋላ በጀርመን የፍሪበርግ ሰበካ የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ጉዳይ የሚከታተለው ቢሮ ቃል ኪዳን ስላፈረሱ ስለ ተፋቱ ተፋተው ዳግም ስለ ተጋቡ ጉዳይ በተመለከተ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸ መጠይቅ ሲመልሱ፦ በቅድሚያ ይኽ የሚባለው የፍሪበርግ የቤተሰብ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ሰበካው በፍያ ያሰራጨው መግለጫ የለም፣ ለዚህ ደ ስፓይገል ዕለታዊ ጋዜጣ ያሰራጨው ዜና ምክንያት ነው አስተያየት እየተሰጠበት ኵላዊ መልስ የሚያሻው ጉዳይ በተለየ የመፍትሔ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚሰጠው የተለየ መፍትሔ ሊፈጠረው የሚችለው ግራ አጋቢ ሁኔታ እንዳይኖር ኩላዊ መልስ የሚሻው ጥያቄ መሠረት ማኅበረ ክርስቲያን በሙሉ ሱታፌ ለመራመድ እንዲችል በኩላዊት ቤተ ክርስቲያን ኩላዊነት ባህርይ አስፈላጊ ነው ስለዚህ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በተለያየ ወቅት በመደጋገም ስለ ቤተሰብ ርእሰ ጉዳይ በተመለከተ በተለይ ደግሞ በቤተ ክርስቲያን ይፈታ የሚባል ውሳኔ የሚሰጥበት ጋብቻና ስለ ሚፈጠረው ዳግማዊ ትሥሥር በተመለከተ ሥልጣናዊ ምዕዳን ሰጥተዋል እንደሚታወሰውም መስከረም 16 ቀን 2013 ዓ.ም. ከሮማ ሰበካ ካህናት ጋር ተገናኝተው ቅዱነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በልባቸው የነበረ ብዙዉን ጊዜ የተወያዩበት አበክረው ያሰመሩበት ጉዳይ እንደነበርም በማስታወስ እንዳሉት፦ “ችግሩ የተፋታ ወይንም ዳግም ያገባ ቅዱስ ቍርባን ሊቀበል ይችላል ወይስ አይችልም በሚል ሃሳብ ሥር ብቻ ውይይት ሲደረግበት ይታያል፣ በዚሁ ዙሪያ ሥር ችግሩን የሚመለከት በእውነቱ ችግሩ ምን መሆኑ አልተረዳውም ማለት ነው። በፍችና በዳግመ ጋብቻ ሥር የሚኖሩ ቤተሰቦች በተመለከተ ቤተ ክርስትያን አቢይ ኃላፊነት አላት፣ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን የታሰረው ምሥጢረ ተክሊል ዙሪያ ስላለው የይፈታ ውሳኔ በማጤን ለችግሩ መፍትሔ ልትሰጥበት ይግባል” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ኦንዳርዛ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.