2013-10-11 15:46:08

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለኮሎምቦስ ፈረሰኞች አዳዲስ መንገዶች ለማሕበረሰብአዊ የሕዳሴ ኃይል የሆነውን ወንጌል ፈልጉ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ጥቅምት 09 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአገረ ቫቲካን የቅድት መንበር ሐዋርያዊ ሕንፃ የኮሎምቦስ ፈረሰኞች ማኅበር የመሥተዳድር ምክር ቤት አባላት ተቀብለው ሥልጣናዊ ምዕዳን መለገሣቸው የተካሄደው ግኑኝነት የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ሲቻል፣ ይኽ በበላይ ፈረሰኛ ካርል አንደርሰን የሚመራው የሰሜን አመሪካ ካቶሊካዊው የግብረ ሰናይ ማኅበር የእምነት መስካሪነቱንና ለተናቁት በድኽነት ጫንቃ ሥር ለሚገኙት በሚያከናውነው ግብረ ሠናይ ቅርበቱን እንዲቀጥልበት በማሳሰብ፣ ከዚሁ ጋር በማያያዝ ቅዱስ አባታች የቅዱስ ጴጥርስ ተከታይና የቅድስት መንበር የግብረ ሠናይ ተግባር ግቡን እንዲመታ ይኽ የኮሎምቦስ የፈረሰኞች ማኅበር የሚሰጠው አስተዋጽኦ ምክንያት አመስግነው፣ በዚህ መንፈስ ከዚሁ የክርስቶስ ወኪል በምድር የግብረ ሠናይ ተግባር ደጋፊ በሚል ከሚከተላቸው ዓላማዎች አንዱ በማድረግ ከተቋቋመው ማኅበር የበላይ መስተዳድር ምክር ቤት አላባት ጋር በመገናኘት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይና የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ግብረ ሠናይ እግብ ለማድረስ የሚሰጠው አስተዋጽኦ በማሰብ የማኅበሩ አንዱ ተግባርም ጸሎት ተጋድሎና ሓዋርያዊ ተግባር መሆኑ በማስታወስ በዚህ ቅዱስ ተግባር አማካኝነትም በተለያዩ የዓለማችን ክልል በሰበካዎች ቁምስናዎች የሚሰጠው አገልግሎት፦ “በጸሎትና በግብረ ሠናይ እምነትን መመስከር፣ የተናቁት የድኾችን ወንድሞች መሠረታዊ ጥያቄ መልስ መስጠት፣ የተሰኙት የማኅበር ዓላማ ነው። የማኅበሩ መሥራች ክቡርነታቸው አባ ሚካኤል ምክጊቭነይ ከመንፈስ ቅዱስ ለተቀበሉት ራእይ በዓለም የወንጌል እርሾ የሚሆኑትን የማሕበርሰብ መንፈሳዊ ኅዳሴ ኃይል የሚሆኑት አዳዲስ መንገዶችን በመከተል ታማኞች ሆናችሁ ተጓዙ” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልዑክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የእምነት ዓመት ወደ ማጠቃለያው እየተቃረበ መሆኑ በማስታወስም በናዚሬቲቱ ጠባቂ በሆነው ተደናቂና ማራኪ ቋሚና ቀጣይ ክብር እርሱም ምሉእነት ታማኝነት መረጋጋት መለያው ለሆነው ለቅዱስ ዮሴፍ አማላጅነት የኮሎምቦስ ፈረሰኞች ማኅበር በማማጸን ለመላ ሕዝብና ለካቶሊካውያን በሞላ በዚህ በቅዱስ ዮሴፍ አብነት የታቀበው እምነት በምትኖሩት የማኅበሩ መንፈሳዊነት አማካኝነት እንዲመሰክሩ ማሳሰባቸው አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.