2013-10-11 15:50:11

ቅዱስ መንበርና ክሮአዚያ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ጥቅምት 09 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአገረ ቫቲካን ይፋዊ ጉብኝት ለማካሄድ የገቡትን የሪፓብሊካዊት ክሮአዚያ መራሔ መንግሥት ኢቮ ጆሲፖቪችን በቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ሕንፃ ተቀብለው ማነጋገራቸው የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ካሰራቸው መግለጫ ለማወቅ ሲቻል ርእሰ ብሔር ጆፊፖቪች ከቅዱስ አባታችን ተሰናብተው በቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ዶመኒክ ማምበርት ከተሸኙት ከቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ጋር መገናኘታቸው ያመለክታል።
የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ፦ በተካሄደው ግኑኝነት የክሮአዚያ ካቶሊካዊ እምነት ባህል የቅድስት መንበርና የክሮአዚያ ክሌአዊ ግኑኝነት አመርቂነት ይኽም በአራት የስምምነት አንቀጾች ሥር የተደረሰው የቆየው የጋራው ስምምነት ለማሕበራዊ ጥቅም ላይ ያቀና በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ግኑኝነትና ትብብር እጅግ እንዲጠነክር ማድረጉንም በተካሄደው ግኑኝነት እንደተሰመረበት ያመለክታል።
ክሮአዚያ የኤውሮጳ ኅብረት አገሮች አባላ ለመሆን መብቃቷ በማስታወስም የሁለቱ አገሮች የጋራ ጥቅም የሚባሉት ጉዳዮች በመዳሰስ በዚህ በአሁኑ ወቅት ተከስቶ ባለው ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ ቀውስ ለክሮአዚያ ተጋርጦ መሆኑና ከዚህ ችግር ለመላቀቅ ክሮአዚያ እየተከተለቸው ያለው መንገድ ብሎም በቦስኒያና ኤርዘጎቪና የሚገኙት የክርአዚያ ተወላጆች ሁኔታ ጭምር ውይይት ተደርጎበት በመጨረሻ ዓለም አቀፍ ነክ ጉዳዮች ዙሪያ በተለይ ደግሞ የማኅበረ ክርስቲያን ሁኔታ በዓለም ዙሪያ በሚል ርእሰ ሥር የሃሳብ ልውውጥ ማድረጋቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.