2013-10-09 16:17:19

ብፁዕ ካርዲናል ማራዲያጋ፦ ቅዱስ አባታችን ሥልጣን የፍቅር አገልግሎት ማለት መሆኑ ምስክር


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ጥቅምት 08 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከተሾሙበት ቀናን ሰዓት ጀምረው ግልጽ ያደረጉት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ተባባሪዎች አበይት የቅድስት መንበር ሓዋርያዊ መስተዳድር መዋቅራዊ ቅዋሜው ማደስ የሚል ፍላጎት መሠረት በማድረግ በዚሁ እቅድ የሚተባበሩዋቸው በስምንት ካርዲናሎች የቆመ የመማክርት አካላት መመልመላቸውም የሚታወስ ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ መማክርት አባል በማድረግ ከመረጡዋቸው አንዱ የሆንዱራስ ርእሰ ከተማ ተጉቺጋልፓ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ኦስካር አንድረስ ሮድሪገዝ ማራዲያጋ በአባ ሚከለ ጁሊዮ ማሺያረሊ “ቅርብ ር.ሊ.ጳ.” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት በታዉ ማተሚያ ቤት የታተመው መጽሓፍ እዚህ በራዲዮ ቫቲካን ሕንፃ በሚገኘው ማርኮኒ የጉባኤ አዳራሽ ለንባብ በበቃበት አውደ ጥናት ተገኝተው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ላይ ያተኮረ ባሰሙት ንግግር፣ °ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሥልጣን የፍቅር አገልግሎት ማለት መሆኑ በቃልና በተግባር የሚመሰክሩ ናቸው። ሥልጣን እንዲኖር ማእከላዊነት ግድ አይደለም፣ ምክንያቱም ሥልጣን የሚያሳድግ የፍቅር አገልግሎት ነው። የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በቤተ ክርስቲስያን የንጉሣዊ መስተዳድር ሥርዓት እዚህ የማዘው እኔ ነኝ የሚል የሥልጣን ትርጉም የሚከተል ሳይሆን ቃሉ በላቲን ቋንቋ ሲገለጥ፣ የሚያሳድግ፣ የሚደርስ የሚሰንድ የሚል ቃል የሚያጠቃልልም ነው። ስለዚህ ቅዱስ አባታችን ሥልጣን የሚለው ቃል እንዲህ ባለ መልኩ ነው የሚረዱት” በማለት ካብራሩ በኋላ ከዚሁ ጋር በማያያዝ ይህ እሳቸው በአባልነት የሚገኙበት ቅዱስ አባታችን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ተባባሪዎች አበይት የቅድስት መንበር ሓዋርያዊ መስተዳድር መዋቅር ለማደስ ያላቸው ፍላጎት መሠረት ስምንት ካርዲናሎች ያቀፈ ያቆሙት የመማክርት አካላት በቅርቡ ቀዳሜ ስብሰባ ማካሄዱንም አስታውሰው የመጀመሪያው ውይይት ሕዳሴው በሙላት ለማረጋገጥ እንዲቻል በተለያዩ አገሮች የሚገኙት ብፁዓን ካርዲናሎች ካህናት ደናግል የተለያዩ የመንፈሳዊ ማኅበር አባላትና ምእመናን ከሚያሰባሰበው ሃሳብ የሚመነጭ ማርድረግ የሚል ሥልት እንዲከተል ውሳኔ እንዳቀረበ ገልጠው ይኽም እ.ኤ.አ. በ 2007 ዓ.ም. ተካሂዶ በነበረው በመላ ላቲን አመሪካና ካራይቢ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በዚያኑ ወቅት ቅዱስ አባታችን የቦኖስ አይረስ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል እያሉ አሰምተዉት በነበረው ንግግር ቤተ ክርስቲያን ከገዛ እራስ መውጣት ሊያስፈራት አይገባም ያሉት ሃሳብ ይኸው የቅዱስ ጴጥሮት ተከታይ ሆነው ከተመረጡ በኋላም መለስ ብለው በማጤን ለኅዳሴ መሠረት እንዲሆን እያደረጉት ነው ወቅቱም የሚጠይቀው ጉዳይ ነው ብለው እርግጥ ነው ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ገቢራዊ ለማድረግ ከተለያየ ነጥብ በመንደርደር የተጀመረ ጉዳይ ነው። ለምሳሌ የሊጡርጊያ ኅዳሴ የማኅበራዊ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ኅዳሴ ከተከናወነ በኋላ ይኸው የብፁዓን ጳጳሳት ኁባሬነት ላይ ያነጣጠረ ኅዳሴ እግብር ላይ ለማዋል ቅዱስ አባታችን ቅድሚያ የሚሰጡት ነጥብ ነው እንዳሉ ለማወቅ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.