2013-10-09 16:14:41

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ከልብ የመነጨ ጸሎት ወደ አብ የሚወስድ በር እንዲከፈት ያደርጋል ተአምራትንም ያፈልቃል


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ጥቅምት 09 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጧት በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት እንደ ተለመደው መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው የዕለቱ የመጽሓፍ ቅዱስ ንባባት ተንተርሰው፦ “ጸሎት ተአምር ይሠራል” በማለት እውነተኛ ከልብ የመነጨ ጸሎት ያለው ኃይል ለማብራራት ባሰሙት ስብከት የዕለቱ ወንጌል ስለ ማርታና ማርያም የሚያወሳ የአገልግሎትና የጸሎት አብነት የሆኑንት ጠቅሰው፦ “በማርታ ፊት ማርያም የመረጠችው በጌታ ፊት ሆና እርሱን በማድነቅና በአግርሞት ልክ እንደ የአንድ ሕፃን በመደነቅ መንፈስ ስትመለከት፣ ትርጉም የሌለው ጉዳይ አድርጎ የሚመለከትም ይኖራል። ማርያም ጌታን ታዳምጠውና በልቧም ትጸልይ ነበር፣ ስለዚህ ጌታ የሚለን በሕይወት ቀዳሚውና መሠረታዊው ጉዳይ ጸሎት ነው ይለናል። ይኽ ማለት ደግሞ በቃል የሚነበነብ ጸሎት አይደለም፣ የልብ ጸሎት፣ ጌታን የሚመለከት እርሱን የሚያስተነትን ጌታን የሚያዳምጥ የሚጠይቅ ጸሎት ማለት ነው። ስለዚህ ተአምረኛ ጸሎት ማለት ነው። ሁላችንም ጸሎት ተአምር እንደሚሠራ እናውቃለን” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።
“ማርታ ምን ትሠራ ነበር። ጸሎት አለ ማድረግ ነበር የምታከናውነው። ሥራዋም ጸሎት አለ ማድረግ ነው። እንደ ዮናስም በቀላሉ ሓሳባቸውን የማይለውጡ ምኅረት ሳይሆን ፍርድ ምኅረት አልቦ የፍርድ ውሳኔ የሚል ቆራጥ የፍርድ ውሳኔ ትንቢት የሚያውጅ፣ ፍርድ ይገባቸዋል የሚል ዓይነት አስተሳሰብ በልቡ ያስቀመጠ ይመስላል፣ ስለ ሕዝብ ግን ከጌታ ምኅረትን አይጠይቅም፣ ገዛ እራሳቸውን ቅንና ፍትሃውያን ነን በማለት በሌሎች ላይ ፍርድ ይወርድ ዘንድ ጥረት የምናደርግ ብዙ ነን። በመጨረሻም ዮናስ ራስ ወዳድ እንደነበር የታወቀ ነው። ጌታ የነነዌን ሕዝብ እንዳዳነ ዮናስ ይቆጣል አንተ ሁሌ መኃሪ ነህ፣ ይቅር ትላለህ ይላል። ምኅረት አልቦ ፍርድ ይኽ ደግሞ ልክ እንደ ማርታ ውስጣዊነት የሚያገል ተግባር ወይንም አገልግሎት ነው” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።
በመጨረሻ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ስብከታቸው ጸሎት አለ ልብ ቅመራዊ ቃል ብቻ ሆኖ እንደ አንድ ጨለምተኛ ተስፋ አልቦ ወይንም ምኅረት ያልታከለው ፍርድ ፍትህ አለ ምኅረት የተሰኙት ክርስቲያኖች የሚያጠቃ ፈተና መሆኑ በሚያስገነዝብ ሃሳብ ሲያጠቃልሉ፦ “እኛም ሳንጸልይ ስንቀር የማንጸልይ ስንሆን ልባችን ለጌታ ዝግ እናደርጋለን፣ አለ መጸለይ በርን ለጌታ ዝግ ማድረግ ማለት ነው። ምክንያቱም በር ከተዘጋ እርሱ ምንም ነገር ለማድረግ አይችልም፣ እንዲገባ በሮቻችን ካለከፈትንለት ምንም ነገር ለማድረግ አይችልም። ችግር ሲያጋጥም በአንድ አስቸጋሪ ወቅትና በሚከሰተው የተፈጥሮና ሰብአዊ ችግር ምክንያት ሲጸለይ በርን ለጌታ መክፈት ማለት ነው። ምክንያቱም እርሱ ይገባ ዘንድ የሚቀርብ ጸሎት በር የሚከፍት ጸሎት ነው። እርሱም ነገሮች ያስተካክላል፣ ስለዚህም ነው የሚጸለየው። በሮቻችን ከዘጋንለት እርሱ ምንም ነገር ለማድረግ አይችልም፣ ስለዚህ ያችን የበለጠውን የመረጠቸውን ማርያምን እናስብ፣ እንዴት ለጌታ በሮቻችን ክፍት ለማድረግ እንደምንችልም አብነት ነች” እንዳሉ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.