2013-10-09 15:56:06

ሲኖዶስ
የቤተሰብ ጉዳይ የሚመለከተው ሃዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተጋርጦ በአስፍሆተ ወንጌል ይዘት


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአገረ ቫቲካን እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 5 ቀን እስከ ጥቅምት 19 ቀን 2014 ዓ.ም. እንዲካሄድ የጠሩት ሦስተኛው ጠቅላይ ጉባኤ የመላ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ የሚከተለው ርእሰ ጉዳይ፦ ቤተሰብ ጉዳይ የሚመለከተው ሃዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተጋርጦ በአስፍሆተ ወንጌል ይዘት” የሚል እዲሆን ውሳኔ ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ ኣባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ትላትና በቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ሕንፃ ባለው የጉባኤ አዳራሽ ተገኝተው በሰጡት ጋዜጠዊ መግለጫ ገልጠው፦ “ይኽ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የጠሩት ልዩ ሲኖዶስና የሚከተለው ርእሰ ጉዳይ ቅዱስነታቸው የማኅበረ ክርስቲያን ሂደትና አስተንትኖ ይኽም ሁሉም በቤተ ክርስቲያን እንደየ ጥሪው የተሳታፊንነ ኃላፊነት እንዳለው የሚያረጋግጥ ነው” ብለዋል።
“ቤተ ክርስቲያን” ይላሉ አባ ሎምባርዲ፦ “በአስተንትኖና በጸሎትና እንዲሁም የጋራና እጅግ አስፈላጊ በሆነው ነጥብ ዙሪያ በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይና በብፁዓን ጳጳሳት መርህነት ሥር የሚከናወን ኵላዊ ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ከዚህ ውስጥ የቤተሰብ ጉዳይ የሚመለከተው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልው ለመጥቀስ ይቻላል” ብለዋል።
በጀርመን የፍሪበርግ ሰበካ የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ጉዳይ የሚከታተለው ቢሮ ቃል ኪዳን ስላፈረሱ ስለ ተፋቱ ተፋተው ዳግም ስላገቡት ጉዳይ በተመለከተ ያወጣው ሰነድ አባ ሎምባርዲ ጠቅሰው፣ ኵላዊ መልስ የሚያሻው ጉዳይ የተለየ የመፍትሔ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚሰጠው የተለየ መፍትሔ ሊፈጠረው የሚችለው ግራ አጋቢ ሁኔታ እንዳይኖር ታቅዶ ኩላዊ መልስ የሚሻው ጥያቄ መሠረት ማኅበረ ክርስቲያን በሙሉ ሱታፌ ለመራመድ እንዲችል ለማረግ መሆኑ አብራርተዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በተለያየ ወቅት በመደጋገም ስለ ቤተሰብ ርእሰ ጉዳይ በተመለከተ በተለይ ደግሞ በቤተ ክርስቲያን ይፈታ የሚባል ውሳኔ የሚሰጥበት ጋብቻና ስለ ሚፈጠረው ዳግማዊ ትሥሥር በተመለከተ ሥልጣናዊ ምዕዳን ሰጥተዋል እንደሚታወሰውም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባለፈው መስከረም 16 ቀን 2013 ዓ.ም. ከሮማ ሰበካ ካህናት ጋር ተገናኝተው ቅዱነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በልባቸው የነበረ ብዙዉን ጊዜ የተወያዩበት አበክረው ያሰመሩበት ጉዳይ እንደነበርም በማስታወስ እንዳሉት፦ “ችግሩ የተፋታ ወይንም ዳግም ያገባ ቅዱስ ቍርባን ሊቀበል ይችላል ወይስ አይችልም በሚል ሃሳብ ሥር ብቻ ውይይት ሲደረግበት ይታያል፣ በዚሁ ዙሪያ ሥር ችግሩን የሚመለከት በእውነቱ ችግሩ ምን መሆኑ አልተረዳውም ማለት ነው። በፍችና በዳግም ጋብቻ ሥር የሚኖሩ ቤተሰቦች በተመለከተ ቤተ ክርስትያን አቢይ ኃላፊነት አላት፣ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን የታሰረው ምሥጢረ ተክሊል ዙሪያ ስላለው የይፈታ ውሳኔ በማጤን ስለ ችግር መፍትሔ ልትሰጥበት ይግባል” ካሉ በኋላ ይኽ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የጠሩት ሲኖዶስ ተለየ ሦስተስኛ ጠቅላይ ጉባኤ የመላ ብፁዓን ጳጳሳቲ ዲኖዶስ ሲሆን፣ ቀዳሜው የተለየ ጠቅላይ ጉባኤ የመላ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ እ.ኤ.አ. በ 1969 ዓ.ም. ሁለተኛው ደግሞ እ.ኤ.አ. በ 1985 ዓ.ም. ‘የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤትና የብፁዓን ጳጳሳት ኁባሬአዊነት (collegialità)’ ርእስ ሥር ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ትግባሬ ዙሪያ ሥር የተካሄ ነበር” ብለዋል።
አንድ ሲኖዶስ ተራና ልዩ የሚል መጠሪያ የሚያሰጠው ምክንያት የሲኖዶስ ሥርዓተ ደንብ አንቀጽ አራት ላይ ተመልክቶ እንደሚገኝም አባ ሎምባርዲ ጠቅሰው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በጠሩት ልዩ ሲኖዶስ ፓትሪያርኮች አበይት ሊቀ ጳጳሳት የምስራቅ ካቶሊካውያን አቢያተ ክርስቲያን ሕገ ቀኖና የሚከተሉ ሜትሮፖሊታ የሁሉም አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት አቢያተ ምክር ቤት ሊቀ መናብርት፣ በመላ የገዳማውያም ማኅበራት ጠቅላይ አለቆች ማኅበር ውሳኔ መሠረት የሚላኩ ሦስት የገዳማውያን ካህናት ወኪሎች፣ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የቅርብ ተባባሪ የተለያዩ የቅድስት መንበር ምክር ቤቶች ሊቀ መናብርትና የቅዱሳት ማኅበራት ኅየንተ የሚያሳትፍ መሆኑ አባ ሎምባርዲ ገልጠው የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ እዚህ ላይ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.