2013-10-07 16:11:37

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሦስተኛው ሓውጾተ ኖልዎ በኢጣሊያ አሲዚ ከተማ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ጥቅምት 4 ቀን የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የምታከብረው የቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘ አሲዚ የአገረ የኢጣሊያ ጠባቂ ቅዱስ በዓል ምክንያት በአሲዚ ሓውጾተ ኖልዎ ማካሄዳቸው ሲገለጥ፣ የአርጀንቲና ርእሰ ከተማ ብፁዕ ካርዲናል ቦርጎሊዮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን እንደተመረጡ የዚያ ድኻ ቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘ አሲዚ ስም የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ መለያ ስማቸው በማድረግ ሲመርጡ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ቀዳሜ እንደሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ ይኽ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሓውጾተ ኖልዎ በተለያየ ምክንያትም የመላ ዓለም የመገናኛ ብዙሃን ሊባል ይቻላል፣ በቅርብ ሆነው እንዲከታተሉት ከማድረጉም አልፎ በተለያየ መልኩ ሰፊና ጥልቅ ትንታኔም እንደሰጡበት የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ጋብሪኤላ ቸራዞ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ሲቻል፣ የኢጣሊያ ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ የኢጣሊያ ጠባቂ ቅዱስ ፍራንቸስኮ ዓመታዊ በዓል እንዲሁም በዚያኑ ዕለት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የአሲዚ ጉብኝታቸው ምክንያት በዋዜማው ባስተላለፉት መልእክት፦ “የቅዱስ ፍራንቸስኮ መንፈስ ያስፈልገናል” የሚል ሃሳብ እንዳሰመሩበት የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ቸራዞ አያይዘውም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘ አሲዚ ከተማ ሓውጾተ ኖልዎ የፈጸሙ 19ኛው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይና የቅዱስ ፍራቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ መለያ ስማቸው ያደረጉ ቀዳሜ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ መሆናቸው ሲነገር፣ የሓዋርያዊ ተልእኮአቸው መርሃ ግብርም የመረጡት የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት መለያ ስም እርሱም ቅዱስ ፍራንቸስኮ የሚያንጸባርቅ ሲሆን፣ በአሲዚ ተገኝተው የሰጡት ሥልጣናዊ ምዕዳን፣ ያስደመጡት ሥልጣናዊ ስክበት ያካሄዱዋቸው ግኑኝነቶች በጠቅላላ ለሕዝቦች ተስፋ የሚያሰጥ እምነት የሚያጸናና የሚያነቃቃ ነበር ብለዋል።
የቅዱስ አባታንች ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የአሲዚ ጉብኝት ምክንያት በዕለቱ “ፍራንቸስኮ እንኳን በደህና ተመለስክ” በሚል ርእስ ሥር የኡምብሪያ ክፍለ ሃገር እንዲሁም የኢጣሊያ ዕለታዊ ጋዜጦች በጠቅላላ በቀዳሜ ገጻቸው በማስቀመጥ ሰፊ ትንተና እንደሰጡበት ሲታወቅ፣ የዚህ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የአሲዚው ሓዋርያዊ ጉብኝት የዚያ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የቤተ ክርስቲይን ታሪካዊ ውስጣዊውና ውጫዊው ሂደት የለወጠና ክርስቶስን በመምሰል የኖረው መንፈሳዊና ሰብአዊ ተግባር የሚያንጸባርቅ ሕይወት ለማስተጋባት መሆኑ ጋዜጦች ካሰፈሩት ዘገባ ለመረዳት ይቻላል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. ጥቅምት 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ከአገረ ቫቲካን ከሚገኘው ከሄሊኮፐር ማረፊያ ተነስተው በኢጣሊያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ ሰባት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ አሲዚ በሚገኘው ተቋም ሰራፊኮ አደባባይ እንደደረሱ በተቋሙ የሚደገፉ የተለያየ የሕክምና እንክብካቤ የሚደረግላቸው በተለያየ ከባድ በሽታ በተጠቁት ከመቶ በላይ በሚሆኑ ሕፃናት አቀባበል ተደርጎላቸው የእንኳን ደህና መልእክት ቀርቦ እንዳበቃም በማስከተል ቅዱስነታቸው ባሰሙት ሥልጣናዊ መልእክት፦ “እነዚህ እዚህ የሚገኙት በተለያየ ከባድ በሽታ የተጠቁት ህጻናት በኢየሱስ ስቃይና መከራ ዘንድ እንደምንገኝ ተጨባጭ ትእምርት ናቸው” በማለት ከዚሁ ጋር በማያያዝ የኤማሁስ ደቀ መዛሙርትን ዘክረው፣ ተክዘው ይጋዙ እንደነበርና በዚሁ ትካዜና ሃዘን በተሞላው ጉዞአቸውም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አብሯቸው ይጓዝ ነበር፣ ቅንዋቱ በማሳየትና አብሮአቸው እንጀራ ቆርሶ በመካፈልም ማንነቱን ይገልጥላቸዋል፣ የእነዚህ ሕሙማን ሕጻናት ሁኔታም የጌታችን ኢየሱስ ቅንዋት ህያው ምስክርነት እንደሆነም ገልጠው፣ በማንኛውም በሚሰቃየው አካል አማካኝነት ጌታችን ኢየሱስ ቅንዋቱን ህያው አድርጎታል፣ በእያንዳንዱ በሚሰቃየው አካል፣ የኢየሱስ ስቃይ ይገለጣል፣ የሕጻናቱን ቁስል መፈወስ ማለት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይ መፈወስ ማለት መሆኑ በማብራራት፣ እነዚህን ሕፃናትን የሚንከባከቡትን ሁሉ ጌታ ይባርካችሁ በእያንዳንዳችሁም ዘንድ ጌታ ፍቅሩን ያኑር በማለት በአሲዚ ሐውጾተ ኖልዎ ለማካሄድ የወሰኑበት ምክንያት የሮማ ጳጳስ እንዲሁም የርእሰ ሊቃነ ጳጳስሳት መለያ ስማቸው በማድረግ ለመረጡት የቅዱስ ፍራንቸስኮ ክብር በቅዱስ መቃብሩ ሆነው ለመጸለይ የፍቅር መንፈሳዊ ንግደት ድኾችን በማፍቅር ብቻ ሳይሆን ሃብታም እያለ ድኻ ለመሆን የመረጠው ቅዱስ ፍራንቸስኮ ገዛ እራሱን ከግኡዛዊው ነገር ሁሉ በማላቀቅ ለተናቁት ለተጠሙት ለታመሙት ሁሉ በመምሰል ቅርብ በመሆን የኖረው የእግዚአብሔር ምኅረት በእርሱ ላይ ማረፉ የሚገልጥ የኖረው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አብነት ለማስተጋባት መሆኑ ካሰሙት ሥልጣናዊ ምዕዳን ለመረዳት ይቻላል። የምንኖርበት ዓለምና ሕብረተሰብ ከማስተናገድ ባህል ይልቅ ድኻን የተናቀውን ማግለል የሚል ባህል የሚከተል እንደሚመስልና ስለዚህ የቅዱስ ፍራንቸስኮ ታሪክ ማፍቀር ማስተናገድ ባህል በቃልና በተግባር የሚያስተጋባ መሆኑ እንዳመለከቱም የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ቸራዞ ካጠናቀሩት ዘገማ ለመረዳት ይቻላል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በመቀጠልም በኢጣሊያ ሰዓት አቆጣጠር ልክ ከጠዋቱ ዘጠኝ ሰዓት ተኩል በአሲዚ ጳጳሳዊ መንበር በከልሉ ሰበካ በሚገኘው የቅድስት መንበር በካሪታስ የሚጠራው የእርዳታ ማኅበር ቅርንጫፍ አማካኝነት ከሚረዱት ጋር በመገናኘት እዚያ ከእኛ ቢጠዎች ጋር በመገናኘት የአሲዚ ጳጳስ ካቀረቡላቸው የእንኳን ደህና መጡ መልእክት በመቀጠል የእሳቸው በዚያ ቅዱስ ፍራንቸስኮ ኢየሱስን መቀበሉና ከእርሱ ጋር መገናኘቱ እርሱን ለማገልገል መጠራቱ ለአባቱ በማሳወቅ ልብሱን በማውለቅ እርቃኑ የወጣበት እርቃን ተብሎ የሚጥራው ሥፍራ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሲጎበኝ ከ 800 ዓመታት በኋላ የተከናወነ መሆኑ የአሲዚ ጳጳስ ያሰመሩበት ሃሳብ በማሰብ፣ ያንን ቅዱስ ሥፍራ ነቢያዊ ሥፍራ የሙሉ ፍቅርና የጸሎት እዲሁም የሙሉ ድኽነት ተግባር ትእምርት ነው በማለት ቅዱስ ጳውሎስ ለፊልጵሲዩስ ሰዎች በጻፈው መልእክት ምዕ. 2 ከቍጥር 6 እስከ 8 ያለው፦ “…እራሱን ባዶ አደረገ…” በማለት የገለጠው ኢየሱስ የሆነውን ለመሆን በተግባር የገለጠበት ሥፍራ ነው ካሉ በኋላ ሁሉም ማኅበረ ክርስቲያን የውሉደ ክህነት አባላት ካህናት ደናግል ሁላችን ሙሉ በሙሉ ክርስቶስን ለመምሰል በክርስቶስ እንማረክም ዘንድ አደራ ብለው፣ እራቁታችን ወጥተን እውነተኛው ልብሳችን የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስን ልንለብስ ይገባናል ይኽ ተግባር ደግሞ ከፍቅር የሚመነጭ መሆኑ ማብራራታቸው ቸራዞ ገልጠው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቅዱስ ፍራንቸስኮ የመረጠው ድኽነት ፖለቲካዊ ርእዮተ ዓለማዊ ሥነ ሓሳባዊ ምርጫ የተከተለ ሳይሆን ከኢየሱስ ጋር ከመገናኘትና እርሱን ለመምሰል ከሚለው ከኢየሱስ ጋር ከሚጸናው እውነትኛው ህይወትን ከሚለውጥ ግኑኝነት የመነጨ መሆኑ ማስረዳታቸው ገልጠው፣ በማስከተልም ወደ ታላቅዋ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሳንታ ማሪያ ማጆረ በመሄድ የግል የጽሞና ጽሎት አሳርገው፣ ልክ ከጠዋቱ 11 ሰዓት በቅዱስ ፍራንቸስኮ ባሲሊካ ፊት ባለው አደባባይ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ባሰሙት ስብከት የዕለቱ ወንጌላዊ ምንባብ እርሱም ማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 11 ቍ. 25 “…አባት ሆይ የሰማይና የምድር ጌታ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመስግንሃለሁ…” የተሰኘውን ቃል ጠቅሰው፥ “ቅዱስ ፍራንቸስኮ ያቀረበው በነበረው ሰላም ወ ሰናይ ይሚሉትን ቃላት በመጠቀም በዚህ በእምነትና በጸሎት ታሪክ ታላቅ ሥፍራ ያለው ቅዱስ ሥፍራ ከእኔ ጋር በመገኘታቸችሁ አመስግናችኋለሁ፣ እንደ ማንኛውም መንፍሳዊ ነጋዲ እዚህ ተገኝቼ ጌታ ለታናናሽ ሕፃናት በገለጠው ሁሉም ከእናንተ ጋር አብሬ እስግድለታለሁ” ካሉ በኋላ ቅዱስ ፍራንቸስኮ ከአንድ ሃብታም ነጋዴ አባት የተወለደ ሆኖ እያለ ከኢየሱስ ጋር መገናኘት ከዚያ ከተናወጠችው ግድ ከማትለው እንዳሻኝ ከምትለው ሕይወት ገዛ እራሱን በማግለል እመቢየት ድኽነትን ለመዳር እንዳበቃና እንደ አንድ የዚያ የሰማይ አባት ልጅ ሆኖ ለመኖር ያበቃው ምርጫ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ተንትነው፣ በአሁኑ ወቅት ቅዱስ ፍራንቸስኮ ታሪክ ሆኖ የሚነገር በቃላት ብቻ የሚገለጥ ሳይሆን ዛሬ ለእኛ ምን ይለናል ለእኔ ምን ይለኛል እንድንልና ክርስቲያን መሆን ማለት ከኢየሱስ ህያው አካል ጋር ህያው ግኑኝነት መኖር ማለት መሆኑ ነው የሚመሰክርልን። ስለዚህ፦ “ክርስቶስ መምሰል ማለት መሆኑ ገልጠው” ቀጥለውም ማቴ. ምዕ. 11 ከቁጥር 28 እስከ 29 ያለውን ጠቅሰው፦ “እናንተ ደካሞች ሸኽማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ እኔ የዋህ በልቤም ትሁት ነኛ ለነፋሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና” ቅዱስ ፍራንቸስኮ በሁለተኛው ደረጃ በህይወቱ የመሰከረው እውነት መሆኑ ተንትነው የዕለቱን መዝሙር፦ የልዑላን ልዑል ከሃሌ ኵሉ መልካም ጌታ ከሁሉም በሁሉም ፍጥረት እምትወደስ” የሚለው ቃል ደግመው፣ ቅዱስ ፍራንቸስኮ ከሁሉም ፍጥረት ጋር በመሆን እግዚአብሔርን በገዛ እራሱ ድንቅ ሥራ አማካኝነት ምስጋናና መዝሙር የማቅረብ መንፈሳዊው ልማዱ እንደነበር የገለጡት ቅዱስ አባታችን፣ ዓለም በሰላምና በመግባባት በስምምነት እንዲኖር ጸልየው በዚህ አጋጣሚም በሶሪያና በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ሁከትና ውጥረት ተወግዶ ሰላም እንዲወርድ በቅዱስ ፍራንቸስኮ አማላጅነት ተማጥነው፣ ጌታ ምህረት እንጂ ኩነኔ እንዳልሆነ፣ ጸጋውን ማመንስገን እንጂ የማያመሰግን ተግባር ማቅረብ አይደለም፣ ዘወትር ምህረቱን እንድናይ በአሲዚ የገለጠው ፍቅሩና ምሕረቱ ዳግም እንድናይ ጸልየው፣ ስምህ ለዘለዓለም እስከ ዘለአለም የተባረከ ይሁን እሜን በማለት ባቅረቡት ጸሎት ያስደመጡት ሥልጣናዊ ስብከት እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ቸራዞ አስታወቁ።
ቅዳሴው እንዳበቃም በቅዱስ ፍራንቸስኮ ባዚሊካ በመግባት የቅዱስ ፍራንቸስኮ ቅዱስ አጽም ባረፈበት ቅዱስ ሥፍራ ጸሎት አሳርገው በየዓመቱ ቅዱስ ፍራንቸስኮ የኢጣሊያ ጠባቂ ቅዱስ ዓመታዊ በዓል ምክንያት ብሔራዊ ቃል ኪዳን ለማደስ የሚበራው የኩራዝ መብራት አብርተው በቅድስት ማርያም ዘ መላእክት ተብሎ በሚጠራው በአሲዚ የባቡር ጣቢያ ክልል ወደ ሚገኘው የቤተ ክርስቲያን የእርዳታ ማኅበር አማካኝነት የሚረዱት ወደ ሚመገቡበት ማእድ ቤት በመግባት እዛው ከእኛ ቢጠዎች ጋር ሆነው ለእነርሱ የሚቀረበው ምሳ ተቋድሰው ልክ ከቅትር በኋል 2 ሰዓት ተኩል ቅዱስ ፍራንቸስኮ እና ወንድሞቹ አብረው ጸሎት ያሰርጉበት ወደ ነበረው ዋሻ መንፈሳዊ ንግደት ፈጽመው ወደ ቅዱስ ሩፊኖ ካቴድራል በመሄድ እዛው ከተገኘት ከሁሉም ውሉደ ክህነት አባላት ካህናት ደናግል ጋር ተገናኝተው ስለ ተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው፣ ጸጋ ምሥጢረ ጥምቀት የሚያስታውስ የእግዚአብሔር ሕዝቦች የሚያሰኘውን ትርጉም ያለው መህኑ የሚገልጥ ሥልጣናዊ ምዕዳን ለግሰው ሁላችን በተወሃደ መልካም ሱታፌ አማካኝነት የቤተ ክርስቲያን ልጆች መሆናችንና ቃሉን በጥልቅ ጽሞና በማዳመጥ አብረን ለመጓዝ የተጠራን ለመሆናችን ምስክርነት ነው በማለት፣ ስለዚህ ይኽንን የሚኖር ቃል ለማበሰር የተጠሩ መሆናቸው አሳስበው፣ በተለይ ደግሞ ሩቅ ከከተሞቻችን ውጭ የተናቁት የተገለሉት የተረሱት ወደ ሚኖሩበት በመሄድ ከእነርሱ ጋር በመሆን ለእነርሱ ሕያው እግዚአብሔር እንዲያበስሩ አደራ ብለው፣ በመጨረሻም መንታ ከቅዱስ ፍራንቸስኮ ወንድሞች ማኅበር ጋር የተመሠረቱት የቅዱስት ኪያራ መናንያን የደናግል ማህበር ቤት በመሄድ እዛው በቅዱስት ኪያራ ባዚሊካ የሚገኘው በቅዱስት ኪያራ ቅዱስ አጽም ባረፈበት ቅዱስ ሥፍራ ጸሎት አሳርገው፣ ከመናንያኑ የቅዱስት ኪያራ ደናግል ማኅበር ጋር ተገናኝተው የቀረበው የምስጋና መልእክት አዳምጠው እንዳበቁ ባስደመጡት ሥልጣናዊ ምዕዳን ለግሰው በመቀጠል ወደ ቅድስት ማርያም ዘመላእክት ባሲሊካ በመሄድ ከክልሉ ወጣቶች ጋር ተገናኝተው ከወጣቶች የቀረበላቸው ጥያቄ በማዳመጥ መልስ ሰጥተው፣ ወርቅ ብር ወይንም ሃብት የለንም ልሰጠው የተጠራነው ያለንን እምነት ነው። በማለት በሕይወታችን የእምነት ማእከልነት አስገንዝበው ከክርስቶስ ጋር በገናኘትና የተገናኘነው ክርስቶስ ማቅረብ ብቻ ሙሉ ደስታ መሆኑ ገልጠው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ከክልሉ ሕዝብ ተስናብተው በሄሊኮፕተር ልክ ከምሽቱ 7 ሰዓት ከ 15 ደቂቃ ተነስተው ሃገረ ቫቲካን ከምሽቱ 8 ሰዓት እንደደረሱም የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ቸራዞ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.