2013-10-04 16:00:36

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መማክርት ብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከተሾሙ በኋላ ግልጽ ያደረጉት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ተባባሪዎች አበይት የቅድስት መንበር ሓዋርያዊ መስተዳድር መዋቅር ለማደስ ያላቸው ፍላጎት መሠረት በማድረግ በዚሁ እቅድ የሚተባበሩዋቸው በስምንት ካርዲናሎች የቆመ የመማክርት አካላት መመልመላቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የመዋቅሩ ህዳሴ ለማስጀመር የመለመሉት መማክርት ብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ በአገረ ቫቲካን እ.ኤ.አ. ከጥቅምት አንድ ቀን እስነ ጥምቅት ሶስት ቀን 2013 ዓ.ም. ቅድስት ማርታ ሕንጻ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በግል ቤተ ንባብ ስብሰባ ማካሄዱ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ጉዳይ ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ገልጠው፦ “ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባኖሩት አቢይ ፍላጎትና ውሳኔ መሠረት የተጀመረው የቤተ ክርስቲያን ማለትም የቅድስት መንበር የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ተባባሪ የበላይ ሐዋርያዊ መስተዳድር ኅዳሴ ተራ ወቅታዊነት ማላበስ የሚል የአደረጃጀት ሂደት የሚመለከት ሳይሆን የበላይ ሐዋራያዊ መስተዳድር የሚመራበት የቅድስት መንበር ‘Pastor bonus-መልካም እረኛ’ የተሰየመው መዋቅር ላይ ያነጣጠረ ይኸም ቲዮሎጊያዊ ሥነ ቤተ ክርስቲያን ሥነ መንፈሳዊ ቲዮሎጊያ እንዲሁም ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ውሳኔዎች ገቢራዊነቱ ሙሉ ለማድረግ ላይ ያነጣጠረ እቅድ የሚከተል ነው። ስለዚህ አንድ አዲስ የቅድስት መንበር ሕገ ሐዋርያዊ እንዲሚኖር ነው፣ ከዚህ አንጻር ሲታይ ኅዳሴው ሙሉ በሙሉ ለማረጋገጥ በቂ ጊዜ ይጠይቃል” ካሉ በኋላ ማገልገል አገልግሎት ከሚለው የቤተ ክርስቲያን ባህርያዊ ጥሪ ጋር የተጣመረ ኅዳሴና ስለ ኵላዊት ቤተ ክርስቲያንና ክክላዊቷ ቤተ ክርስቲያን ማእከልነት ላይ የጸና ትሥሥር ሳይሆን መደጋገፍ የሚል መሆኑ አብራርተው ለምሳሌ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ የሚለው የቅዱስ አባታችን ዋና ጸሓፊ በሚል ተልእኮ ላይ የሚገለጥ መሆኑም አብራርተው፦ “የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ላይ ያተኮረው ሕዳሴ ሁሉም እንደሚያውቀው ቅዱስነታቸው አዲስ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ሹመዋል ስለዚህ የአዱስ የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ይፋዊ አገልግሎቱ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 15 ቀን 2013 ዓ.ም. የሚጀመር በመሆኑም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ሚናና አገልግሎት ተግባር አዲሱ ዋና ጸሐፊ ተልእኮአቸው ከመጀመራቸው በፊት ግልጽ ሆኖ እንዲቀርብ የሚሹ በመሆናቸው የተካሄደው ስብሰባ በዚሁ ጉዳይ ላይ አበክሮ ተወያይተዋል” ብለዋል።
በመጨረሻም የተካሂደው ስበሰባ አንድ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቅርብ ተባባሪ የበላይ ሐዋርያዊ መስተዳድር የሚያስተባብር እርሱም አቀናጅ ክፍል እንዲኖር የሚል በተለያዩ በቅድስት መንበር የበላይ ሐዋርያዊ መስተዳድር የዓለማውያን ምእመናን ተሳትፎ ለማጠናከርና በመጨረሻም አንድ አዲስ የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ሊካሄድ በእቅድ መያዙንም አባ ሎምባርዲ ገልጠው ከዚሁ ጋር በማያያዝ የዚህ የመማክርት ብፁዓን ካርዲናሎች ቀጣይ ስብሰባ እ.ኤ.አ. በ 2014 ዓ.ም. በጥር ወይንም በየካቲት ወር ሊካሄድ እንደሚችል ነው በማለት የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ እዚህ ላይ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.