2013-10-02 16:15:42

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ አገልግሎታችን ውብ የቤተ ክርስቲያን ምስክርነት ለማቅርብ እንድንችል ትሁታን የሚያደርገን ይሁን


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ጥቅምት 1 ቀን 2013 ዓ.ም. እንደተለመደው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ካማካሪዎቻቸው ብፁዓን ካርዲናላት ማለትም “የካርዲናላት ምክር ቤት አባላት ”ጋር በመሆን በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ እ.ኤ.አ. እስከ ጥቅምት 3 ቀን 2013 ዓ.ም. የሚከናወነው ጥቅምት 1 ቀን 2013 ዓ.ም. የተጀመረው ጉባኤ በማሰብ ባሰሙት ስብከት፦ “ጉባኤው፣ መላ ተጋባእያኑን የተዋበ የቤተ ክርስቲያን ምስክርነት ለማቅረብ ይችሉ ዘንድ ትሁታንና እማኔያቸውንም በእግዚአብሔር ማኖር ወሳኝ ነው የሚል ነው” በማለት፣ “የክርስትስናው መንገድ የብቀላ ሳይሆን የትህትናና የምህረት መንገድ ነው” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አያይዘው ቅዱስ አባታችን ዕለቱ የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ተረዛ ዘ ሕፃነ ኢየሱስ ዓመታዊ በዓል እንደምታከብር በማስታወስ “እግዚአብሔር ከእኛ የሚፈልገው የምህረት መንፈስ እንዲኖረን ነው። የዕለቱ በዓል ትህትና የዋህነትና መልካም ፈቃደኛነት የተሰኙት ወንጌላውያን እሴቶች እንድናስተነትን ያደርገናል” ካሉ በኋላ፦ “ሌላው የሚሠዋ ፍቅር እርሱም ካለው ሳይሆን የሆነው ሁሉ የሚሰጥ ሁለ መናነትን የሚጠይቅ ፍቅር ሁሉም የሚምር የማይታበይ፣ ትሁት ገዛ እራስ ከመሻት የተላቀቀ ፍቅር የሚል ነው። በርግጥ አንዳንዶቻችን ይኽ የተባለው ጉዳይ አንዳንድ ፈላስፋዎች ያሉት ሃሳብ ነው ለማለት እንችላለን፣ አርግጥ ነው አስበዉት ሊሆን ይችላል ነገር ግን የሰው ልጅ ታላቅነት ለማረጋገጥ ያለመ ነው። ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ተረዛ ዘ ሕፃነት ኢየሱስ፣ ትህትና ታናሽነት ዝቅ ብሎ የመጨረሻነትን በመኖር እማኔዋ በእግዚአብሔር ያኖረች ነች በማለት ቅድስናዋ በማወጅ የተልእኮ ወንጌል ጠባቂ በማድረግም ሰይማታለች፣ አዎ የወንጌል ኃይል ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትህትና ድኽነት የተናቀ ካደረገው ትህትና የሚመነጭ ነው። ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ‘ቤተ ክርስቲያን የምታድገው ሌላውን የሚከተለው ሃይማኖት ትቶ እርሷ የምታቀርበው እምነት እንዲቀበል በማድረግ ሳይሆን፣ በማራኪነቷ እርሱም ሌላውን በመማረክና በምስክርነትዋ ነው የምታድገው’ ይኽ ነው ቤተ ክርስቲያንን ታላቅ የሚያደርጋት። ሕዝቦች የቤተ ክርስቲያንን ትህትና የዋህነት ምሕረት መልካምነት ሲመለከቱ ነቢይ ዘካሪያስ የሚለው እርሱም ‘ከእናንተ ጋር ለመሆን እንሻለን’ የሚለው ቃል የራሳቸው በማድረግ ይደግሙታል። ቤተ ክርስቲያን በምትሰጠው ትሁት ልዋጭ የማይጠይቅ ልዕልና በማያሰማው ርእሰ በቂነት ያማይኖር ማገልገልን የሚወድ የሚሠዋ ፍቅር ምስክርነት የሚያይ ሕዝብ ‘ከእናንተ ጋር ለመሆን እንሻለን እንደሚሉ የተረጋገጥ ነው” እንዳሉ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ካስተላለፉት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከአማካሪያን ብፁዓን ካርዲናላት ጋር በዚያኑ ዕለት የሚያካሂዱት ጉባኤ በማሰብም አብሮአቸው በቅዳሴው የሚሳተፉት የዚህ ምክር ቤት አባላት ብፁዓን ካርዲናላት ሁሉ፦ “ከዚህች ሰዓትና ቀን ጀምሮ የምንፈጽመው ትሁታን መሃሪያን ታጋሾች እማኔአችን በእግዚአቤር በማኖር የምናድግ በእርሱ የምንታመን እንድንሆን ያድርገን፣ በዚህ መንገድ ብቻ ነው ቤተ ክርስቲያን ለሕዝቦች ውብ ምስክርነት ለመስጠት የምትችለው። አሕዛብ የእግዚአብሔር ሕዝብ፣ ቤተ ክርስቲያንን በማየትም ከእኛ ጋር ለመሄድ ከእኛ ጋር ለመሆን ይሻሉ” በማለት ያሰሙት ሥልጣናዊ ስብከት እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.