2013-09-27 16:01:23

የእምነት ዓመት፦ ዓለም አቀፍ የትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎች ዓውደ ጥናት


RealAudioMP3 በዚህ በእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስቲያን እየተከበረ ባለው የእምነት ዓመት ምክንያት የዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ምክር ቤት የተለያዩ መርሃ ግብሮች የማረጋገጥ ሂደቱን በመቀጠል እ.ኤ.አ. ከ መስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም. 1,600 ተጋባእያን በማሳተፍ በአገረ ቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ የተጀመረው ዓለም አቀፍ የትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎች ዓውደ ጥናት መስከረም 29 ቀን 2013 ዓ.ም. የሚጠናቀቅ መሆኑ ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ ይኸንን ዓለም አቀፍ ጉባኤ በንግግር የከፈቱት አዲስ አስፍሆተ ወንጌል የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ኦክታቪዮ ሩዊዝ እረናስ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ይኽ ጳጳሳዊ ምክር ቤት እንዲቋቋም የወሰኑት ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የምክር ቤቱ አንዱ አላማ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ መከተልና ማነቃቃት ብሎም በጥልቀት ለሙሉ ግንዛቤ በተለያዩ ሰበካዎች አስተምህሮ እንዲሰጥበት የሚል እንዲሆን ማሳሰባቸው አስታውሰው፣ ስለዚህ በእምነት ዓመት ይኸንን ጉዳይ ማእከል ያደረገ የዓውደ ጥናት መርሃ ግብር እንዲከናወን ቀደም በማድረግ ያመለከቱት ስልጣናዊ ምዕዳን የተከተለ ነው ብለዋል።
በመካሄድ ላይ ያለው ዓውደ ጥናት በቅድሚያ የድህነት ምስጢር፣ ስለ መዳን ጌታችን የለገሰው እውነትና የእኛ መልስ በሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ ያተኮረ ሰፊ ውይይትና አስተምህሮ የሚቀርብበት ነው፣ ስለዚህ የሰውን ልጅ ለመፈለገ የሚወርደው ማደሪያውን በእኛ መካከል ስለአኖረው እግዚአብሔር ይኽም ሰውን በመፈለግ ዓለማ ተከትሎ የሚመጣው ምስጢረ ትስብእት በጥልቀት የሚያስተነትን ነው። ሁሉም ሰብአዊ ፍጡር ይኸንን የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ጸጋ እንዲቀበልም ቤተ ክርስቲያን ይኸንን የማዳን እቅድ ታበስራለች፣ ተልእኮዋ የማዳን እቅድ ማወጅና ማብሰር ነው ብለዋል።
በዚህ እምነት በማስፋፋቱ ተልእኮ ከብፁዓን ጳጳሳት ጋር ተባባሪዎች እንዲሆኑ ከሚጠሩት ካህናት ጎን ሆነው የሚያገለግሉ የትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎች እንዲኖሩ ቅዱስ መጽሐፍ ላይ የጸና የቤተ ክርስቲያን ውሳኔ ነው። ይኽ ጥሪ በመጽሓፍ ቅዱስ በቤተ ክርስቲያን ትውፊትና በቤተ ክርስቲያን አበው የሚረጋግጥም ነው። እምነት በትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎች ታቅቦ በብዙ የዓለማችን ክልል መበሰሩ የቤተ ክርስቲያን የታሪክ ማኅደር የሚመሰክረው እውነት ነው።
ትምህርተ ክርስቶስ ካለው ዓላማ መሠረት የትምህርተ ክርስቶስ አስፈላጊነቱ እንገነዘባለን፣ ስለዚህ በዚህ ጥሪ በቤተ ክርስቲያን ተልእኮ የሚሳተፍ የቤተ ክርስቲያን አባል ልክ ካህነት ለመሆን የሚጠይቀው የማዘጋጃ ሕንጸት ማግኘት ይኖርበታል፣ ምክንያቱም በቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ የአብሳሪነት ተልእኮ ተካፋይ ነውና። ለሌው ሰው የቤተ ክርስቲያን አባል እንዲሆን የሚያስተምረው የትምህረተ ክርስቶስ አስተማሪ የቤተ ክርስቲያን አባልነቱ ምንኛ ጥልቅን ጥብቅ መሆን እንደሚገባው ለመገንዘብ አያዳግትም፣ ይኸንን ሁሉ እግምት ውስጥ በማስገባት ይኸ የገለጡት ሃሳብ በተለያየ መልኩ በመጽሓፍ ቅዱስ በቤተ ክርስቲያን በቲዮሎጊያና በቤተ ክርስቲያን ትውፊት ታሪክ የሚተነተንበት ነው ሲሉ የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠናቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.