2013-09-25 18:43:04

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ፣


ውድ ወንድሞችና እኅቶች! ደኅና አደራችሁን! ጸሎተ ሃይማኖት በምንደግምበት ጊዜ “አንድ በሆነችው ቤተ ክርስትያን አምናለሁ” በማለት ቤተ ክርስትያን አንድ መሆንዋና ይህችም ቤተ ክርስትያን በገዛ ራስዋ የተዋኃኃደች መሆንዋን እንመሰክራለን፣ ነገር ግን በመላው ዓለም ያለችውን ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የተመለከትን እንደሆነ ከ3.000 በላይ የሚሆኑ ሃገረ ስብከቶች በተለያዩ ክፍለ ዓለማት ብዙ ቋንቋዎችና ብዙ ባህሎች እንዳሉ እናያለን፣ እዚህ ሮም ውስጥ ከተለያዩ አገሮች የተለያዩ ባህሎች ያልዋቸው ብዙ አቡናት አሎ፣ የስሪላንካ ጳጳስ የደቡብ አፍሪቃ ጳጳስ እንዲሁም የህንድ ጳጳስ ባጠቃላይ ብዙ ጳጳሳት ከደቡብ አመሪካም አሉ፣ ቤተ ክርስትያን በመላው ዓለም ተዘርግታ ትገኛለች፣ ይህ እንዲህ ሳለ እነኚህ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ካቶሊካዋን አንድ ቤተ ክርስትያን ናቸው፣ ይህ እንዴት ይሆናል ብለን የጠየቅን እንደሆነ፤
አንደኛ አጠቃላይ የሆነ መልስ በአዲሱ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ በመላው ዓለም ተዘርግታ የምትገኝ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን “አንድ እምነት አንድ ብቻ የሆነ የቅዱሳት ምሥጢራት ሕይወት አንድ የኅብረት ተስፋና አንድ ፍቅር አላት” ይላል፣ አቅጣጫ የሚያስይዘን ጥርት ያለ ቆንጆ አገላለጽ ነው፣ በእምነት በተስፋና በፍቅር አንድ መሆን እንዲሁም በቅዱሳት ምስጢራትና በሐዋርያዊ ግብረ ተል እኮ አንድ መሆን፤ የሚሉ አንቀጾች ታላቁን የቤተ ክርስትያን ግንብ አጽንተው በአንድነት የሚያቆሙ ምሶሶዎች ናቸው፣ በሄድነበት ቦታ ማንም በቀላል ሊደርስበት በማይችልበት በዓለማችን ጥግ ተወስና በምትገኝ ታናሽዋ ቍምስናም ይሁን የሄደን እንደሆነ እዛ ላይም ይህች አንዲት ቤተ ክርስትያን አለች፤ በገዛ ቤታችን አለን፤ ከቤተ ሰቦቻችን ጋር ከወንድሞቻችንና ከእኅቶቻችን ጋር አለን ማለት ነው፣ ይህም ታላቅ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው! ቤተ ክርስትያን ለሁላችን አንድ ብቻ ናት! ለኤውሮጳውያን አንድ ለአፍሪቃውያን ሌላ ለአመሪካውያን አንድ ለኤስያውን ሌላ የሚል ሓሳብ ከቶ ቦታ የለውም፣ በሄድንበት አንዲት ቤተ ክርስትያን ብቻ ናት፣ እንደ አንድ ቤተ ሰብ አንዳንዴ ተራርቆ በመላው ዓለም ሊዘረጋ እንደሚቻል ሆኖም ግን የቤተ ሰቡን አባላሎች አንድ የሚያደርግ ጥልቅ የቤተ ሰብ መተሳሰር ሁሌ እንዳለ ነው፣ ለምሳሌ በዓለም አቀፉ የወጣቶች ቀን በሪዮ ዲ ጃነሮ የሆነውን መለስ ብየ ሳስብ ወሰን በሌለው የኮፓቻካባና ባህር ጠረፍ ላይ አጥልቅልቆ በነበረበት ጊዜ እዛ ላይ ብዙ ቋንቋዎች ይሰሙ ነበር ብዙ የተለያዩ ፊቶችም ይታዩ ነበር የተለያዩ ባህሎችም ይገናኙ ነበር ነገር ግን ጥልቅ የሆነ አንድነት ይታይ ነበር አንዲት የሆነች ቤተ ክርስትያን ትታይ ነበር፣ አንድ ሆነን ነበር ይህንም አንድነት ሁላችን እናየውና እንሰማው ነበር፣ እስቲ ወደ ገዛ ራሳችን መለስ ብለን “እኔ ካቶሊክ እንደመሆኔ መጠን ይህን አንድነት ይሰማኛልን? ካቶሊክ እንደመሆኔ መጠን ይህንን የቤተ ክርስትያን አንድነት እኖረዋለሁን? ወይንስ በታናሽ ቡድን ወይንም በገዛ ራሴ ተዘግቼ ስላለሁ አያገባኝም እላለሁ? ወይንስ አንዳንዶቹ እንደሚያደርጉት ቤተ ክርስትያንን ለገዛ ጉድናቸው ለአገራቸው ብቻ ወይንም ለጓደኞቻቸው ብቻ የግላቸው እንደሚያደርጉት አደርጋለሁ? አንዲት ለግል ጥቅም ብቻ የተወሰነች ቤተ ክርስትያን እጅግ ታሳዝናለች! ይህም የእምነት መጕደል ነው! አሳዛኝ ነው! አንዳንዴ በዓለማችን ብዙ ክርስትያን እየተሰቃዩ ናቸው! ሌሎች ብዙ ክርስትያኖች ደግሞ ደንታ የላቸውም ሲሉ በምሰማበት ጊዜ እጅግ አዝናለሁ፤ ከቤተ ሰብ አባሎች አንዱ እንደሚሰቃይ ሆኖ ይሰማኛል፣ እንዲሁም ብዙ ክርስትያኖች እየተሰደዱ ናቸው ለእምነታቸው ሲሉም ሕይወታቸውን መሥዋዕት እየከፈሉ ናቸው ሲሉ በምሰማበት ጊዜ ወይንም ስለዚህ በማስብበት ጊዜ ልቤ ይቆስላል፣ እስቲ እናስተንትን “ለእነዚሁ የቤተ ሰባችን አባሎች የሆኑ ሕይወታቸውን ለክርስቶስ አሳልፈው ለሚሰጡ ለዚህ ወንድም ወይም ለዚህች እኅት ልባችን ክፍት ነው ወይ? አንዱ ለሌላው እንጸልያለን ወይ? አንዲት ጥያቄ ላቅርብላችሁ እወዳለሁ፤ ድምጻችሁን ከፍ አድርጋችሁ አትመልሱ በልባችሁ ውስጥ ብቻ መልሱት፤ ስለሚሰደዱ ክርስትያን የሚጸልዩ ስንቶቻችሁ ናችሁ? ስንት? እያንዳንዳችሁ በልባችሁ መልሱ፣ እምነቱን ለመመስከርና ለመከላከል ስለሚሰቃየው ወንድሜ ስለምትሳቀየው እኅቴ እጸልያለሁን? ከግዛ አከባቢያችን ወጣ ብሎ መመልከትና ቤተ ክርስትያንን እንደ አንድ የእግዚብሔር ቤተሰብ አድርጎ ማየት ያስፈልጋል፣
2. ሌላ እርምጃ ወደፊት እናድርግና እንዲህ ብለን እንጠይቅ፤ በዚሁ የቤተ ክርስትያን አንድነት ቍስሎች አሉ ወይ? እኛስ ይህንን የቤተ ክርስትያን አንድነት ለማቍሰል እንችላለንን? እንደእውነቱ ከሆነ በቤተ ክርስትያን ታሪክ ጉዞ አሁንም ቢሆን ይህንን አንድነት በሚገባ አንኖረውም፣ አንዳንዴ አለመግባባት ግንጭቶች ውጥረቶች እና መከፋፈል ብቅ ይላሉ፤ እነኚህ ደግሞ ቤተ ክርስትያንን ያቆስላሉ፣ ስለዚህ ቤተ ክርስትያን የምንፈልገውን ገጽታ አታሳየንም እግዚአብሔር የሚፈልገውን መፈቃቀርን አታሳይም፣ አቍሳዮቹ እኛ ነን! በክርስትያኖች መካከል ያሉ መከፋፈሎችን ማለት ካቶሊኮች ኦርቶዶክሶች ፕሮተስታንቶች የተመለከትን እንደሆነ ያ ጌታ የተመኘውን አንድነት በተግባር ላይ ለመዋል ስንት ድካም እንደሚያስፈልግ እንረዳለን፣ እግዚአብሔር አንድነትን ይሰጠናል እኛ ግን እተግባር ላይ ልናውለው እንቸገራለን፣ ስለዚህ ውህንደትን ለመገንባትና አንድነትን ለመፈለግ ከሁሉ አስቀድሞ ለአንድነት ማነቃቃት ማስተማር አለመግባባትንና መከፋፈል ከቤተ ሰብ ጀምሮ እስከ ቤተ ክርስትያን ለማስወገድ እና ንጹሕ የአብያተ ክርስትያን አንድነት ውይይት መጀመር ያስፈልጋል፣ ዓለማችን አንድነት ያስፈልገዋል፣ ዘመናችን ሁላችን የአንድነት የዕርቅ እና የውህደት አስፈላጊነት ያለው ዘመን ነው፣ ቤተ ክርስትያንም የውህደት ቤት ናት፣ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ኤፌውሶን ክርስትያኖች ሲጽፍ “እንግዲህ በጌታ እስር የሆንሁ እኔ በተጠራችሁበት መጠራታችሁ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤ በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም፤ እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ፤ በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።” (4፡1-3) ብሎ ይማጠናል፣ ትሕትና ጥዑመ ልሳን መሆን ታላቅ ልብ መኖርና ፍቅር አንድነትን ይጠብቃሉ፣ እነኚህ እውነተኛ የቤተ ክርስትያን መንገዶች ናቸው፣ እስቲ ልድገማላችሁ ትዕቢት እና እኔነትን የምናሸንፍባቸው ትሕትና ጥዑመ ልሳን መሆን ታላቅ ልብ መኖርና ፍቅር አንድነትን ይጠብቃሉ፣
ቅዱስ ጳውሎስ አያያዞ ለኤፍውሶን ክርስትያኖች “በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤ ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ።” (4፡4-6) ይላል፣ አንድ የሚያደርጉን ስንት ነገሮች እንዳሉ ያመለክታል፣ ይህ እውነተኛ ሃብት ነው፣ ሁሉም አንድ የሚያደርግ እንጂ የሚለያይ የለም፣ ይህም የቤተ ክርስትያን ሃብት ነው፣ እያንዳንዳችን ወደ ኅልናችን መለስ ብለን የቤተ ሰብ አንድነትን አሳድጋለሁን የቍስምናስ የምኖርበት ማኅበረሰብስ ወይንስ አለ ምንም ቍምነገር ለፍላፊ ብቻ በመሆን የመለያየትና የአሳዛኝ ሁኔታ ምክንያት ሆኜ ቀርቼአለሁ? ብለን እንመርምር፣ እውነቱን ልንገራችሁ ለፍላፊ መሆንና ስም ማጥፋት በቤተ ክርስትያን በቍምስና በማኅበረሰብ ላይ የሚያደርሱት ጉዳት የምታውቁት አይመለኝም፣ የማይረቡ ንግግሮች ያቆስላሉ፣ አንድ ክርስትያን ሰው ከማማትና ስም ከማጥፋት እንዲሁም የማይጨበጥ ነገር ከመለፍለፉ በፊት ምላሱን መንከስ አልበት፤ ይህ መድኃኒት ሊሆነን ይችላል፣ እንዲህ በማድረጋችን ምላሳችን እንዲያብጥ እናደርገዋለን ስለዚህ ሊያማ ሊለፈልፍ አይችልም፣ ሌላው የኅልና ምርመራ ደግሞ ለአንድነቱ ያደርስክዋቸውን መቍሰልቶች በት ዕግሥትና በመሥዋዕትነት ለመፈወስ በቂ ትሕትና አለኝ ወይ ብለን ራሳችን እንጠይቅ፣
3. በመጨረሻም ጠለቅ ያለ እርምጃ ለመውሰድ ቆንጆ የሆነች ጥያቄ ላቅርብላችሁ፤ የቤተ ክርስትያን አንድነት አንቀሳቃሽ ማን ነው? እኛ ሁላችን በምስጢረ ጥምቀትና በምስጢረ ሜሮን የተቀበልነው መንፈስ ቅዱስ ነው፣ ስለዚህ መጠንቀቅ ያለብን አንድነታችን ከሁሉ አስቀድሞ የእኛ መተባበር ሥራ ውጤት ወይም በቤተ ክርስትያን ውስጥ ባለው ደሞክራሲ ወይንም ተስማምተን ለመኖር በምናደርገው ጥረት የሚመጣ እንዳይመስላችሁ፤ ነገር ግን በልዩነቶች አንድነትን ከሚፈጥረው ከመንፈስ ቅዱስ የሚጀምረው፣ ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ ውህደት ስምምነት ስለሆነ በቤተ ክርስትያን ውስጥ ውህደትን ይፈጥራል፣ ይህ የተወሃሃደ አንድነት በተለያዩ ባህሎች ቋንቋዎችና አስተሳሰቦች መካከል የሚፈጠር አንድነት ነው፣ አንቀሳቃሹም መንፈስ ቅዱስ ነው፣ በዚህም ምክንያት እንደ የአንድነት እና የውህደት ሰዎች ነፍስ ሆኖ የሚያንቀሳቅሰን ጸሎት ዋና እና አስፈላጊ ነው፣ በተለይ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ በቤተ ክርስትያን መጥቶ አንድ እንዲያደርጋት የመንፈስ ቅዱስ ጸሎት አስፈላጊ ነው፣
ጌታ እንዲህ ስንል እንለምነው! ጌታ ሆይ ሁሌ አንድ የምንሆንበት ጸጋ ስጠን፤ የመከፋፈል መሳርያ ከመሆን ሰውረን፤ ብለን እንለምነው፣ ስመ ጥር ቅዱስ ፍራንቸስኮስ የደረሰውን ጸሎት የገዛ ራሳችን በማድረግም “ጌታ ሆይ! ጥላቻ ባለበት ፍቅር በደል ባለበት ይቅርታ መለያየት ባለበት የዕርቅና የሰላም መሳርያ እንድሆን አድርገኛ ብለን እንጸሊ፣ አሜን








All the contents on this site are copyrighted ©.