2013-09-23 19:10:58

“በመልካም እረኛ ሆናችሁ ዘወትር በመንጋዎቻችሁ መካከል ሁኑ፤ ሕዝበ እግዚአብሔር የእናንተ ፍላጎት አለው፣”


በመንበረ ጴጥሮስ በጳጳሳዊ ማኅበርና የምስራቃውያን አብያተ ክርስትያን ማኅበር የተዘጋጀ ለአዳዲስ ጳጳሳት የሚሰጥ አውደ ጥናት ላይ የተሳተፉ የዘንድሮ አዳዲስ ጳጳሳት ትናንትና ከቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ጋር ሲገናኙ፤ ቅዱስነታቸው “በመልካም እረኛ ሆናችሁ ዘወትር በመንጋዎቻችሁ መካከል ሁኑ፤ ሕዝበ እግዚአብሔር የእናንተ ፍላጎት አለው፣” ሲሉ ጳጳሳት እንደ እረኞች ሁሌ ከመንጋቸው ጋር እንዲሆኑ የሥልጣን እሽቅድድም ትተው በቃላቸው የሚያስተምሩትን በሕይወታቸው መመስከር እንዳለባቸው አሳስበዋል፣
አያይዘውም “በችሎታችን ሳይሆን በጌታ ጸጋ እረኞች ለመሆን የተጠራንና የተቋቋምን ነን ይህም ለሕዝበ እግዚአብሔር አገልግሎት እንጂ ለገዛ ራሳችን ምቾት አይደለም፣ ስለዚህ ጌታ በጎቼን ጠብቁ ብሎ የሰጠን ስልጣን በሶስት ቃላት ሊገለጥ ይችላል፣ ልባችን ሁላቸውን እንዲቀብል ታላቅነትና ክፍትነት እንዲኖረው ከመንጋው ጋር መጓዝና ዘወትር በመካከላቸው መኖር ናቸው፣ ልባችን በየዕለቱ የምናገኛቸውን ሁሉ ለመቀበልና ሌሎችን ለመፈለግ ታላቅና ክፍት መሆን አለበት፣”
“ካሁን ጀምራችሁ የቤቴን በር ለሚያንኳኩ ሁሉ እንዴት እንቀበላቸው! ለሁሉም መልካም እረኛ በመሆንና ለመርዳት ዝግጁ እንደሆናችሁት መጠን በሩን ክፍት ሆኖ ያገኙት እንደሆነ የእግዚአብሔር አባትነትን ያጣጥማሉ እንዲሁም ቤተክርስትያን ርኅሩኅ እናት ሆና ሁሌ እንድምትቀበላቸውና እንደምታፈቅራቸው ይረዳሉ” ሲሉ ሁሉን መቀበል እንዳለባቸውና በጉⶋአቸው መሸኘት እንዳለባቸው አሳስበዋል፣ ከም እመናኑ ጋር መጓዝና መሸኘት ምን ማለት መሆኑ ሲገልጹ ደግሞ በም እመናኑ ደስታና ተስፋ ችግርና ሥቃይ እንደ ወንድሞችና እንደ ጓደኞች መካፈል እንዳለባቸው በበለጠው ደግሞ ሊሰምዋቸው ሊረድዋቸው እንዲሁም ሊረድዋቸውና አቅጣጫ ሊያስይዛቸው እንደሚችል ርኅሩኅ አባት ሆነው እንዲቀበልዋቸው ያስፈልጋል፣ በተለይ ደግሞ ለጳጳሳት እጅግ ቅርብ የሆኑና ከመንጋው የማይለዩ ካህናት ምክርና እርዳታ በሚያስፈልግበት ጊዜ መተባበር እንዳለባቸው ጳጳሳትም ካህናቱን እንደ አባቶች ወንድሞችና ጓደኞች አድርገው ሊቀበልዋቸው እንደሚግባም አስመረውበታል፣
“ማድረግ ከሚገባቸው ዋና ነገሮች አንደኛው ስለ ካህናቶቻችሁ መንፈሳዊ ሁኔታ ማሰብ ነው ይህ ማለት ግን ቁሳዊ ፍላጎታቸውንም መዘንጋት እንደሌለባችሁ አስታውሱ ከሁሉ በላይ ደግሞ በሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮአቸውና በሕይወት ኑሮአቸው አስቸጋሪና አስፈላጊ በሆኑ ግዝያት እንድትረድዋቸው ይሁን፣ ከካህናት ጋር የምታሳልፉት ጊዜ ከቶ የጠፋ ጊዜ አይደለም፣ ሊያገኝዋችሁ በመጠየቁ ጊዜ ወዲያዉኑ እንድትቀብልዋቸው ይሁን፣ ካህን የደወለው የተለፎን ጥሪ ሳይመለስ እንዳይቀር፣ ወዲያውኑ የማይመች ከሆኖ ቢያንስ በሚቀጥለው ቀን መልሶ መጥራት ያስፈልጋል፣ በስልክ መናገር ብቻ ሳይሆን በአካል እንድትገናኙም ጊዜ መወሰን ያስፈልጋል፣ ቅርበታችሁ እንዲጸና ይሁን፣ ሲሉ በካህናትና በጳጳሳት መካከል መስረጽ ያለበት ቅርበትና መረዳዳት እንዲሁም መተባበር ጥብቅና ጥልቅ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል፣
ቅዱስነታቸው እንደገና ወድሚወዱት ሓረግ “እረኛ የበግ ጠረን መኖር አለበት” ሲሉ ጳጳሳት ከም እመናን ጋር ያላቸው ግኑኝነትም ከዛው ባለነሰ መዘውተር እንዳለበት እንዲህ ሲሉ አሳስበዋል፣
“ለመኖር እና ለማስተንፈስ አየር እንድሚያስፈልግ ሁሉ በገዛ ቤታችሁ ተዘግታችሁ ዝም ከማለት በሕዝባችሁ መካከል ሂዱ ማንም የማይሄዳቸው ድኅችና የተገለሉ ሰዎች በሚርኖሩበት አከባቢም እየሄዳችሁ ብቸኝነት ድኅነትና ስቃይ ሰብ አዊ ሁኔታቸውን ዝቅ ወዳደረጋቸው ሰዎች ሂዱ፣ በሐዋርያዊ ግብረተል እኮ እረኛነት ማለት ከሕዝቡ ጋር መጓዝ እንዲያው መሪ ሆኖ መጓዝን ያመልክታል፣ በዚህም መንገዱን ልታሳዩ አንድነታቸውን ልታጠነክሩ ትችላላችሁ፣ እንዲሁም ከበስተኋላም መከታተል ያስፈልጋል ምክንያቱም አደራ ከተሰጥዋችሁ ም እመናን ማንም ኋላ እንዳቀር ከሁሉ በላይ ደግሞ የእግዚአብሔር ሕዝብ አዳዲስ ጐዳናዎች ለማግኘት ለመርዳት ነው፣ ከሕዝቡ ጋር የሚጓዝ አንድ ጳጳሳ የበጎቹን ድምጽ ለመስማት ክፍት ጅሮዎች አሉት፣ በሃገረስብከቶቻችሁ የሚገኙ የተለያዩ ተቅዋሞች ደግሞ ለመረዳዳትና ለመመካከር የሚረዱ መሆን አለባቸው፣ ጳጳሳት እንዲህ በማድረጋቸው የሕዝባቸው ባህል ኑሮና ሁኔታ በበለጠ ለመረዳትም ይችላሉ፣ ይህንን ሁሉ ሲያደርጉ ከሁሉ በላይ ትሕትና እንደሚያስፈልጋቸውም ገልጠዋል፣
“እኛ ጳጳሳት መስፍናዊ አስተሳሰብ ያለን ሰዎች አይደለንም፤ የበለጠች እጅግ አስፈላጊ እና ሃብታም የሆነች ሌላ ቤተ ክርስትያን የመሻት ጉጉት ያለን ሰዎችም አይደለንም፤ ይህ ዕንቅፋት ነው! በሥልጣን ሽኩቻ ፈተና እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ! መድኃኒት የሌለው ወረርሽኝ ነውና! ይህንን በቃል ብቻ ሳይሆን ተጨባጭ በሆነ መንገድ በአኗኗራችሁ መመስከር ያለባችሁ ስለሆነ በሕይወታችሁ ምሳሌያውን የሕዝብ አስተማሪዎች እንድትሆኑ አደራ፣ የእምነት ስብከት የምታስተምረውና ኑሮህ አንድ እንዲሆነ ቅድመ ሁኔታ ይጠይቃል፣ ተል እኮ የሕይወት አኗኗር አይለያዩም፣ በየዕለቱ የምኖረው ሕይወት ከምሰብከው ጋር ይስማማልን ብላችሁ ኅልናችሁን መርምሩ፤ የምታደርጉትን ሁሉ ለክርስቶስ ስትሉ አድርጉት እንጂ ምንም ዓይነት የጥቅም ፍላጎት እንዳያሸንፋችሁ አደራ፣ ለኑሮ አችሁና ለስብከተ ወንጌል የሚያስፈልግዋችሁ መጠነኛ የሆኑ ነገሮችን ተጠቀሙ እንጂ ለእዩልኝ ስሙልኝ የሚደረግ ነገር ሁሉ ከሕይወታችሁ ይወገድ ሲሉ መጠነኛ ኑሮ እንዲኖሩ አሳስበዋል፣
“የአየር ማረፍያ ጳጳሳት የመሆን ዕንቅፋትን አስወግዱ! እንግዳ ተቀባይ እረኞች ሁኑ! ከሕዝባችሁ ጋር በፍቅርና በርኅራኄ እንዲሁ በአባታዊ ጣዕምና ጽናት በትሕትናና በመጠን ኑሩ! በተቻላችሁ መጠን አለምንም ክብደት ከመንጋዎቻችሁ ጋር ቀለል ባለ መንገድ እየቀለዳችሁም ተወያዩ፣ ይህ ልዩ ጸጋ ጳጳሳት መለመን ያለብን ነው፣ ለሁሉም ክፍት መሆን! ነገሮችን ቀለል ባለ መንገድ መግለጥ፣ ከሁሉ በላይ ግን ከመንጋውቻችሁ ሁኑ ሲሉ ደጋግመው በማሳሰብ ምክራቸውን ለግሰዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.