2013-09-23 18:10:11

አለሥራ ክብር የለም! አምልኮ ንዋይ ምጣኔ ሃብታዊ ሁኔታችን ማዘዝ የለበትም፣


ይህንን ያሉት ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና በሳርደኛ ባደረጉት ጉብኝት ክፍለ ሃገርዋ ስራ በማጣት በሚሰቃዩ ሰዎች አጥለልቃ ባዩት ጊዜና ሁኔታውን ሰራተኞቹ በገለጥዋቸው ጊዜ ነው፣ ቅዱስነታቸው ለሐዋርያዊ ጉብኝት ካልያሪ በገቡ ጊዜ በየነ አደባባይ ከ20 ሺ በላይ የሚሆኑ ተቀብለዋቸው በጉብኝቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልጠው ስላለው ሁኔታ ሶስት ሰዎች ተራ በተራ በሠራተኞች እና በአሰሪ ድርጅቶች ላይ ወርዶ ስላለው ችግር በገለጡላቸው ጊዜ ሁኔታው ልባቸው እጅግ ስለነካ እሳቸው ራሳቸውም በ1930 ዓም ዓለም አቀፍ ምጣኔ ሃብታዊ ቀውስ ወደ አርጀንቲና ከተሰደዱ ቤተ ሰብ የተወለዱና አሰቃቂ ድህነት ምን መሆኑ እንደሚያውቁትና ይህ ሁሉ ችግር የሰው ልጅ ገንዘብን በማምለኩ ገንዘብም ሁሉን በማዘዙ እንደተከሰተ ገልጠው! ስራ የሰው ልጅ ክብር! ስራ ዕለታዊ እንጀራ የማገኛ ምንጭ! ስራ የፍቅር መግለጫ በአጭሩ ስራ ጸሎት መሆኑን ገልጠዋል፣ ለቅዱስነታቸው ችግራቸውን ከገለጡ አንዱ ተናጋሪም ይህንን የሚደግፍ ዓይነት ሓሳብ እንዲህ ሲል አቅርበዋል፣
“የሥራ ማጣት ችግርን የሚሸከሙት ቤተ ሰቦች ናቸው፣ አብዛኛውን ጊዜ በቤተ ሰብ መካከል የሚነሳው ጸብ በተለይ ደግሞ በባልና ሚስት እንዲሁም የአብራክ ፍሬ የሆኑ ልጆቻቸውን ሳይቀር የሚጐዳ ሁኔታ የሚከሰተው የስራ አጥነት ችግር በሚያስነሳው ሳቢያ ነው፣ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የእኛ የሁላችን አባት ስለሆንክ እባክህ እኛን መንጋህን በዚሁ የዘመናችን ነጣቂ ተኵላ የሆነው ተስፋ የመቍረጥና የሕይወታችን ፈታኝ በሆነ ሁኔታ ብቻችን አትተወን፣” በማለት ተማጥነዋል፣
ሁኔታው እጅግ የሚያሳዝን ነው፣ ቅዱስነታቸውም ልባቸው እጅግ ስለተነካ ሊያነቡት ያቀረቡትን ጽሑፍ ትተው የምራቸውን መናገር ጀምረዋል፣ ለዚህም በቤተሰቦቻቸው ታሪክ ጀመሩት፣ ቤተ ሰቦቻቸው ከኢጣልያ ወደ አርጀንቲን የተሰደዱበት ድህነትን በማስታወስም በብርቱ ስሜት እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፣
“ቤተ ሰቦቼ ሁሉን አጡ! ስራ አልነበረም! ብሕጻንነቲ ይህንን ታሪክ እሰማው ነበር! እኔ ምንም አላየሁም! ገናም አልተወልድኩም! ሆኖም ግን ስለዚህ አሰቃቂ ጊዜ በቤቴ ሲነገር እሰማ ነበር! ስለዚህ ምን እንደምትሉ ጥሩ አድርጌ አውቃለሁ! አይⶋአችሁ በርቱ ልላችሁ እወዳለሁ፣ ሆኖም ግን ይህ ብርታት ይኑራችሁ የሚል አነገጋገር የማንኛው መንገድ አላፊ ንግግር አይደለም! የምሬን ነው!
!”ይህ ቃል አንድ የቤተ ክርስትያን ሰራተና የሚላችሁ አይዞ በርቱ አይደለም፣ እኔ ይህንን ለማለት አልፈልግም፣ ይህ ቃል ከውስጤ መፍለቅ አለበት እንደ እረኛ እንደ ሰው መጠን ደግሞ የተቻለኝን ያህል ለማድረግ የሚገፋኝ ኃይል መሆን አለበት፣ ይህንን ታሪካዊ ችግራችን በጥበብና በአጋርነት መጋፈጥ አለብን፣ አጋጣሚ ሆኖ ያደርግህዋቸው ሁለት ሓዋርያዊ ጉብኝቶች በሁለት ደሴቶች ላይ ነው፣ የመጀመርያው በላምፐዱሳ ሲሆን ያ ምንም የሌለው ድኃ ኅብረተሰብ በየዕለቱ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ተስፋ በማጣት ሕይወታቸውን ለመዳን በተለያዩ መርከቦች በሚመጡ ስደተኞች አጥለቅልቀው አገኝህዋቸው! ከሁሉ በላይ የማረከኝ ግን ታላቅ ልብ ስላላቸው ሁሉን ተቀብለው ያላቸውን ትንሽ ነገር ከስደተኞች ጋር ሲካፈሉ አይቻለሁ፣ በዚህ በካልያሪም ቢሆን ብዙ ስቃይ እመለከታለሁ፣
“ከእናንተ መካከል አንዱ እንደገለጸው ይህ ስቃይ አድክሞህ ተስፋህ ሊሰርቅ እንደሚሻ ጠላት ነው፣ ይህ የሥራ ማጣት ስቃይ ነው! እውነቱን ጥርት አድርጌ ለመግለጥ ኃይለ ቃል እጠቀማለሁ ሆኖም ግን እውነትን መናገር ስላለብኝ ይቅርታ! ስራ አጥ መሆን ማለት ክብር የሌለውህ መሆን ማለት ነው! ስራ የሰው ልጅ ክብር ነውና! ስራ ከጠፋ መብት ይጠፋል፣ ስራ ከጠፋ የእለት እንጀራ ይጠፋል! ይህ የሳርደኛ ብቻ ችግር አይደለም ሆኖም ግን እዚህ እጅግ ገነዋል! በመላው ኤውሮጳ ይህ ችግር እያንዣበበ ነው፣ ይህንም የሆነበት ምክንያት ገንዘብን የሚያመልክ ምጣኔ ሃብታዊ ስልት በመጠቀማቸው ነው፣ እግዚአብሔር ግን እርሱ ብቻ እንጂ ገንዘብ የሚባል አማልክት ሊኖር አልፈለገም፣ በዚሁ ግብረ ገብነት የሌለው ምጣኔ ሃብታዊ ስልት መካከል አንድ ጣዖት አለ እርሱም ገንዘብ ነው፣
“ሁሉን የምያዝ ገንዘብ ነው! ገንዘብ ያዛል! ለእርሱ የሚያገልግሉትን ሁሉ ይገዛል ይህም አምልኮ ጣዖት ነው፣ እንዲህ ከሆነ ምን ይከተላል ያልን እንደሆነ ይህንን ጣዖት ለመከላከል ሁላቸው በእርሱ ዙርያ ይሰበሰባሉ፣ እዛ ሊደርሱ የማይችሉ ኃይልና ጉልበት የሌላቸው ወድቀው ይቀራሉ! እነኚህም ሽማግሌዎች ሕጻናት ሕሙማን እና ረዳት የሌላቸው በቅድምያ ይወድቃሉ፣ ይህም የሚሆንበት ምክንያት ለእነዚህ ሰዎች የሚሆን ቦታ የለም፣ የባሰው ደግሞ ስራ የሌላቸው ወጣቶችም ከእነዚህ ቡድን ጋር ይጨመራሉ፣ ስራ አያገኙም ክብር የላቸውም መብትም የላቸውም፣ እስኪ አስቡት ሁለት የወጣት ትውልድ አልስራ ቢዋልል ምን ይመስላችሁዋል፣ ዓለማችን መጻኢ እንደሌላት ነው፣ ምክንያቱም ወጣቶቹ ክብር የላቸውምና፣ አለሥራ ክብር ሊገኝ እጅግ አስቸጋሪ ነው፣ ስቃያችሁም ይህ ነው፣ እናንተ ደጋግማችሁ የምትጸልዩት ጸሎትም ይህ ነው፣
“ስራ ስራ ስራ፣ ይህ ጸሎት ነው፣ አስፈላጊ ጸሎትም ነው፣ ምክንያቱም ስራ ማለት ክብር ማለት ስራ ማለት ወደ ቤትህ የዕለት እንጀራ ይዞ መግባት፣ስራ ማለት ማፍቀር ነው፣ ሌላው አሳዛኝ ክስተት ደግሞ እላይ የጠቅስነውን የአምልኮ ጣዖት ምጣኔ ሃብታዊ ኑሮ ለመከላከል የመገለል የማይረባውን የመጣል ባህል ሰርጸዋል፣ የሚጣለው ምግብና ቁሳቁስ ብቻ ሳይሆን ምርት የማይሰጥ ሁሉ መጣል አለበት! ሕሙማን! የአካል ጉዳተኞች! አሮጌዎች ወዘተ መጣል አለባቸው፣ እኛ ማለት ያለብን ይህ የመጣል ባህል መሆን የለበትም ነው፣ ፍትሕ ያለበት አስተዳደር እንፈልጋለን፣ ሲሉ በርትተው ለክብራቸው መታገል እንዳለባቸው አሳስበዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.