2013-09-23 19:12:44

በክርስትያኖችና በሙስሊሞች መካከል መረዳዳት የተገኘ እንደሆነ በዓለም ውስጥ ሰላም ይነግሣል::


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለሱኒት እስላሞች ባህላዊ ዋና ተቅዋም ለያዘው የአል አዝሃር ዪኒቨርሲቲ ታላቁ ኢማም ሸክ አሕመድ አልጣየብ በጻፉት መልእክት በክርስትያኖችና በሙስሊሞች መካከል መረዳዳት የተገኘ እንደሆነ በዓለም ውስጥ ሰላም ይነግሣል ሲሉ አሳስበዋል፣ የዩኒቨርሲቲው መንበር በካይሮ ሲሆን ፊደስ የሚባለው የዜና አገልግሎት ከካይሮ ጽሕፈት ቤቱ እንዳረጋገጠው የር.ሊ.ጳጳሳቱ መል እክት ለኢስላም ሃይማኖትና ለሙስሊሞች ታላ አክብሮትና ግምት የሚሰጥ መሆኑን እንደገለጡና ክርስትያኖችና ሙስሊሞች ሁላቸው አብረው ሰላምና ፍትህን ለማንገስ የተረዳዱ እንደሆነ ዓለም አቀፉ ሰላም ሩቅ እንዳልሆነ እንደገለጹ አመልክተዋል፣ ቅዱስነታቸው ይህንን የግል መል እክታቸውን በካይሮ በሚገኘው እንደራሴያቸው ማለትም ኑንስዮ አፖቶሊኮ ብፁዕ አቡነ ዣን ፖል ጎበል አማካኝነት እንደላኩት ሲመለከት መል እክቱ የጳጳሳዊ የውስጠ ሃይማኖት ውይይት ምክር ቤት የሮማዳን ጾም ፍጻሜ ላይ ከጻፈው መል እክትም እንደሚያያዝና ወዲያውኑ በመጻፉ ፍሬ ያስገኛል የሚል እምነት እንዳለም ተገልጸዋል፣ ባለፉት ዓመታት በአል አዝሓር እና በቅድስት መንበር መካከል ውስጠ ሃይማኖታዊ ውይይት ይካሄድ እንደነበረና በካይሮው አል አዝሓር ጥያቄ መሠረት ውይይቱ እንዳቋረጠ ምክንያቱም ልሂቅ ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ በግብጽና በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ ክርስትያኖች የሚከላከልላቸው የለም ወይ በሚል አሳቢነት በአለክሳንድርያ በ2011 ር እሰ ዓመት ላይ በኮፕቶቹ ካተድራል ካጋጠመው አደጋ በኋላ ባስተላለፉት ጥሪ እንደሆነ ይነገራል፣
ያም ሆነ ይህ የአለክሳንድራይ ካቶሊካውያን ኮፕቶች ፓትርያርክ ጸሓፊ አባ ሃኒ ባኹም ለፊደስ እንደገለጹት ከሆነ መልእክቱ ቅዱስት መንበርና ር.ሊ.ጳ ሙስሊሞችን በሚመለከት በተለይ ደግሞ የአል አዝሓር ሱኒ ሙስሊሞችን የሚወክል ማኅበረሰብ ላይ ያላቸውን አስተያየትና ለክርስትያኑ ማኅበረሰብ ያላቸውን ፍቅር ይገልጻል፣ በእርግጥ ይህ መልእክት በመካከላችን ያሉትን ልዩነቶም ለማጥበብ እንዲሁም በቅድስት መንበርና በአል አዝሓር መካከል የነበረውን ውይይት እንደገና ለማነሳሳት ይረዳል ሲሉ አስተያየታቸውን ገልጸዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.