2013-09-23 18:12:51

የእምነት ዓመት መዝግያ ቀናት በቅድስት መሬት


ለቅድስት መሬት ቤተ ክርስትያን የእምነት ዓመት መዝግያ ቀናት እ.ኤ.አ ኅዳር 16 እና 17 ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲሆን ተወሰነ፣ በቅዱስ መሬት የሚግኙ ካቶሊካውያን አብያተ ክርስትያን ማለት የላቲኑ ሥርዓት የሚከተሉ እንዲሁም የመልካይት የማሮናይት የሲሮ አንጾክ ያ እና የአርመን ሥርዓት የሚከተሉ ካቶሊካውያን አብያተክርስትያን ናዝሬትን እንደ ዋና ማእከል በመምረጥ እላይ በተጠቀሱት ዕለታት ዓለም አቀፍ የእምነት ዓመት መዝጊያ ቀናት እንዲሆኑ ተስማምተዋል፣ በእነዚሁ አብያተ ክርስትያን ጳጳሳት የቆመ አንድ ኮሚቴ እንዳለና ኮሚቴውም በኅዳር 16 ቀን በብስራተ ገብር ኤል ባዚሊካ ማርያማዊ ሥር ዓተ አምልኮን እንድሚያዘጋጁ እንዲሁም በኅዳር 17 ቀን ጌታን ገፍተው ለመግደል በፈለጉት ገደል አፋፍ ላይ በናዝሬት ከተማ የሚካሄደውን የመሥዋዕተ ቅዳሴ ሥር ዓት ያዘጋጃሉ፣ በዚሁ ቦታ ላይ ባለፈው ግንቦት 14 ቀን 2009 ዓም ልሂቅ ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ነበር፣
All the contents on this site are copyrighted ©.