2013-09-23 18:09:10

እግዚአብሔር ከቶ እንደማይተወን ከእመቤታችን ድንግል እንማር!


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና በሳርደኛ የካልያሪ ደሴትን በጎበኙበት ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ “እግዚአብሔር ከቶ እንደማይተወን ከእመቤታችን ድንግል እንማር!” ሲሉ ሰብከዋል፣ ሥልጣነ ጴጥሮስ ከያዙ ከስድስት ወራት ወዲህ ይህ በጣልያን አገር የሚያደርጉት ሁለተኛ ሐዋርያዊ ጉብኝት ሲሆን አንደኛውን ባለፉት ወራት በላምፐዱሳ ደሴት አድርገው ነበር፣
መላው ዓለምን አስቸግሮ ያለው የምጣኔ ሃብት ቀውስ ሁሉም ሲያሰቃይ በተለይ በሳርደኛ ሥራ አጥነት እጅግ ከፍተኛ ብሶት ሆኖ ስላለ በቦታው ሁሉንም ለማግኘትና ለማጽናናት ሠራተኞች ወጣቶችንና የተለያዩ ድኆችን አግኝተው እንዳጽናኑና ተስፋ እንደሰጡም ተነግረዋል፣
ቅድስነታቸው ካልያሪ በደረሱ ጊዜ በእመቤታችን ድንግል ማርያም ዘቦናርያ መካነ ንግደት አደባባይ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ም እመናን ደማቅ አቀባበል አድርገልዋቸዋል፣ ለዕለቱ ቅዳሴ እንዲያሳርጉ የተዘጋጀው መንበረ ታቦት በባህር ጠረፍ ላይ ተሠርቶ ስለነበርም ልዩ ስሜት የሚፈጥር ቢሆንም ቅዱስነታቸው ግን ዓይኖቻቸውና ልባቸው በሕዝቡ ሰቆቃ ላይ ስለነበር መጀመርያ በቦታው የሳርድ ቋንቋ የጌታ ሰላም ሁሌ ከእናንተ ጋር ይሁን፤ በማለት ሰላምታ ካቀረቡ በኋላ ይህንን ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ የገፋቸው ምን እንደሆነ በቀጥታ መግለጥ ጀምረዋል፣ እዚህ ያመጡኝ ሶስት ምክንያቶች ናቸው አንደኛውና ዋነኛው ባሁኑ ጊዜ የሚሰምዋቸው የደስታና የተስፋ የድካምና የኃላፊነት እንዲሁም ህልምቻችሁና ፍላጎታችሁን ከእናንተ ጋር ለመካፈልና በእምነት እንዳጸናችሁ ነው፣
“የሁላችን ታማኝ መተባበር አስፈላጊ ነው፤ ዋናዎቹ ኃላፊነት የለበሱ ባለሥልጣኖችና ተቅዋሞች ቢሆንም ቤተ ክርስትያን ለእያንዳንዱ ሰውና ለቤተ ሰብ መሠረታውያን መብቶቻቸው እንዲጠበቁና ውንድማማችነትና አጋርነት የነገሰባት ማኅበረሰብ ለማሳደግ ትተባበራለች፣ ዛሬ እዚህ ላይ ልጅዋን በሰጠችን በእመቤታችን ድንግል ማርያም ሥር ከእናንተ ጋር መቆሜ ደግሞ ሁለተኛው የዚህ ጉብኝት ዓላማ ነው፣ ዛሬ ሁላችን እመቤታችን ድንግል ማርያምን ሁል ጊዜ ስለምትሸኘን ልናመስግናት እንፈልጋለን፣ ብለው ሁለተኛ የጉብኝቱ ምክንያት ከገለጡ በኋላ በዕለቱ ሥር ዓተ አምልኮ በተነበበው የመጀመርያ ንባብ ላይ እመቤታችን በጽርሓ ጽዮን ከሓዋርያት ጋር አብራ ስትጸልይ የሚያመልክት ስለነበር ይህንን አስመልክተው እንዲህ ብለዋል፣
“እመቤታችን ድንግል ማርያም ትጸልያለች፤ ከደቀ መዛሙርት ማኅበር ጋር ሆና ትጸልያለች፤ እንዲህ በማደረግዋም በእግዚአብሔር ርኅራኄና ምሕረት ሙሉ መተማመን እንዲኖረን ታስተምረናለች፣ የጸሎት ኃይል ይህ ነው! የጌታ በርን ከማንኳኳት አንታክትም!! እመቤታችን ድንግል ማርያም ጌታ ከቶ እንደማይተወን ታስተምራናለች! ምንም እንኳ ደካማዎች ብንሆንም ታላላቅ ነገሮች ሊያደርግ ይችላል፣ በመጨረሻም ሶስተኛው የዚህ ጉብኝቴ ዓላማ የእመቤታችንን ጥበቃ ለመጠየቅ መጣሁ ሁላችንም እንዲሁ ጥበቃዋን ለመጠየቅ ነው የመጣነው፤ በምሕረት ዓይኖችዋ እንድትመለከተን፣
“የእርስዋ አጽናኝ ጥበቃና እይታ ያስፈልገናል፣ ይህ እይታ እናታዊ ስለሆነ የዚሁ ፍቅርና አሳቢነት የሞላው እይታ ከማንም በላይ ያውቀናል፣ እመቤታችን ድንግል ማርያም ዛሬ ለማለት የምንፈልገው! እናታችን ሆይ ተመልከቺን! ይህ እይታሽ የመልካሙ እግዚአብሔር አባታችን ስጦታ ነው፣ በሕይወት ኑሮ ጉⶋአችን ሁሌ ይሸኘናል፣ በዚሁ ስቃይ ድካምና ኃጢአት በሞላው ሕይወታችን ደግሞ ጌታ ኢየሱስ በመስቀላይ ላይ ሆኖ የሰጠን ስጦታ መሆኑንና ሁሉንም ጌታ እንደተሸከምልን ያሳየናል፣ እመቤታችን ድንግል ማርያም ወንድማሞች እንድንሆን ትጠራናለች፣ በሕይወት ኑሮ ጉዞ አችን ብቻችን አይደለንም አንድ ሕዝብ ነን! እንዲያው የእግዚአብሔር ሕዝብ ነን! በወንድማማችነት እንኑር! ችግረኞችና ድሆች ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን በምሕረት እይታ መመልከትንና መርዳትን ከእርስዋ እንማር፣ በዚሁ የምሕረት እይታዋና በመካከላችን ማንም ገብቶ እንዲዘበርቀው አንፍቀድ፣
“የእኛ የልጆችዋ ልብ ከሓሰተኞችና የማይጨበጥ ተስፋ ከሚሰጡ ለፍላፊዎች ይጠንቀቅ! እነኚህ ሰዎች ሕይወትን ቀለል ባለ መንገድ በመመልከት ሊፈጸሙ የማችሉ ተስፋዎች ይሰጡናል፣ ፍቅር የሞላውና ኃይል የሚሰጠን እና በአጋርነት እንድንኖር የሚረዳን የእመቤታችን እይታን አይስረቁብን፣ ሲሉ ከሰበኩና መሥዋዕተ ቅዳሴን ከፈጸሙ በኋላ በቦታ በነበረው የእመቤታችን ድንግል ማርያም ዘቦናርያ የሚከተለውን ጸሎት ስለሁላችን አሳርገዋል፣
“ለእያንዳንዱ የዚሁ ከተማና አውራጃ ቤተሰብ እለምንሻለሁ! ስለ ወጣቶች ስለ ሽማግሌዎች እና ስለ ታመሙት እንዲሁም ብቻቸው ቀርተው በብቸኝነት ስለሚሰቃ ዩ እና በየእስር ቤቱ ስለሚገኙ ሁላቸው! በረሃብ ስለሚሰቃዩና ስራ በማጣት ስለሚቸገሩ ሁሉ! ተስፋ ስለቆረጡና እምነታቸውን ስላጠፉም ሁሉ እለምንሻለሁ፣ ስለአስተዳዳሪዎችና ስለ አስተማሪዎችም እለምንሻለሁ፣ ጣፋጭዋ እናታችን ሆይ ጌታ ኢየሱስ አሳዪን እርሱ የሚለንን ነገር ብቻ እንድናደርግ ዘንድም አስተምሪን ሲሉ ተማጥነዋል፣
All the contents on this site are copyrighted ©.