2013-09-19 18:34:29

የአፍሪቃና የመደጋስካር የቅዱስ መጽሓፍ ማእከል ስምንተኛ አጠቃላይ ጉባኤ:


የሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮ አንኳር ቅዱስ መጽሓፋዊ ቅስቀሳ ነው በሚል መሪ ሐሳፍ የአፍሪቃና የመደጋስካር የቅዱስ መጽሓፍ ማእከል ስምንተኛ አጠቃላይ ጉባኤ በማላዊ በሊኖግወ ከተማ ከነገ መስከረም 17 ቀን እስከ መስከረም 23 ቀን ሊካሄድ ነው፣ እንደ ዋና መነሻ አሳብ አድርጎ የሚወስደው ትምህርትም ከቨርቡም ደሚኒ የጌታ ቃል ከሚለው ብ2010 ዓም ልሂቅ ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ከጻፉት ድኅረ ሲኖዶሳዊ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ነው፣ በዚህም አጠቃላይ የጉባኤው ይዘት ቃለ እግዚአብሔር በሕይወታችንና በቤተ ክርስትያን ተልእኮ በሚመለከት እንደሚወያይም ተመልክተዋል፣ በዚሁ ጉባኤ የሚሳተፉ በአፍሪቃና ማዳጋስካር ረኪበ ጳጳሳት ስዩምፖዝዩም ማለት ሰካም በሚለው ምሕጻረ ቃል የሚታወቀው ጉባኤ አባላት የሆኑ የቅዱስ መጽሓፍ ሊቃውንት ጳጳሳት ካህናት ገዳማውያንና ገዳማውያት ም እመናንና ም እመናት የትምህርተ ክርስቶስ መማህራን እና ወጣቶች ናቸው፣ ከአፍሪቃ ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ክፍላተ ዓለማት የሚመጡ ታዛቢዎችና ተሳታፊዎችም ይኖራሉ፣ እንዲሁም በማላዊ ከሚገኙ ካቶሊካውያን ያልሆኑ ሌሎች አብያተክርስትያንትም ታዛቢዎች እንደሚሳተፉ ተመልክተዋል፣
ከዚሁ አጠቃላይ ጉባኤ የሚጠበቀውም ለሶስት ዓመት የሚሆን ለአፍሪቃ አህጉር የሚያገለግል ቅዱስ መጽሓፍ በዕለታዊ ኑሮ በማኅበራዊ ሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮ ለማስራጨት ነው፣ ዋናው መል እክትም የዚሁ ግብረ ተል እኮ ሠራተኞች ጥሪና ግዴታ ለሰው ልጆች ሁሉ መልካሙ ዜና የሆነው ቃለ እግዚአብሔርን መስበክና በኑⶂአቸው መመስከር መሆኑን ለማስመር ነው፣








All the contents on this site are copyrighted ©.