2013-09-19 18:27:12

ዓለምን የሚያድን የእግዚአብሔር ምሕረት እንጂ የሰው ልጆች ፍትሕ አይደለም:


ይህንን ያሉት ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍርናቸስኮስ ትናንትና እኩለ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት የዕልቱን ቃለ ወንጌል በመመርኰዝ ባስተማሩት ጉባኤ አስተምህሮ ነበር፣ ትናንትና ምንም እንኳ በሮም ዝናም ቢኖርም ምእመናኑና ነጋድያኑ እንደ ወትሮው አደባባዩን አጥለቅልቀውት ነበር፣
በላቲኑ ሥር ዓተ አምልኮ የትናንትናው ቃለ ወንጌል ስለ ጠፍቶ የተገኘው ልጅ በሉቃስ ወንጌል ም ዕራፍ አሥራ አምስት ላይ የሚገኝ ምሳሌ ነበር፣ በዚሁ የሉቃስ ወንጌል ስለ ጠፍቶ የተገኘው በግ እንዲሁም ስለጠፍቶ የተገኘው የወርቅ መሐለቅ ምሳሌዎችም ይገኛኛሉ፣ በአጠቃላይ ም ዕራፉ ስለ የእግዚአብሔር ይቅር ባይነት ይናገራል፣ በተለይ ጠፍቶ የተገኘው ልጅ ምሳሌ ላይ የአባቱ ደስታ ጐልቶ ይታያል፣ ይህም አንድ ኃጢአተኛ ንስሓ ሲገባ የእግዚአብሔር ደስታን ይገልጣል፣
“የእግዚአብሔር ደስታ ይቅር ባይነት ነው፣ ይህም ጠፍቶ በተገኘው በግ ምሳሌ ላይ እንደተገለጸው የጠፋውን በግ የሚያገኝ እረኛ እንደሚሰማው ደስታ እንዲሁም የጠፋ ገንዘብዋን የምታገኝ ሴና የጠፋ ልጁን በሚያገኝ አባት ምሳሌ ላይ እንደተገለጸው ነው፣ በተለይ ያ ጠፍቶ የተገኘው ልጅ አባት ስለልጁ ሁኔታ ሲገልጥ ልጄ ጠፍቶ ነበር አሁን ግን ተገኘ ሞቶ ነበር አሁን ግን ወደ ሕይወት ተመለሰ በማለት ወደ ቤቱ ስለተመለሰው ልጅ እንደሚገልጠው ነው፣ አጠቃላይ የወንጌል መል እክት እዚህ ይገኛል በጠቅላላ የክርስትና ትምህርትና እምነትም በዚሁ ምሳሌ ይገኛል፣ ጠፍቶ የመገኘት ስሜት ወይንም መልካምነት አይደለም፣ ከዛ በላይ ነው፣ ዓለምን ካለት የኃጢአት ካንሰር የግብረ ገብነት ጥፋት ከመንፈሳዊው ሕመም ሊያድናት የሚችል የእግዚአብሔር ምሕረት ብቻ ነው፣ በልቦቻችን እና በታሪካችን የሚከሰቱትን ቍስሎች ሊፈውስና ያለንን ባዶሽ ሊሞላ የሚችል የእግዚአብሔር ፍቅር ብቻ ነው፣ ፍቅር ይህን ማድረግ ይችላል የእግዚአብሔር ደስታም ይህ ነው፣
ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለመናው ምሕረትና ፍቅር ነው፣ ሰው የሆነ እግዚአብሔር ነው፣ እያንዳንዳችን ደግሞ ያ የጠፋች በግ ያ የጠፋው የሴትየዋ ግነዝብ ያ ገንዘቡን ሁሉ በብላሽ ያጠፋው የጠፋ ልጅ ነን፣
“እግዚአብሔር ግን አይረሳንም! አባት ልጁን ፈጽሞ አይረሳምና፣ አባት ሁሌ ትዕግሥተኛ ነው፣ ሁሌ ይጠባበቀናል፣ ነጻነታችንን ይጠብቃል ሆኖም ግን ሁሌ ታማኝ ነው፣ ወደ እርሱ ወደ ቤቱ በምንመለስበት ጊዜ እንደ ልጆቹ ይጠባበቀናል፤ ምክንያቱም በፍቅር ከመጠባበቃችን ለአንድ አፍታ ያህል እንኳ አይቆምምና፣ ልቡም ወደ እርሱ በሚመለስ አንድ ልጅ ሁሌ በታላቅ ደስታ ይሞላል፣ ኃጢአቶኞች ከሆነው ከእኛ አንድ ወደ እርሱ ተመልሶ ይቅረታ በሚጠይቅበት ጊዜ እግዚአብሔር ሁሌ ደስ ይለዋል! ታላቅ በዓል ያደርጋል!
ችግራችንና ዋና አደጋ ገዛ ራሳችንን እንደ ጻድቃን ቆጥሮ ሌሎችን መፈረድ ነው፤ ሆኖም ግን ጓደኞቻችን ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርንም ለምን ኃጢአቶችን አይቀጣም አይገድላቸውም በማለት እንፈርዳለን፤ እግዚአብሔር ግን መሓሪ ስለሆነ ቢምራቸው ብለን ብናስብ ይሻል ነበር፣
“በዚህም በምሳሌው ላይ እንደተመለከተው ታላቁ ልጅ በአባታችን ቤት ደስታና በዓል ከመሳተፍ ይልቅ በውጭ ቀርተን እንፈርዳለን፣ ታላቁ ልጅ ወንድሙ በመመለሱ ደስተኛ መሆን ነበረበት ሆኖም ግን እኔ ይህን ያህል ሳገለግል አንድ ቀን እንኳ ከጓደኞቼ ደስ እንዲለኝ አልፈቀድክም ሆኖም ግን ይህን ገንዘብህን ያጠፋ ልጅህን ይህን ያህል ድግሥ አደረግህለት ይላል፣ በልባችን ምሕረት ከሌለና የይቅር ባይነት ደስታ ያልለበስን እንደሆነ ትእዛዛቱን ሁሉ የምንጠብቅ ብንሆንም ከእግዚአብሔር ጋር አንድነት የለንም፤ ምክንያቱም የሚድን ፍቅር እንጂ ት እዛዛቱን ብቻ መጠበቅ አይደለም፣ የት እዛዛት ሁሉ ፍጻሜ በእግዚአብሔር እና በጓደኛ ፍቅር ይገኛልና፣ የእግዚብሔር ፍቅር ይህ ነው፣ ደስታው ምሕረት በማድረግ ይገኛል፣ ሁሌ ይጠባበቀናል፣ ምናልባት አንድ ሰው ይህንን ሁሌ አድርጌ በማለት በኃጢአቱ ክብደት ሊሰማው ይችላል ሆኖም ግን እርሱ አባት ሰልሆነና መሓሪና ይቅር ባይ ስለሆነ ዘወትር ብምሕረት ይጠባበቀናል፣
በኦሪት እንደተመለከተው ዓይን ቤዛ ዓይን ጥርስ ቤዛ ጥርስ በሚለው ሕግ የምንኖር ከሆንን ከዚሁ ዓለም ክፋት ልንወጣ አንችልም፣
“ጸላኤ ሰናያት የሆነ ክፋት ብልጥ ነው በሰብ አዊ ፍትሕ ዓለምን ልናድንና ገዛ ራሳችን ልናድን እንደሚቻል በማታለል ያሳምነናል፣ እንደእውነቱ ከሆነ ግን በመስቀል የተገለጠው የእግዚአብሔር ፍትህ ለእኛ ሁላችንና ዓለምን በሙሉ ሊያጸድቅ የሚችለው ይህ መስቀል ብቻ ነው፣ ለመሆኑ እግዚአብሔር እንዴት ይፈርደናል ያልን እንደሆነ ሕይወት እየሰጠ ነው የሚያጸድቀን፣ ስለዚህ ለአንዴና ለመጨረሻ የተሸነፈው የዚህ ዓለም ጽድቅና ፍትሕ በዚሁ በእግዚአብሔር ይቅር ባይነት ነው፣ ኢየሱስም ለዚህ ነው የሚጠራን “ሰማያዊ አባታችሁ ይቅር ባይ እንደሆነ ሁሉ እናንተም ይቅር ባዮችና መሓሪዏች ሁኑ” (ሉቃ 6፤36) ይለናል፣
በማለት ካስተማሩ በኋላ በአደባባዩ ለነበሩት ሰዎች እንዲህ ሲሉ ጠይቀዋል፣
“አሁን አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ፣ ሁላችሁ በጸጥታ አስተንትኑ! ያሳዘነው ወይንም ያሳዘነን ሰው እንዳለ አስታውሱ! አሁኑኑ ስለዚህ ሰው በልባችን እንጸልይ ይቅርም እንበልለት! ካሉ በኋላ የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገዋል፣
ከመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት በኋላ ከትናንትና ወዲያ ቅዳሴ ዕለት በአርጀንቲና ብፅ ዕናው የታወጀው የኮርዶባ ሰበካ ካህን አባ ኾዘ ጋብሬል ብሮኸሮ በማስታወስ ካህኑ ምሳሌ ሊሆነን የሚችል ቍምስናውን በታማኝነት ያገለገለና ወደ እግዚአብሔር እንዲመራ የተሰጡትን ምእመናን አንድ በአንድ እየጐበኘና እያጽናና የኖረ ካህን መኖሩን ገልጠዋል፣
“በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ተገፍቶ ሕይወቱን ለም እመናኑ የሰዋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የመራ እና ታላቅ ምሕረትና የነፍሳት ቅናት ያሳየ እረኛ ነበር፣ ሁሌ ከም እመናን ጋር ነበር ዘወትርም ለመንፈሳዊ ሱባኤ ይመራቸው ነበር፣ ዳገትና ቁልቁለት እየወጣና እየወረደ ባለመጥፎ እይታ በምትባለው በቅሎው እየተመላለሰ ያገለግላቸው ነበር፣ ብርድ ዝናም ሳይል በብርታት ያገለግል ነበር፣ ለምን ሲባል እናንተም በዚሁ ብርድና ዝናም እየተመታችሁ ስትኖሩ እኔም እንዲሁ በዚሁ ማገልገል አለብኝ በማለት ም እመናኑም ብርቱ መሆናቸውን ይገልጥላቸው ነበር፣ በመጨረሻ ዓይነ ስውር ሆነ ለምጽም ያዘው ሆኖም ግን ልቡ በደስታ የተሞላ ነበር፣ ይህ ደስታ የመልካም እረኛ የይቅር ባይ እረኛ ደስታ ነበር፣ ሲሉ ካሳሰቡ በኋላ የዚህ ዓይነት ታታሪ ካህናት እንዲገኙ ጸሎት አሳርገው ትናንትና በቶሪኖ ከተማ የኢጣልያ ካቶሊካውያን ኅብረተሰብ ሳምንት በማካሄድ ላይ ያሉትን ሰላምታ አቅርበዋል፣
ይህ በእንዲህ ሳለ ቅዱስነታቸው ዘወትር እንደሚያደርጉት በዘመናችን የመገናኛ ብዙኃን ትዊተር አጭር መል እክት ጽፈዋል፣ የመል እክቱ ይዘትም “ደስታን በዚህ ዓለም ንብረት መፈልግ ደስታን ያለማግኘት እርግጠኛ ምልክት ነው” የሚል ነበር፣








All the contents on this site are copyrighted ©.