2013-09-19 18:24:29

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕልተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ;


ውድ ወንድሞችና እኅቶች! መልካም ቀን ይሁንላችሁ! ዛሬ ቤተ ክርስትያንን እንደ እናት የሚያቀርብልን ምሳሌ እንደገና ለማስተማር እወዳለሁ፣ ይህ ምሳሌ እጅግ ደስ ይለኛል! ስለዚህም ነው እንደገና ለመናገር የፈልግሁት፣ ምክንያቱም ይህ ምሳሌ የቤተ ክርስትያን ማንነትን ብቻ አይደለም የሚያስተምህረን እናታችን ቤተ ክርስትያን ዘወተር ማሳየት ያለባት እናታዊ ገጽታን ስለሚያመለክትም ነው፣
እናቶቻችንን በመመለከት ምን እንደሚያደርጉ እንዴት እንደሚኖሩ ለልጆቻቸው ምን ያህል እንደሚያዝኑ የሚያመለክቱ ባለፈው ትምህርት የጀመርኩትን በማስታወስ ዛሬ ሶስት ነገሮች ላይ ማስመር እወዳለሁ፣ እናት ምን ታደርጋለች ብየም እጠይቃለሁ፣
አንደኛ፤ እናት ከሁሉ አስቀድማ የሕይወት ጉዞን ታስተምራለች፣ በሕይወት ኑሮ እንዴት መጓዝ እንዳለባቸው ልጆችዋን ትክክለኛ አቅጣጫ በማስያዝ የሕይወት የዕድገት ጐዳናን በማመልከት እንዴት አድገው ለብስለት እንደሚደርሱ ታስተምራለች፣ ይህንን ደግሞ በታላቅ ጥንቃቄ ፍቅርና አሳቢነት ታደርገዋለች፣ በሕይወት ኑⶂአችን ሁሌ ስለምንታቀፍም እንዲሁም ወደ ጥፋት የሚወስዱ መንገዶችን በምንከተልበት ጊዜ ዘወትር ትክክለኛውን ፈር ለማስያዝ ትረዳለች፣ አንዲት እናት ልጅዋ በሚገባ እንዲያድግ በሕይወት ኑሮውም መልካም ጐደና እንዲከተል ምን እንደሚያፈልገው ጠንቅቃ ታውቃለች፣ ይህንን ከመጻሕፍት አልተማረችውም፤ ከልብዋ ጥልቀት ይፈልቃል፣ የእናቶች ዩኒቨርሲቲ ልባቸው ነው እዛ ላይ ልጆችን እንዴት ማሳደግ እንዳለባቸው ይማራሉ፣ ይህም መልካም ነገር ነው፣
ቤተ ክርስትያንም ይህንን ነው የምታደርገው፣ ሕይወታችንን ትመራለች፣ መልካም የሕይወት ጐደናን እንድንከተል ትምህርት ትሰጠናለች፣ አስር ት እዛዛትን እናስታውስ፣ በትክክለኛ መንገድ ለማደግ ይመሩናል፣ በጸባያችን መሠረታዊ የሆኑ ሓሳቦች እንዲኖሩን ይረዳናል፣ እነኚህ ት እዛዛት ፍሬ ናቸው በደምብ አስታውሱ! አሰርቱ ት እዛዛት ራሱ ፍቅር የሆነው እግዚአብሔር በአሳቢነት የሰጠን የርኅራኄው ፍሬ ናቸው፣ ምናልባት እናንተ እነኚህ እኮ ትእዛዞች ናቸው! ሁሉም አታድርግ አይሆንም የሚሉ ናቸው! ለማለት ትችላላችሁ፣ እኔ ደግሞ ምናልባት ረስታችሁት እንዳይሆን እንደገና አንብብዋቸው፣ በመልካሙ አዎታዊ ገጽታም አስተንትኑት፣ ከዛም ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግኑኝነት እንዴት መሆን እንዳለበት እንዲሁም ከጓደኞቻችን ያለን ግኑኝነት እንዴት መሆን እንዳለበት እንደሚያስተምሩ ልትገነዘቡ ነው፣ ይህም ልክ እናት ከሌሎች ጋር እንዴት በሰላም መኖር እንዳለብን የምታስተምርን ትምህርት ዓይነት ነው፣ የዚህ ዓለም ቍሳዊ ነገሮችን እንዳናምልክ ይጠሩናል ምክንያቱም የዚህ ዓለም ቍሳዊ ሃብትና ነገሮች ተመልሰው ባርያዎቻቸው ያደርጉናልና! ስለዚህም ስለእግዚአብሔር ማስታወስ እንዳለብን ወላጆቻችን ማክበር እንዳለብን ቅን መሆን እንዳለብን ሌሎችን ማክበር እንዳለብን ያስተምሩናል፣ እነኚህን ነገሮች ልክ እናት ለመልካም አስተዳደግ እንደምትሰጣቸው መልካም ምክሮችና ትምህርት አድርገን እንመለከታቸው፣ አንዲት እናት መጥፎ የሆነ ነገር በፍጹም አታስተምርም፤ ዘወትር የልጆችዋ መልካም ነገር ነው የምትሻው፣ ቤተ ክርስትያንም እንዲህ ነው የምታደርገው፣
ሁለተኛ፤ እንደ ሁለተኛ ነጥብ የምነግራችሁ ነገር ደግሞ አንድ ሕጻን ልጅ ሲያድግ ጐልማሳ ይሆናል የገዛ ራሱ ሕይወት ወይንም መንገድ ይመርጣል፤ ኃላፊነትም ይሸከማል በገዛ ራሱ እግሮች ይራመዳል ደስ የሚለውን ነገር ያደርጋል አንዳንዴም አደጋ ያጋጥመዋል፣ እናት ግን በማንኛውም ሁኔታ በት ዕግሥት ልጆችዋን ትሸኛለች፣ ይህንን ለማድረግ የሚገፋፋት ደግሞ የፍቅር ኃይል ነው፣ አንዲት እናት በት ዕግሥት በፍቅርና በአሳቢነት ልጆችዋን ትከታተላለች ይህንን የምታደርገው ደግሞ ልጆችዋ ቢሳሳቱና ጥፋት ቢፈጽሙም ዘወትር እንድትረዳቸው በጉናቸው ትገኛለች፣ በመጣሁበት አገር ባህል አንዲት እናት ሁሌ ፊትዋን ታሳያለች የሚል አባባል አለን፣ ይህ ማለትም አንዲት እናት ልጆችዋን ለመካላከል ዘወትር ዝግጁ ናት የሚል ሓሳብ አለው፣ በእስር ቤት እና በተለያዩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች የሚገኙ ልጆች እናቶችን አስባለሁ፣ ጥፋት ማድረጋቸውና አለማድረጋቸው ጥያቄ ውስጥ አይገባም እናቶች ልጆቻቸውን ማፍቀር ይቀጥላሉ በልጆቻቸው የሚከተሉትን አሳፋሪ ሁኔታዎች በት ዕግሥት ይቀበሉታል ፍቅራቸውን ለመግለጥ አይደክሙም አይፈርሙምም፣ እናቶች ለልጆቻቸው ፊታቸውን ማሳየት ያውቃሉና፣
ቤተ ክርስትያንም እንዲሁ የይቅር ባይነት እናት ናት፤ ዘወትር ልጆችዋን ትረዳለች ልትረዳቸውም ዝግጁ ናት፤ የተሳሳቱና የሚሳሳቱ ልጆችዋን ለማበራታት ዝግጁ ናት፤ የቤትዋን በሮች በምንም ተአምር አትዘጋም፣ አትፈርዳቸውምም ነገር ግን የእግዚአብሔር ምሕረትን ትሰጣለች፣ ጥልቅ በሆነው የጥፋት ሸለቆ ለወደቁም ልጆችዋ ሳይቀር እንደገና የሕይወት ጉዞን ለመጀመር ጥሪ ታቀርባለች፣ እጅግ በጨለመው የሌሊት ግዝያት ገብታ ለጠፉ ልጆችዋ ተስፋ ለመስጠት ምንም ፍርኃት አይሰማትም፣ እኛም የነፍሳችን ጨለማ የኅልናችን ጥፋት በሚሰማን ጊዜ ቤተ ክርስትያን በዚሁ ሌሊታችን ጨለማ ውስጥ ለመግባት እና ተስፋ እንትሰጠን ምንም ፍርሓት የላትም፤ ምክንያቱም ቤተ ክርስትያን እናት ስለሆነች እንዲህ ታደርጋለች፣
የመጨረሻ ሓሳብም አንዲት እናት አለ ምንም መሰላቸት አለምንም ድካም ልጆችዋን መለመን በሮቻቸውን ማንኳኳት ትችላለች ይህንን የምታደርገውም አለምንም መቆጣጠር በፍቅር ነው፣ ይህም ቍጥር ስፍር የሌላቸው እናቶች በእግዚአብሔር ልብ በር የሚያደርጉት ያልታከተ መንኳኳትን ያሳስበኛል፣ እናቶች ስለልጆቻቸው ብዙ ጸሎት ያሳርጋሉ፤ በተለይ ደግሞ ስለደካሞቹ ብዙ አስፈላጊነት ስላላቸው ልጆቻቸው እንዲሁም በሕይወት ኑⶂአቸው አደገኛ እርምጃ ስለወሰዱ ልጆቻቸው ሌት ተቀን የጌታ ቤት በርን የሚያንኳኳ ብዙ እናቶች አሉ፣ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በዚሁ በሮም በቅዱስ አጎስጢኖስ ባሲሊካ መስ ዋዕተ ቅዳሴ አሳርጌ ነበር፣ በባዚሊካው የቅዱስ አጎስጢኖስ እናት ቅድስት ሞኒካ ቅሪት ይገኛል፣ ይህች ቅድስት እናት ስለ ልጅዋ ስለቅዱስ አጎስጢኖስ ለእግዚአብሔር ስንት ጸሎት አሳረገች ስንትስ እንባ አፈሰሰች! ይህንን ነገር ሳሰላስል እዚህ ስለምትገኙና በመላው ዓለም ስላሉ እናቶች አስባለሁ፤ ሳትታክቱ ስለልጆቻችሁ ስንት ጸሎት ነው የምታደርጉት፤ ልጆቻችሁን ለእግዚአብሔር ለመስጥት ስንት ጸሎት እንድምታደርጉ አውቃለሁ፤ ቀጥሉበት እርሱ ታላቅ ልብ ስላለው በዚሁ ልብ በር ማንኳኳትን አታቋርጡ፣ በእግዚአብሔር ልብ በር ስለልጆቻችሁ በመጸለይ ዘወትር በእምነት አንኳኩ፣
ቤተ ክርስትያንም እንዲሁ ነው የምታደርገው ምክንያቱም ቤተ ክርስትያን ሁሉን ነገር በእግዚአብሔር እጅ በማኖር አጠቃላይ የልጆችዋን ሁኔታ በጸሎት ለእግዚአብሔር ታቀርባለች፣ በዚሁ የእናት ቤተ ክርስትያን ጸሎት እንተማመን እግዚአብሔር ሳልመልስላት አይቀርምና፣ ዘወትር ባልጠበቅነው ጊዜ እንደሚመልስልን እናውቃለንና፣ እናት ቤተ ክርስትያንም ይህንን ታውቃለች፣ ለዛሬ ከእናንተ ጋር ለማጋራት ያቀድክዋቸው ኃሳቦች እነኒህ ነበሩ፤ በቤተ ክርስትያን አንዲት መልካም እናት እናገኛለን ይህችም እናት በሕይወት ኑⶂአችን መከተል ያለብንን መልካም ጐዳና ታሳያናለች፣ ይህም እናት ዘወትር ት ዕግሥተኛ መሓሪ እና የምትረዳ እናት ሆና ሁሉንም በእግዚአብሔር እጅ ለመተው የምትችል ናት፣ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፣All the contents on this site are copyrighted ©.