2013-09-18 16:18:13

ካቶሊክ ምእመናን ለማሕበራዊ ጥቅም ትጋት ይኑራቸው


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. መስከረም 16 ቀን 2013 ዓ.ም. ካቶሊክ ምእመናን ትጉ ካቶሊክ የሚባለው ከፖለቲካ የሚሸሽ ሳይሆን የበለጠውንና ከፍ ያለ ሚና በመጫወት የሚያስተዳድር በሚገባ ለማስተዳደር ይቻለውም ዘንድ ገዛ እራሱ በበለጠ የሚያሳትፍ መሆን አለበት ያሉትን ሃሳብ በካቶሊክ ምእመናን ብቻ ሳይሆን በፖለቲካው መድረክ ጭምር የውይይት ርእስ ሆኖ ብዙ አስተያየት እየተሰጠበት መሆኑ ሲገለጥ፣ በኢጣሊያ የፖለቲካ ማኅበራዊ ማእከል የፖለቲካና ማኅበራዊ ሥነ ምርምር ኮሚቴ ሊቀ መንበር ዳቪደ ኮቺ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “ፖሊቲክ ሲባለ ማኅበራዊነትን መኖር ማለት ነው፣ ከተማን አገርን መኖር ማለት ነው። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በቀጥታ የመናገር ብቃታቸው አማካይነትም ይኽንን ነው ያሉት፣ ምክንያቱን ፖሊቲካ አይመለከተኝም ሳይሆን ፖለቲካ የማስተዳደር ሥነ ጥበብ ከሆን ተዳዳሪዊ ወይንም ነዋሪው ቀሪ መሆን የለበትም፣ የመጀመሪያ ለመሆን የሚሻ የመጨረሻ ይሆኑ የሚለው ወንጌላዊ ቃል እንዲኖር የሚያነቃቃ ነው። በፖለቲካው ጉዳይ መጠመድ ማለት የመጨረሻ መሆን እጅጌን አጥፎ መረባረብ ሌላውን ማገልገል ማለት ነው። ስለዚህ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ይኸንን ነው ያሳሰቡት።” ብለዋል።
በተለይ ደግሞ ይላሉ ኮቹ፦ “የሚያስተዳድር የሚመራ ሕዝቡን የሚያፈቅርና ትሁት መሆን አለበት በማለት ቅዱስ አባታችን መሪ የሚሆን እነዚህ ሁለት የላቁ እሴቶች የሚያገናዝብ የሚኖር መሆን አለበት ያሉት ሃሳብ፣ እውነት ነው። ሕዝብን የማያፈቅር የሌላው ሃሳብና አስተያየት የማያገንዛብ የማይቀበል የማይወያይ ትህትና የሌለው ከሆን እንዴት የአገር መሪ ወይንም አስተዳዳሪ ለመሆን ይችላልን? ገዛ እራስን ለማፍቀር ተብሎ መሪ አይኮንም። ይኽ በፖለቲካ የሚሳተፉ የካቶሊክ ምእመናን ብቻ የሚመለከት ሳይሆን ሁሉንም የፖሊቲካ አካል ጭምር የሚመለከት ነው። ስለዚህ የሕይወት መሪ ቃል መሆን አለበት” በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.