2013-09-18 16:21:45

ብፁዕ አቡነ ማምበርቲ በለአለ አቀፍ የአቶሚክ ኃይል ምንጭ ተቆታጣሪ ድርጅት


RealAudioMP3 በቪየና ዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኃይል ምንጭ ተቆጣጣሪ ድርጅት ባካሄደው ጠቅላይ ጉባኤ የተሳተፉት የቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነቶች ጉዳይ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ዶመኒክ ማምበርቲ ሰላም በምድር የተሰኘችው የር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ 23ኛ ዓዋዲት መልእክት ዝክረ 50 ዓመት እየተከበረ መሆኑ አስታውሰው፦ “የአቶሚክና ኑክሊየር ኃይል ለወታደራዊ ዓላማ የማዋሉ ጉዳይ ተወግዶ ለሰላማዊ ጉዳይ ማስፈጸሚያ ማዋል” የሚል ሃሳብ የተሰመረበት ንግግር ማሰማታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ወቅቱ የኑክሊየር ጦር መሣሪያ ምርት የሚገታበት ይኽ ምንጭ ለጦር መሣሪያ እንዲውል የሚደረገው ርብርቦሽና የሚፈሰው ጉልበትና ብቃት እንዲሁም ሥነ እውቀት ለመልካም ለሁሉም ሕዝቦች እርባና በሰላም ለመኖር ዓላማ ማዋል ያለው አስፈላጊነት ብፁዕ አቡነ ማምበርቲ ባሰሙት ንግግር ገልጠው፣ ለዚህ 57ኛው ዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኃይል ምንጭ ተቆጣጣሪ ድርጅት ጉባኤ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለጉባኤው ያስተላለፉት የሰላምታ መልእክት ብፁዕነታቸው አቅርበው፦ “የዓለምና የሕዝቦች ጸጥታና ደህንነት ለጦር መሣሪያ በጠቅላላ ለኑክሊያር ጦር መሣሪያ ማስረከብ ጸረ ጸጥታና ደህንነት ነው፣ የኑክሊየር ጦር መሣሪያ የሕይወት ደህንነትና ዋስትና ሊሆን አይችልም። ስለዚህ በኑክሊያር የጦር መሣሪያ ጸጥታና ደህንነት መዋስ ማለት አለ መዋስ ማለት ነው። አለ ምንም ቅድመ ሁኔታ አደገኛ የጦር መሳሪያ ላለ ማምረት የተደረሰው የስምምነት ሰነድ ሁሉም አገሮች እንዲከተሉትና እንዲያከብሩት” ጥሪ አቅርበው፦ “በዓለማችን ያለው የኑክሊየር የጦር መሣሪያ የማርገፍ እቅድ ቀስ በቀስ እየተረጋገጠ ከዚህ አደገኛው ጦር መሣሪያ ነጻ የሆነ ዓለም መገንባት የሁሉ አገሮች ኃላፊነት ነው፣ ይኽ ተኪዶ በዓለማችን ሰብአዊነት የሚያስፋፋ ተግባር ነው” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
በመጨረሻም፦ “በአሁኑ ሰዓት በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱና ቅዱስት መንበር ይኽ ጉዳይ ኣንገብጋቢ መሆኑ እንደምታምንበትና ዓለም ከኑክሊየር ጦር መሳሪያና ከአደገኛው ሕዝብ ረፍራፊው ጦር መሣሪያ ነጻ ለሁሉም ጸጥታና ደህንነት ተብሎም መካከለኛው ምስራቅ ከዚህ አደገኛው የጦር መሣሪያ ነጻ ማድረግ” ያለው አስፈላጊነት ገልጠው፣ የኑክሊያር ጦር መሣሪያ ጉዳይ በተመለከተ ከኢራን ጋር እየተካሄደ ያለው ውይይት ብፁዕነታቸው አስታውሰው፣ ውይይቱ ወደ ፊት እንዳይል የሚፈጠረው መሰናከል ሁሉ በውይይት መንገድ መፈታት አለበት የሚለው የቅድስት መንበር አመለካከት እንዳገለጡ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።







All the contents on this site are copyrighted ©.