2013-09-18 16:23:12

በመካከለኛው ምሥራቅ የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጉባኤ


RealAudioMP3 በመካከለኛው ምስራቅ የሁሉም የላቲን ሥርዓት የሚከተሉት የካቶሊክ አቢያተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ትላትና በሮማ ስብሰባው እንደከፈተ ሲገለጥ፣ የላቲን ሥርዓት ተከታይ ካቶሊክ አቢያተ ክርስቲያን በምስራቅ ክልል የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት አረብ አገሮች ግብጽና ሶማሊያንም ጭምር የሚያጠቃልል ሲሆን፣ የግኑኝነት ማእከላዊ ርእስ የእምነት ዓመት መሠረት ያደረገ እነዚህ ካቶሊክ አቢያተ ክርስቲያን በዚህ በእምነት ዓመት የሚከትሉት የሚፈጽሙት ጅምሮች ላይ ያተኮረ መሆኑ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሳልቫቶረ ሳባቲኖ ገለጡ።
በመካከለኛው ምስራቅ ክርስቲያን ማኅበረሰብ አናሳ የክልሉ ሕዝብ ክፍል መሆኑ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት በእየሩሳሌም የላቲን ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፉአድ ትዋል ገልጠው፣ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ሁኔታ ለማንም የተሰወረ አይደለም ስለዚህ በአንድ የክልሉ አገር ውስጥ የሚከሰተው ውጥረት መላ መካከለኛው ምስራቅ ክልል የሚነካካ ነው። ስለ ሰላም መጸለይ አስፈላጊ መሆኑ ገልጠው፣ የሰላም የውይይት መድረክ ከጦር መሣሪያ ምርጫ አይሎ የሁሉም ፍላጎት እንዲሆን መጸለይና የሰላምና የሕይወት ባህል ማስፋፋት ወሳኝ ነው፣ በዚሁ ረገድ ልክ በሁሉም ሥፍራ እንዳለችው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በምስራቅ አገሮች ክልል የምትገኘውም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የምታምንበት በዚሁ ረግድ አቢይ አገልግሎት የምስተጥበት መሆኗ ገልጠው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ እዚህ ላይ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.