2013-09-18 16:11:41

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ቤተ ክርስቲያን ልጆችዋን ከኢየሱስ ጋር እንዲገናኙ የምትሸኝ ብርቱ እናት ነች


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. መስከረም 17 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሁሌ ጧት አገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት የሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ በመቀጠል ቤተ ክርስቲያን እንደ አንዲት ብርቱ ሴት (እናት) ልጆችዋን በመከላከል ከሙሽራዋ ጋር እንዲገናኙ የምትሸኝ ነች” በሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ የጸና ስብከት ማሰማታቸው የቅዳሴውን ሥነ ሥርዓት የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ገለጡ።
ቅዱስ አባታችን የዕለቱ ወንጌል ኢየሱስ በናይን ከአንዲት መበለት ጋር መገናኘቱ የሚያወሳው ቃል ተንተርሰው፦ “ኢየሱስ ከእኛ ጋር የመናገር ልዩ ብቃት ያለው፣ ስቃያችንን የገዛ እራሱ ለማድረግ ለስቃያችን ቅርብ ነው” ኢየሱስ አንድያ ልጅዋ የሞተባት መበልት ጋር በመገናኘት የስቃይዋ ተካፋይ ብቻ ሳይሆን ራርቶላት ሸክምዋንም ጭምር የእርሱ እንዳደረገ ሲገልጡ፦ “እግዚአብሔር ለሚሰቃዩት ረዳት ነው። በርግጥ መበለቲቱ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ልናመሳስላት እንችላለን፣ ሙሽራዋ ቢለያትም ከእርሱ ጋር ለመገናኘት በታሪክ ጉዙዋን ትቀጥላለች፣ ታማኝ ሙሽራ ነች። በተጨባጭ ሙሽራዋ የለም ሰለዚህ ለብቻዋ ነች፣ ሆኖም ልጆችዋ ከኢየሱስ ጋር እንዲገናኙ የምትሸኝ እናት ነች። እናታችን ቤተ ክርስቲያን ብርቱ ነች። አደጋ ከሆነ ሁሉ በመከላከል ወደ ሙሽራዋ ልጆችዋን የምትሸኝ ነች” ካሉ በኋላ በመጽሐፍ ቅዱስ የሚዘረዘሩትን የመበለቶችን ሁኔታ በመመልከት በተለይ ደግሞ እግዚአብሔርን አንክድም በማለት የደም ሰማዕትነት የተቀበሉት የሰባት ልጆች እናት መበለቷ መቃብያንን በመጥቀስ፦ “ቤተ ክርስቲያን የዚህ አይነቱ ተምሳል ማለትም የመበለትነት አድማስ አላት ለማለት ይቻላል፣ ታማኝ የልጆችዋን ስቃይ የገዛ እራስዋ በማድረግ አብራ የምትሰቃይ የምትጸልይ እናት ነች፣ ልጆችዋን በመንከባከብ ለሙሽራዋ እስከ ምታስረክብበት ቀንና ሰዓት እስከ ሕይወቷ ፍጻሜ ትሸኛለች፣ በመጨረሻ እርሷም ከሙሽራዋ ጋር ትገናኛለች፣ ቤተ ክርስቲያን የሌሎችን ስቃይ የገዛ እራሷ በማድረግ እንባዋንና ጸሎትዋን ለጌታ ታቀርባለች፣ የኢየሱስና የመበልቲቱ ግኑኝነት የሚያረጋግጠው እውነት ነው። ጌታ አብሯት እንዳለና ለብቻዋ እንዳልተዋት በማረጋግጥም እንባዋን እያበሰ አዎ ይኽ ሞቶ የነበረ ልጅሽ አሁን ሕያው ነው የሚል የኢየሱስ ቃል የሚሸኛትና በፍጻሜ የመጨረሻው ሠርግም ይጠባበቃታል” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አስታውቀው፦ “በእኛና በኢየሱስ መካከል የሚከናወነው ውይይትና ግኑኝነት በእኔና በእርሱ መካከልና በሚያናዝዙን ኢየሱስ ይቅር ብሎልሃል ከሚሉን ካህን ጋር ታጥሮ የሚቀር ግኑኝነት አይደለም፣ ስለዚህ ከጌታ መታራቃችን በዚሁ ሶስትአዊ ግኑኝነት ታጥሮ የሚቀር አይደለም፣ ከጌታ ጋር መታረቅ ዳግም ለእናታችን ተረክበናል ማለት ነው ከራሷ ጋር በመገናኘት የሚጠቃለል ነው። ቤተ ክርስቲያን እንደ መበለት ስመለከት፣ ልጆችዋን በብርታት በመከላከል ወደ ጌታ የምታደርስ ነች፣ በዚህች ሰዓት ለዚህች ታማኝ እናት ታማኞች እንድንሆኖ ጌታ ይርዳን” በማለት ያሰሙትን ስብከት እንዳጠቃለሉ አመለክቱ።








All the contents on this site are copyrighted ©.