2013-09-18 16:13:55

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የአሲዚው ሐውጾተ ኖልዎ መርሃ ግብር


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ጥቅምት 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኢጣሊያ ኡምብሪያ ክፍለ ሃገር የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ዘ አሲዚ ዱካ የሚከተል መንፈሳዊ ንግደት እንደሚያከናውኑ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል መግለጫ አስተወቀ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሄሊኮፕተር ከአገረ ቫቲካን የሄሊኮፕተር ማረፊያ ተነስተው በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 07 ሰዓት 45 ደቂቃ በሰራፊኮ ተቋም የስፖርት ሜዳ እንደደረሱ በክልሉ የሚገኙት በተለያየ በሽታ ምክንያት የአካል ስንክልና ባጋጠማቸው በተለያየ አደገኛ በሽታ የተጠቁት ወጣት ዜጎች አቀባበል እንደተደረገላቸው በዚህ መንፈሳዊ ንግደት የመጀመሪያው ቅዱስ ጴጥሮሳዊ መልእክታቸው ለእነዚህ ወጣቶች የሚያስደምጡት ይሆናል፣ ከዚህ በመቀጠል ቅዱስ ዳሚያኖ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ፍራንቸስኮ የስቁል ኢየሱስ ድምጽ ያዳመጠበትን የተለወጠበት ቅዱስ ሥፍራን ጎብኝተው፣ ወደ የአሲዚ ሊቀ ጳጳስ መንበር በመሄድ ሓዋርያዊ ጉብኝት ፈጽመው ቅዱስ ፍራንቸስኮ ሁሉን ትቶ ገዛ እራሱ ለጌታ እንዳስረከበ በአባቱ ፊት ልብስን በማውለቅ ለማረጋገጥ ዕርቃኑ የወጣበት ቤተ እርቃን በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ታሪካዊ ቅዱስ ቤት ጎብኝተ፣ እዚያ በክልሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበር ቅርንጫፍ የሚረዱት በድኽነት ጫንቃ ሥር ለሚኖሩት ሐዋርያዊ ቃል እንዳሰሙ ልክ 11 ሰዓት በቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘ አሲዚ ባሲሊካ አደባባይ ፊት መሥዋዕተ ቅዳሴ ያሳርጋሉ። እዛው በቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበር ለሚረዱት ድኾች በቅድስት ማርያም ዘመላእክት ክልል ባለው የመርጃ ማእከል የሚቀርበው ምሳ አብረው ተቋድሰው እንዳበቁ ከሰዓት በኋላ ልክ 02.30 ቅዱስ ፍራንቸስኮ ለጸሎት ገዛ እራሱ ገለል ያደርግበት የነበረው የኤርሞ ወህኒ ጎብኝተው ለመላ የሰበካው ሕዝብ ሥልጣናዊ ምዕዳናቸውን ለማስደመጥ ወደ ቅዱስ ሩፊኖ ካቴድራል ያመራሉ፣ ከዝህ በመቀጠል በቅድስት ኪያራ ባሲሊካ የቅድስት ኪያራ ቅዱስ አጽም ለመሳለም ግላዊ ግቡኝት ፈጽመው በገዳሙ ከሚገኙት ከየቅድስት ኪያራ መነኩሳት ጋር ከተገናኙ በኋላ በፍራንቸስካውያን መንፈሳዊ ማእከል የጽሞና ጸሎት አሳርገው ከወጣቶች ጋር ተገናኝተው ከወጣቶች ለሚቀርብላቸው ጥያቄ መልስ ሰጥተው ቅዱስ ሥፍራ ዘ ሪቮቶሪዮ ጎብኝተው ልክ በሮማ ሰዓት አቆታጠር ከምሽቱ 08 ሰዓት አገረ ቫቲካን እንደሚደርሱ የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል መግለጫ ያመለክታል።
All the contents on this site are copyrighted ©.