2013-09-09 15:45:32

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ወደ ክርስቶስ ከማይመራ ኢየሱስን ማእከል ከማያደርግ አምልኮና ግልጸት እንጠንቀቅ


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. መስከረም 7 ቀን 2013 ዓ.ም. እንደተለመደው ጧታ በአገረ ቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ ሕንጻ ቤተ ጸሎት በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ “ክርስቲያን አለ ኢየሱስ ከመሆን ፈተና ይቆጠብ፣ አለ ኢየሱስ አምልኮን ብቻ ከሚፈልግ ክርስትና ይጠንቀቅ፣ ወደ ክርስቶስ ከማያደርስ ዘወትር ኢየሱስ ማእከል ከማያደርግ አምልኮ መቆጠብ አለብን” በሚል ጥልቅ ሃሳብ ላይ ያተኮረ ሥልጣናዊ ስብከት ማሰማታቸው የቅዳሴው ሥነ ሥርዓት የተከታተሉ ይቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ገለጡ።
“ኢየሱስ የክርስትናችን ማእከል ነው፣ ኢየሱስ ጌታ ነው ሆኖም እኛ ክርስቲያኖች ይኸንን እውነት ብዙውን ጊዜ የምንረዳው እንደማይመስል ነው፣ ኢየሱስ እንደገለጠውም እርሱ ከጌቶች ውስጥ አንዱ ሳይሆን ብቸኛና ልዩ ጌታ ነው። ፈሪሳውያን የሃይማኖታቸው ማእከል ሥፍር ቁጥር የሌለው ትእዛዝ ሲያደርጉ ይታያል፣ ስለዚህ ኢየሱስ ማእከል ካልተደረገ በምትኩ ሌሎች ነገሮች ማእከል ሆነዋል ማለት ነው። ፈሪሳውያን ይኸንን አድርግ ይኸንን አታድርግ በሚሉት ስፍር ቁጥር በሌላቸው ትእዛዞች ላይ ሃይማኖታቸውን ያኖራሉ፣ ትእዛዛት ማእከል ያደርጋሉ፣ ግዴታዊ ትእዛዝ ይሆናል፣ ከኢየሱስ የሚመጣ ትእዛዝ እሙን ነው። ስለዚህ ከክርስቶስ ጋር በእርሱ ኃይል በመተማመን እንፈጽመዋለን” ካሉ በኋላ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ አያይዘው.፦ “አለ ክርስቶስ የሚኖር ክርስትና አምልኮ ብቻ ሆኖ ነው የሚቀረው፣ ወደ ኢየሱስ የሚመራ አምልኮ እውነተኛ አምልኮ ነው። ብዙዎች የግል ግልጸቶችን የሚከተሉ ክርስትናን አለ ክርስቶስ የሚኖሩ ገዛ እራሳቸው ክርስቲያን በማለት የሚጠሩ ማኅበረ ክርስቲያን ብዙ ናቸው አሉም፣ ሆኖም ግን ግልጸት በአዲስ ኪዳን ተጠቃለዋል፣ ስለዚህ ሌላ የግል ግልጸት መከተል ሳይሆን ወንጌል መኖር ነው አስፈላጊነቱ” እንዳሉ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አስታወቁ።
“ክርስቶስን ማእከል ያደረገ ክርስትና መቀበል አለ ክርስቶስ ክርስቲያን ላለ መሆን ምን ማድረግ ይኖርብኛል? ክርስቶስ ማእከል ያደረገ ክርስትና የመኖር ምልክቱ ምንድር ነው? ከኢየሱስ የሚመጣ ወደ ኢየሱስ የሚመራ ክርስትና የእውነተኛ ክርስትና ምልክት ነው። ኢየሱስ ማእከል ነው። እርሱ እንዳለውም ጌታ እርሱ ብቻ ነው። ይኽ እውነት ወደ ኢየሱስ የሚመራ ወደ ኢየሱስ የሚያደርስ ነው። ትእዛዙም ይኽ ነው። ከኢየሱስ የማይመጣ ወደ እርሱ የማያደርስ ሁሉ እጅግ አደገኛ ነው” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አያይዘው፦ “ኢየሱስን መስገድና ማምለክ ካቃተህ የጎደለህ ነገር አለ ማለት ነው። ስለዚህ ኢየሱስ ያለውም ከኢየሱስ የሚመጣ ማድረግ ነው ይኽም እርሱ የሕይወት ማእከል ማድረግ ብቻ ነው እውነተኛ ስግደትና አምልኮ፣ እርሱ ባመለከተውና ገዛ ኣራሱ በሆነው እውነትና መንገድ መጓዝ። እውነትና መንገድ እርሱ ነው። ስለዚህ እውነተኛው ክርስትና በእርሱ መጓዝና መኖር እርሱን ማእከል ማድረግ ማለት ነው” ብለው ያሰሙትን ሥልጣናዊ ስብከት እንዳጠቃለሉ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.