2013-09-09 15:40:41

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ እነሆኝ እንዳልከው ይሁንልኝ ማርያማዊ መልስ የሁላችን ይሁን


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. መስከረም 8 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እኩለ ቀን ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ እንደተለመደው በሚሰጡት ስልጣናዊ አስተንትኖ በዕለቱ የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ያከበረችው በምሥራቅ አቢያተ ክርስቲያን እጅግ ክቡር የሆነው በዓለ ልደታ ለማርያም መሆኑ ጠቅሰው፣ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡት ከውጭና ከውስጥ ለመጡት በብዙ ሺሕ ለሚገመቱት ምእመናን እንዲሁም የምሥራቅ ሥርዓት ለምትከተለው የካቶሊክና የኦርቶዶክስ አቢያተ ክርስቲያን ገዳማውያም ብፁዓን ጳጳሳት በጠቅላላ ለሁሉም ማኅበረ ክርስቲያን ሰላምታን አቅርበው እነሆኝ እንዳልከው ይሁንልኝ በማለት ማርያም ለእግዚአብሔር ያቀረበቸው የፍጹም ተአዝዞ ቃል የእያንዳንዳችን መልስ ሊሆን እንደሚገባው ማሳሰባቸው ሲገለጥ፣ በዚያኑ ዕለት በኢጣሊያ ሎሬቶ ቅድስት የናዝሬቲቱ ቤት የታቀበበት የቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ሥፍራ ልዩ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጆቫኒ ቶኑቺ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በዓለ ልደታ ለማርያም ከእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ጋር ያለው ጥልቅ ትሥሥር እርሱም ጌታ ከማሪያም ጋር በመገናኘት የማዳን እቅዱን ያስጀመረበትን ቅዱስ ሁነት የምናከብርበት ዕለት መሆኑ አብራርተው፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታህሳስ 8 የቅድስት ድንግል ማርያም አለ አዳም ኃጢአት መጸነስ ታከብራለች፣ ጽንሰታ ለማርያም በቤተ ክርስቲያን አቢይ በዓል ነው። ይኽ በዓል ከማዳን እቅድ ጋር የተቆራኘ መሆኑ ገልጠው፣ ቅድስት ድንግል ማርያም ለእግዚአብሔር ልጅ ትስብእት እሺ በማለት ትስብእቱ በማሕጸንዋ አድሮ ይፈጸምም ዘንድ ፍጹምና አለ ምንም ቅድመ ሁነት እሺ እነሆኝ ያአንተ አገልጋይ ነኝ እንዳልከው ይሁንልኝ በማለት ገዛ እራሷን ለጌታ እቅድ በማዋል፣ ቃሉን በመኖር እርሱ አንዳላችሁ አድርጉም በማለትም የቤተ ክርስቲያንና የክርስቲያን የሕይወት መርሃ ግብር ቃሉን ማዳመጥና እግብር ላይ ማዋል የሚል መሆኑ በማረጋገጥ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ መቀበል እርሱ ያለውን ሁሉ ማድረግ የክርስቲያን ጥሪ መሆኑ በቃልና ሕይወት ምስክር ነች በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.