2013-09-09 15:56:37

ናይጀሪያ፦ ጸረ ቦኮ ሃራም ጥቃት


RealAudioMP3 በናይጀሪያ የመንግሥት የመከላከያ ኃይል አባላት ገዛ እራሱ ቦኮ ሃራም በማለት የሰየመው አክራሪው የምስልምና ሃይማኖት ተከታይ በናይጀሪያ በተለያየ ወቅትና በተደጋጋሚ ለተሰነዘሩት የሽበራ ጥቃት ተጠያቂ መሆኑ የሚነገርለት ታጣቂው የአሽበራ ኃይል ለማጥፋት የተያያዘው ጸረ የሽበራ ኃይሎች ጥቃት አሁንም እየቀጠለ መሆኑ ሲነገር፣ በቅርቡ የመንግሥት የመከላከያ ኃይል አባላት በሰነዘሩት ጥቃት ሳቢያ ወደ 50 የሚገመቱት የሽበራው ቡድን አባላት ለሞት መዳረጋቸው ሲገለጥ፣ የሽበራው ኃይል ባለፉት ቀናት በአገሪቱ ማኢዱጉሪ በተሰየመው አካባቢ አቅራቢያ በሚግኘው ክልል በሰነዘሩት የሽበራ ጥቃት ሳቢያ 20 ሰዎች ለሞት አደጋ ማጋለጣቸው የአገሪቱ የዜና ምንጮች ሲያመለክቱ፣ ከባለፈው ግንቦት ወር ጀምሮ የናይጀሪያ መንግሥት የተጠንቀቅ ያስቸኳይ አዋጅ በመደንገግ ጸረ ቦኮ ሃራም በአየር ኃይል የተሸኘ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ጥቃት እያካሄደ መሆኑ ሲነገር፣ ወታደራዊው ጥቃት በአገሪቱ ሰሜናዊ ክልል በተለይ ደግሞ በቦርኖ ግዛት እጅግ ሰፊ ሲሆን ባለፉት በመጨረሻ ወራት በዚሁ ግዛት የተሰማራው የአገሪቱ የመከላከያ ኃይል ቁጥር ብዛት ከፍ እንዲል መደረጉም ይነገራል።
All the contents on this site are copyrighted ©.