2013-09-06 14:59:57

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ የግኑኝነት ባህል ቅድመ ፍርድና መከፋፈልን ያስወግዳል


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. መስከረም 5 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሶሪያ ማላንካረሰ ሥርዓት ለምትከተለው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ሞራን ባሰሊዮስ ማርቶማ ጳውሎስ ዳግማዊ በቅድስት መንበር ተቀብለው ማነጋገራቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሰርጆ ቸንቶፋንቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ሲቻል፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በተካሄደው ግኑኝነት በጋራ ወደ ተሟላ ውህደት ለመድረስ በሚደግፈው ጎዳና በጋራ ለመጓዝ የግኑኝነትና የውይይት ባህል መሠረት መሆኑ መግለጣቸው ያስታወቁት ልኡክ ጋዜጠኛ ቸንቶፋንቲ አያይዘውም፣ የሶሪያ ማላንካረሰ ሥርዓት የምትከተለው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ ቶማስ በሰጠው ቀጥተኛ የጌታችን ኢየሱስ ትንሳኤ የእምነት ምስክርነትና የደም ሰምዕትነት ላይ የጸናች መሆንዋ የህንድ ታሪክ የሚሰጠው ምስክርነት በእውነቱ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የጸናው እምነት አቢያተ ክርስቲያንን የሚያዋኅድ አንድ የሚያደርግ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ገልጠው፣ ምንም’ኳ ሁለቱ አቢያተ ክርስትያን አብረው በአንድ መሥዋዕተ ቅዳሴ መሠረት በጌታችን ቅዱስ ሥጋውና ደሙ ለመካፈል ባይችሉም በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ላይ የጸና እምነታቸው ለውህደት እንደሚመራቸው እምነት አለኝ እንዳሉ ገልጠዋል።
በካቶሊካዊትና የሶሪያ ማላንካረሰ ሥርዓት የምትከተለው በህንድ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መካከል የዛሬ 30 ዓመት በፊት የተጀመረው ለውህደት ያቀናው የጋራው ውይይት ወንድማዊ ፍቅር ቀጥሎም ቲዮሎጊያ ውይይትና ባጸኑት የጋራው ድርገት ከዚህ አልፎም እ.ኤ.አ. በ 1990 ዓ.ም. በበዓለ ጰራቅሊጦስ የጋራ ስምምነት ያረጋገጠ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባካሄዱት ግኑኝነት የጋራው ውይይት ውጤት ገልጠው ወቅታዊው ሁነት ግምት በመስጠት ሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን የሚታየው ማኅበራዊና ሃይማኖታዊ ተጋርጦ ለመወጣት የሚያስችል አዲስ የውይይት ቅርጽ ያለው አስፈላጊነት እንዳሰመርበት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ቸንቶፋንቲ አስታውቀዋል።
በተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን መካከል የሚካሄደው ሃይማኖታዊ የጋራው ውይይት ያለው አስፈላጊነት ሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን በጋራው ውይይት ያረጋገጡበት ስምምነት የሚመሰክረውና ቀስ በቀስ የነበረው ቅድመ ፍርድ እንዲወገድ ማድረጉንም ቅዱስ አባታችን አስታውሰው ስለዚህ ቅድመ ፍርድና መከፋፈልን ለማስወገድ የግኑኝነት ባህል ወሳኝ ነው እንዳሉ የገለጡት ልኡክ ጋዜጠኛ ቸንቶፋንቲ፣ ሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን በጋራ የመግባባትና የውህደት ባህል በማስፋፋት ረገድ ተግተው እንዲጠመዱም አሳስበው በእውነት የውህደት ጉዞ ዘገምተኛ የሚያደርገው ሰብአዊ ድካምና ኃጢአት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የታለመው ውኅደት የሚያዘገይ ነውና የመንፈስ ቅዱስ ጸጋና ሥጦታ የሆነው ይኽ ውህደት እንዲረጋገጥ መንፈስ ቅዱስ ለእግራችን ብርሃን በመስጠት በውህደት መንገድ እንዲመራን ጸሎት መሠረት ነው እንዳሉ አስታውቀዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በመጨረሻም መንፈስ ቅዱስ ወደ ስምምነትና እርቅ ምራን በዚህ የስምምነትና የእርቅ መንገድ እንገኝም ዘንድ ምራን በማለት ጸልየው አብረን በዚህ መንገድና በመጨረሻ ሁሉም አንድ እንዲሆኑ በሚያደርገው እግዚአብሔር ላይ ያለን እምነት በመኖር እንጓዝ ካሉ በኋላ የቅዱስ ጴጥሮስና የቅዱስ ቶማስ ጥበቃን ተመጽነው ግኑንነት እንዳጠቃለሉ ቸንቶፋንቲ ገለጡ።







All the contents on this site are copyrighted ©.