2013-09-06 15:02:10

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ ወንጌል ማእከል ያደረገ ሕይወት የኅዳሴ መሠረት ነው


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ 21ኛው ጠቅላይ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ለሚገኘው ለቀርመለሳውያን ካህናት ማኅበር መልእክት ማስተላለፋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ ካስተላለፉት ዘገባ ለመረዳት ሲቻል፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በዚህ ለማኅበሩ ጠቅላይ አለቃ አባ ፈርናንዶ ሚላን ሮመራል ባስተላለፉት መልእክት የክርስቶስ ተከታይነት ጸሎትና ወንገላዊ ልኡክነት የቤተ ክርስቲያን መሠረት መሆኑና ለቤተ ክርስቲያንና ለመንፈሳዊ ገዳማዊ ማኅበሮች ኅዳሴ መሠረት ወንጌል ማእከል ያደረገ ሕይወት መሆኑ እንዳሰመሩበት ገልጠዋል።
የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ክርስቶስን ወደ ዓለም ሁሉ ማድረስ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባስተላለፉት መልእክት አስታውሰው፣ በቀርመለሳውያን ማኅበር ይኽ ተልእኮ የኢየሱስ ተከታይነትና ሰቂለ ኅሊና ማለትም አስተንታኝ ሕይወት በመኖር የሚመሰከር ብሎም የተስፋ ነቢያት ለመሆን የተጠሩ ናቸው እንዳሉ ፒሮ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
በዚህ በአሁኑ ወቅት መደናገር በተሞላው ዓለም የተዘነጋው የሰቂለ ኅሊና አስተንታኝ የመናንያን ሕይወት ዳግም ለመመስከር፣ ጸሎት ተጨባጭ መንገድ የሚያመለክት፣ ለእግዚአብሔር ምሥጢር ሁለመናን ክፍት ለማድረግ የሚያበቃ ጸጋ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ገልጠው፣ የሰዓታት ጸሎት ዕለታዊ ሕይወት በጌታ ዓይን እይታና በቃሉም ጭምር ለመኖር የሚመራ ነው እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ አያይዘውም፣ የቀርመልሳውያን ካህናት ሰባክያን ቃል ወንጌል እንዲዘሩ የተጠሩ ናቸው ይኽ ልኡካነ ወንጌላዊነት ከወንጌላዊ ሕይወት የሚመነጭ መሆኑ ቅዱስ አባታችን አብራርተው ቃለ ወንጌል ብዙውን ጊዜ ተቀባይነት የማያገኝ በዓመጽና በጥላቻም እምቢ ሲባል የሚታይ ነው ሆኖም ግን ለወንጌላዊ ልኡክነት በሚጠራው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድጋፍና ጽናት በቆራጥነት በሙሉ መስዋዕትነት የሚፈጸም መሆኑ ገልጠው ቀረመለሳውያን በሚኖሩት እምነትና በተቀበሉት ገዳማዊ ሕይወት የፍቅር የተሰፋ መስካሪያን ጥሪ የተቀበሉ ናቸው ብለው ፍቅርና ተስፋ በዓለም የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ የሚያድስ ነው እንዳሉ አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.