2013-09-06 14:51:35

ብፁዕ አቡነ ማምበርቲ፦ በሙሉ ኃይል ለሰላም ውይይት መትጋት


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. መስከረም 4 ቀን 2013 ዓ.ም. የቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዶመኒክ ማምበርቲ በቅድስት መንበር ለተለያዩ አገሮች ልኡካነ መንግሥታት ተቀብለው እ.ኤ.አ. መስከረም 7 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ስለ ሶሪያ ሰላም ኩላዊት ቤተ ክርስቲያንና መልካም ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ሁሉ ጾምና ጸሎት እንዲያሳርጉ ያቀረቡት ኵላዊ ጥሪ ዙሪያና የጥሪው መሠረታዊ ሃሳብ ማብራራታቸው የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ በማያያዝ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከሶሪያው ርእሰ ብሔር አል አሳድ ጋር በስልክ ተገናኝተው ተወይዩ ተብሎ የተሰራጨው ዜና የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ጉዳይ ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ጉዳይ ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ ለተገኙት ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስተባብለዋል።
ብፁዕ አቡነ ማምበርቲ እልባት ያጣው የሶሪያ ቀውስ ጉዳይ በተመለከተ የቅድስት መንበር አቋም ምን እንደሚመስል ሲያብራሩ፣ በቅድሚያ ማንኛውም ዓይነት አመጽ እንዲቆምና ከዚህ በመቀጠልም በውይይት ላይ የጸና እውነተኛው መፍትሔ ማፈላለግ እንዲሁም የሰላም ውይይት ቀጥሎም አገራዊ እርቅና የሶሪያ ብሔራዊ አድነት ማቀብ የሚል መሆኑ ማብራራታቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ጉዳይ ተጠሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀው በጠቅላላ 71 በቅድስት መንበር የሚገኙት የተለያዩ አገሮች ለኡካን መንግሥታት በበኩላቸው የሶሪያ ሉአላዊነት በአገሪቱ የሚገኙት ንኡሳን ጎሳዎችና ኃይማኖቶች እንዲከበር የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ ውይይት ብሎም የሰላም ባህል ማነቃቃት የሚል በመልእክቱ ላይ የሰፈረው ሃሳብ ያለው አስፈላጊነት መግለጣቸው አባ ሎምባርዲ ጠቅሰው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. መስከረም 7 ቀን 2013 ዓ.ም. ስለ ሶሪያ ሰላም ያወጁት የጸሎትና ጾም ቀን ካቶሊካውያን ምእመናንና መልካም ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ሁሉ የሚመለከት ሲሆን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሚሳተፉበት የጾምና ጸሎት መንፈሳዊ መርሃ ግብር እንደሚከናወንም ብፁዕ አቡነ ማምበርቲ መግለጣቸው አባ ሎምባርዲ አመልክተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.