2013-09-04 18:43:56

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ፣


ውድ ወንድሞችና እኅቶች! መልካም ቀን ይሁላችሁ! ከነሓሴ ወር ዕረፍት በኋላ ዛሬ ሳምንታዊ የዕልተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ እንደገና ለመጀመር ባለፈው ሓምሌ ወር በብራዚል ለአለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ስላደረግሁት ጉዞ ለመናገር እሻለሁ፣ ከአንድ ወር በላይ አልፈዋል ሆኖም ግን ይህንን ፍጻሜ እንደገና መመለት አስፈላጊ ሆኖ ስለታየኝ እንዲሁም የጊዜው ርቀት ትርጉሙን ጠለቅ ባለ መንገድ ለመረዳት ያስችለናል፣
ከሁሉም አስቀድሜ እግዚአብሔር አመሰግናለሁ! ምክንያቱም በአሳቢነቱ ሁሉን የመራ እሱ ነውና፣ ከደቡብ አመሪካ ለመጣሁት ለኔ፤ ይህ አጋጣሚ ታላቅ ስጦታ ነበር፣ ለዚህም የአፓራሲዳ እመቤታችን ድንግል ማርያምን በዚህ ጉዞ ስለሸኘችን አመሰግናታለሁ፣ ለዚህም በብራዚሉ ታላቅ መካነ ንግደት መንፈሳዊ ንግደቴን በተከበረው ሁሌ በአለም አቀፍ የወጣቶች ቀን መድረክ በሚቀመጠው ስእልዋ ፈጽምያለሁ፣ የአፓራሲዳ እመቤታችን ለብራዚል ቤተክርስትያን ታሪክ እጅግ አስፈላጊ በመሆንዋ በዚሁ መንፈሳዊ ንግደት እጅግ ደስ አለኝ፤ ለዚህ ብቻ ሳይሆን ለመላው የደቡብ አሜሪካ ሕዝብ ባለፉት ግዝያት የላቲን አመሪካና የካራይቢ ጳጳሳትም ከልሂቅ ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ጋር አጠቃላይ ጉባኤቸውን በዚሁ ቦታ አድርገው ነበር፣ ስለዚህ አፓረሲዳ በዓለማችን ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን በአብላጫ በምትገኝበት የብራዚል ቦታ ለሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮ እጅግ አስፈላጊ ቦታ አለው፣
ምንም እንኳ ድሮ የፈጸምኩት ቢሆን ለጠቅላላው የላቲን አመሪካ የቤተ ክርስትያንና የቤተ መንግሥት ኃላፊዎች እንዲሁም በበጎ ፈቃዳቸው ነጻ አገልግሎት ለሰጡ ለጸጥታ ኃላፊዎች የሪዮ ዲ ጃነሮ ቍምስናዎች እና ለሌሎች የብራዚል ቍምስናዎች ነጋድያኑን በታላቅ ወንድማማችነት በመቀበላቸው ምስጋናየን እንደገና ለመድገም እወዳለሁ፣ ለመሆኑ ማወቅ ያለብን የብራዚል ቤተሰቦችና ቍምስናዎች ያደረጉት መስተንግዶ የዘንድሮው አለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ከፍተና ምግባረ ሠናይ እንደነበር ለማስታወስ እወዳለሁ፣ እውነትም ብራዚላውያን በጎ ሕዝብ ናቸው! ጎበዞች! ታላቅ ልብ ያላቸው ሕዝብ! መንፈሳዊ ንግደት ሁሌ ችግር ይፈጥራል የእንግዳ አቀባበል ግን እነዚህን ችግሮች ለማቃለል ይረዳል ስለሆነም የመተዋወቅና የጓደኝነት አጋጣሚ አድርጎ አቸዋል፣ እንዲህ ባለ አጋጣሚ ለሁል ጊዜ የሚቀሩ መተሳሰሮች ይፈጠራሉ ከሁሉ በላይ ደግሞ በጸሎት የሚደረጉ መተሳሰሮች ሆነው ይቀራሉ፣ በዚህ ዓይነት መተሳሰርም በመላው ዓለም ያለች ቤተ ክርስትያን ታድጋለች፣ ይህ ዓይነት መታሳሰር በኢይሱስ ክርስቶስ የሚገኝ ጓደኝነት ሆነ እያጠመደህ ነጻነት የሚሰጥህ መተሳሰር ነው፣ ስለዚህ በብራዚል ባደረግሁት ጉዞ ከፍተኛውን ቦታ ይዞ የሚገኘው እንግዳን የመቀበል መንፈስ ነው፣ እንግዳን መቀበል፣ !
ሌላው አጠቃላይ ቃል ደግሞ በዓል ነው፣ አለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ዘወትር በዓል ነው ምክንያንቱም አንድ ከተማ በወጣት ልጃገረጆችና ወንዶች ስትሞላና በከትማውም የመላው ዓለም ባዲራዎች ይዘው ሲዘዋወሩ ሰላምታ ሲለዋወጡ ሲተቃቀፉ ይህ በዓል ነው፣ ለአማኞች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም የሚሆን ምልክት ነው፣ ሆኖም ግን ሌላው ታላቅ በዓል አለ ይህም የእምነት በዓል ነው፣ በዚህ በዓል በአንድነት ጌታን ለማክበር ዜማዎችና መዝሙሮች ይደረጋሉ! ቃለ እግዚአብሔር ይሰማል! ይህኑን ለማስተንተንና ጌታን በቅዱስ ቍርባን ለማመልክ በጸጥታ ይጠበቃል፣ በዚህም ዓለም አቀፉ የወጣቶች ቀን ከፍተኛውን ጠርዝ ይደርሳል የዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ዋና ዓላማን መንፈሳዊ ንግደትም ለዚህ ነው፣ መላው ዓለም የተከታተለው የቅዳሜ ምሽት ጸጥታ የሰፈነበት አስተንትኖና የተከተለው ቅዳሴም በዚህ መንፈስ ነበር፣ እየውላችሁ ታላቁ በዓል የምነትና የወንድማማችነት በዓል ይህ ነው፤ በዚህ መንገድ የሚጀምር በዓል መጨረሻ የለውም፣ የዚህ ዓይነት በዓል ግን ከጌታ ጋር ሲሆኑ ብቻ ነው! አለጌታ ፍቅር ለሰው ልጅ እውነተኛ በዓል ሊገኝ አይችልም፣
እንግዳ መቀበልና በበዓሉ መደሰት ብለናል ሆኖም ግን ሶስተኛና ዋና ነገር ሊረሳ ይችላል፣ ይህም ተልእኮ ነው፣ ለዚህም የዘንድሮው ዓለም አቀፉ የወጣቶች ቀን እንደመሪ ቃል የወሰደው “ወደ መላው ዓለም ሂዱና ሁላቸውንም ደቀ መዛሙርትየ አድርጋዋቸው” የሚለውን ቃለ ወንጌል ታጥቆ የተነሣው፣ ይህ የሰማነው የኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ለእያንዳንዳችን የሰጠን ተል እኮ ነው፣ ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ሂዱ ከገዛ ራሳችሁ ውጡ ከሚዘጋችሁ ነገር ሁሉ ተላቀቁና የወንጌል ብርሃንና ፍቅር ለሁሉም እስከ ዓለም ዳርቻ አዳርሱ አላቸው፣ ይህንን የኢየሱስ ተል እኮ ነው በዘንድሮ አለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በኮፓካፓባና ባሕር ሰላጤ ለይቶ ለማየት እስከማንችልበት መልተው ለነበሩ ለእያንዳንዱ ወጣትና ለሁሉም ምእመን ያስረከብኩት ተልእኮ፤ ይህ የባህር ጠረፍ ትእምርታዊ ቦታ ነበር ምክንያቱም የገሊላ ሃይቅ ጠረፍ እንድናስታውስ አድርጎናልና፣ አዎ ዛሬም ጌታ “ሂዱ” የሚለውን ቃል በኅልናችን እያስተጋባ ነውና ሆኖም ግን “እስከ መጨረሻ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ” የሚል ቃልም ይጨምርልናል፣ ይህ መሠረታዊ ነገር እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ስንሆን ብቻ ነው ወንጌልን ለመስበክ የምንችለው፣ በወንጌለ ዮሓንስ 15፡5 እንደሚያስታውሰን አለእርሱ ምንም ማድረግ አንችልም፣ ከእርሱ ጋር ሆነን ግን ብዙ ለማድረግ እንችላለን፣ እንዲያው አንድ ልጅ ወይንም አንዲት ልጃገረድ በዓለማችን ፊት ምንም ዋጋ የሌላቸው የሚመስሉ በእግዚአብሒር ፊት ግን የእግዚአብሔር መንግስት ሐዋርያት ናቸው፣ እንዲያው ለዓለማችን አንድ ተስፋ ናቸው፣ ለሁሉም ወጣቶች እንደገና በኃይለ ቃል አንድ ነገር ለመጠየቅ እፈልጋለሁ፣ ለመሆኑ ዛሬ በዚሁ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ወጣቶች አሉን! አዎ አሉ! ስለዚህ ለእናንተና ለሁላቸው ወጣቶች ለመጠየቅ የምፈልገው “ለእግዚአብሄር ተስፋ ለመሆን ትፈልጋላችሁን! እናንተን ነው ወጣቶች ተስፋ ለመሆን ትፈልጋላችሁን! ብለው ይጠይቃሉና ወጣቶችም አዎ ብለው ይመልሳሉ፣ የክርስቶስን ፍቅር የሚቀበል የወጣት ልብ ወደር የሌለው ኃይል ነው ወደ ሌሎች ተስፋ ይለወጣል! ሆኖም ግን እንንተ ወጣቶች ወንዶችና ሴቶች ሁላችሁ ወጣቶች አስቀድማችሁ እናንተ መለወጥ አለባችሁ! ወደ ተስፋ መለወጥ አለባችሁ! የእናንተው ሥራ ይህ ነው፣ ለሁሉም ተስፋ ለመሆን ትፈልጋላችሁን! በሪዮ ዲ ጃነሮ ከሙታን ተለይቶ የተነሣውን ክርስቶስ ስላገኑት ወጣቶች እንሰብ! እነዚህ ወጣቶች የክርስቶስን ፍቅር በየቀኑ በሕይወታቸው እንደሚኖሩትን ለሌሎች እንደሚያዳርሱት እንሰብ፣ በጋዜጦች ተለጥፈው እንዲቀሩ ብቻ አይደልም ምክንያቱም ዓመስ አይፈጽሙምና! ዕንቅፋቶች አይደርጉም ስለዚህ ለዜና የሚበቃ ነገር የላቸውም፣ ሆኖም ግን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድ ሆነው የቀሩ እንደሆነ መንግሥቱን ያንጻሉ፩ ወንድማማችነት ያንሳሉ! መረዳዳት ያነግሳሉ! የምሕረት ስራ ያዳብራሉ፣ ዓለምን የበለጠና የተሻለ ለማድረግ ብርት ኃይል አላቸው! ሊለውጡትም ይችላሉ! አሁን ብዚሁ አደባባይ ለሚገኙ ወጣት ልጃገረዶችና ወንዶች ይህንን ትግል ለማጋፈጥ ብርታት አላችሁ ወይ ብየ ለመጠየቅ እወዳለሁ! ትንሽ ነው የሰማሁት! ብርታቱ አላችሁ ወይ! ይህንን የፍቅርና የምሕረት ኃይል እንድትሆኑ እርስ በእርሳችሁ ተረዳዱ!
ውዶቼ የአለም አቀፉ የወጣቶች ቀን ተመኵሮ የታሪክ ታላቁ እውነተኛ ዜና ያስታውሰናል፣ ይህም መልካሙ ዜና የሆነው ምንም እንኳ በጋዜጦችና በተለቪዥን ብዙ ባይነገረለትም የደህንነት ዜና ነው! እጅግ በሚያፈቅረንና በእያንዳንዳችን ጐን እንዲሆንና እንዲያድነን ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስን በሚልክልን አባታችን በሆነ በእግዚአብሔር የተፈቀርን ነን፣ እንዲያድነና ኃጢአቶቻችንን ይቅር እንዲለን ኢየሱስን ላከልን ምክንያቱ እርሱ ሁሉ ጊዜ ይቅር ባይ ነውና፣ ርህሩኅና መሓሪ ስለሆነ ይቅር ይለናል፣ አስታውሱ እንግዳ መቀበል በዓልና ተል እኮ፣ ሶስት ቃላት ብቻ እንግዳ መቀበል በዓልና ተል እኮ፣ እነኚህ ሶስት ቃላት በሪዮ ዲ ጃነሮ የሆነ አለም አቀፍ የወጣቶች ቀን መስታወሻ ሆነው ብቻ እንዳይቀሩ ነገር ግን የሕይወታችንና የማኅበረሰባችን ሕይወት አንቀሳቃሽ ኃይል እንዲሆኑ አደራ፣








All the contents on this site are copyrighted ©.