2013-09-03 10:43:32

አዲስ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ሆነው ተሹመዋል፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ባለፈው ቅዳሜ ለረዥም ዓመታት የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ሆነው ያገለገሉ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዝዮ በርቶነ በሕገ ቀኖና ቍ.354 መሠረት ሥልጣናቸውን የመልቀቅ ጥያቄ ተቀብለዋል፤ ነገር ግን ገና እስከ ፊታችን ጥቅምት 15 ቀን 2013 ዓም ሥራቸውን እንዲቀጥሉ እንደጠየቅዋቸው ከቅድስት መንበር የወጣ ዜና አመልክተዋል፣
ቅዱስነታቸው ለዚሁ ታላቅ የቅድስት መንበር ኃላፊነት ብፁዕነታቸውን የሚተኩ እስካሁን የቨንዝወላ የቅዱስነታቸው እንደራሴ ማለት ኑንስዮ አፖቶሊኮ ሆነው እያገለገሉ ላሉ ብፁዕ አቡነ ፕየትሮ ፓሮሊን እንደሾሙና እፊታችን ጥቅምት 15 ቀን 2013 ዓም የቅድስት መንበር የዋና ጸሓፊ ስልጣን እንደሚረከቡም ተመልክተዋል፣
ከብዙ አገልግሎት በኋላ ሥልጣናቸውን ለሚያስረክቡ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዝዮ በርቶነን ለማመስገንና አዲሱን እጮኛ ለቅድስት መንበር ለማሳወቅ ቅዱስነታቸው እፊታቻን ባሉ ሳምንታት የቅድስት መንበር ኃላፊዎችን ይሰብስባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ከዚህ ጋር ተያይዞ የወጣ ዜና አመልክተዋል፣
አዲሱ ተሰያሚ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፕየትሮ ፓሮሊን ኢጣልያዊ ሆነው እ.አ.አ በ1955 በቪቸንሳ ሃገርስብከት የተወለዱና በ1980 ዓም ክህነት የተቀበሉ ሲሆን ለሁለት ዓመታት እንደምክትል ቆሞስ ካገለገሉ በኋላ በሮም ለከፍተኛ ትምህርት ተለከው በ1986 ዓም በሕገ ቆኖና ዶክተርይት አግኝተዋል፣ ከሓምሌ 1986 ዓም ጀምረው በቅድስት መንበር የዲፕሎማሲ አገልግሎት በተለያዩ ደረጃዎች አገልግለዋል፣
All the contents on this site are copyrighted ©.