2013-09-03 10:20:27

ጦርነት በፍጹም መከሰት የለበትም! ጦርነት ፈጽሞ መገታት አለበት!


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሲርያና በመላው ዓለም ሰላም እንዲወርድ የአንድ ቀን ጾምና ጸሎት አውጀዋል፣ ዕለቱም ፊታችን ቅዳሜ እ.አ.አ መስከረም 7 ቀን 2013 ዓም ነው፣ RealAudioMP3
አብዛኛውን ጊዜ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ አለበለዚያ በሚገኙበት ቦታ ዘወትር እሁድ እኩለ ቀን ላይ እንደሚያደርጉት ቅዱስነታቸው ትናንትና በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባ አለወትሮዋቸው እጅግ ባዘነ ድምጽ በታላቅ ጩኸት ጦርነት ይቁም ሲሉ በጦርነት ተተራምሳ በምትገኘው በሲርያ እና በተለያዩ የግጭት ቦታዎች ላይ የሚካሄደው የሰው ልጅ እልቂት እጅግ እንዳሳዘናቸውና በጥልቅ እንዳቈሰላቸው ገልጠዋል፣ ጌታ እንዳለው የዚህ ዓይነት የሰው ልጅ ጭካኔ በጾምና በጸሎት እንዲወገድ ፊታችን ቅዳሜ ሁሉ በያለበት በተለይ ክርስትያኖች እንዲሁም የሌሎች ሃይማኖት ተከታዮች እምነት የሌላቸው አረሜንም ሳይቀሩ ጾምና ጸሎት እንዲያደርጉ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ደግሞ ከምሽቱ አንድ ሰዓት እስከ እኩለ ሌሊት አብረው እንደሚጾሙና እንደሚጸልዩ ተመልክተዋል፣
“ጦርነት ፈጽሞ መገታት አለበት! ጦርነት በፍጹም መከሰት የለበትም! ሰላም ሊዳበርና ሊጠበቅ ያለበት እጅግ የከበረ ስጦታ ነው፣ በየዕለቱ እየተከፋው ከሁሉም የምድር ዳርቻ የሚሰማው የሰላም መጣራት ከሁሉ ሕዝብና ከእያንዳንዱ ልብ በአጠቃላይ ከታላቁ አንድያ ቤተሰብ ማለትም ከሰው ልጆች ሁሉ እየተሰማ ነው፣ ይህንን አሰቃቂ ሁኔታ በልዩ ስቃይና አሳቢነት አሳልፈዋለሁ፣ በዚችው ምድራችን የሚገኙ የተለያዩ የግጭት ሁኔታዎች እጅግ ያዛዝኑኛል፣ ሆኖም በእነዚህ ቀናት በሲርያ በሚካሄደው ዕልቂትና በየዕለቱ እየባሰ የሚሄደው ድራማ ልቤን በከፋ ሁኔታ አቍስሎታል፣ የባሰውኑ በዚችው ሞት ያንዣብባት ባላት አገር የጦርነት መሳርያዎቹ ስንት ውድመት! ስንትስ ስቃይ! አስከተለላት ገናም እያስከተለ ነው፣
“ኬማካላዊ የጦር መሳርያዎች በልዩ ጽናት እኰንነዋልወሁ፣ እስቲ ስለሕጻናቱ እናስብ! ስንት ሕጻናት ናቸው ብርሃንን ለማየት ያልታደሉ፣
“አንድ ቀን የእግዚአብሔር ፍርድ አለ፤ እንዲሁም ልናመልጥባቸው የማንችልባቸው ተግባሮቻችን አንድ ቀን በታሪክ ይፈረዳሉ፣ በኃይል ወይንም በዓመጽ ሰላም ፈጽሞ ሊመጣ አይችልም፣
“ጦርነት ጦርነትን ይጠራል! ዓመጽ ዓመጽን ይጠራል፣ በዚሁ ግጭት ውስጥ ላሉ ሁሉ አንዴ ኅልናቸውን እንዲያዳምጡ ለገዛራሳቸው ጥቅም ሲሉ በገዛ ራሳቸው ውስጥ ከመዘጋት ይልቅ ሌሎችን እንደወንድማሞች በመመልከት ዓይነጭፍን ግጭትን በመተው በብርታትና በቈራጥ ውሳኔ የመገናኘትንና የድርድርን መንገድ እንዲመርጡ፣ በሙሉ ኃይልየ እጣራለሁ፤ ሲሉ አደራ ብለዋል፣
ቅዱስነታቸው አያይዘውም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ስለመላው የሲርያ ሕዝብ በጎ ነገር በተቻለው መጠን አለምንም ቅድመ ሁኔታ በውይይትና ድርድር የተመሠረተ ሰላም እንዲገኝ እንዲጥሩ ጥሪ አቅርበዋል፣
“በዚሁ አሰቃቂ ግጭት ለተጉዱ ወገኖች ለመርዳት በተለይ ደግሞ በአገር ውስጥና በጐረቤት አገሮች ተሰደው ላሉ ወገኖች ለመርዳት ምንም ነገር አይቀር፣ ሲሉ ሁሉ ነገር ለተቸገሩትና ለተጨነቁት ለመርዳት እንዲሆን ካሳሰቡ በኋላ በዓለም ውስጥ ሰላም እንዲገኝ ምን ማድረግ አለብን? ብለው ይጠይቃሉና ሰላም አለምንም ድንበር የመላው የሰው ልጅ ዘር በጎ ነገር መሆን ይገልጣሉ፣
“አሁንም በታላቅ ጩኸት እደግመዋለሁ! የጥላቻ ባህል ወይንም የግጭት ባህል አይደለም ሰዎች አብረውና ተቻችለው እንዲኖሩ የሚረዳ! ነገር ግን የመገናኘትና የመወያየት ባህል ብቻ ነው ለሰላም የሚሆን ጐዳና፣ ሁላቸው የጦር መሳርያዎችን ጥለው የሰላም ጐዳናን እንዲከተሉ ጩኸታችን ልባቸውን እንዲነካ የሰላም ጩኸቱ ከፍ ይበል፤ ካሉ በኋላ በመካከለኛው ምሥራቅ ለሲርያ እና ለመላው ዓለም ሰላም ካቶሊኮች የሌላ ኃይምኖች ተከታዮች የማያምኑም ሳይቀር የአንድ ቀን ጾምና እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፣
“መስከረም ሰባት ቀን እዚህ ጋ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከምሽቱ አንድ ሰዓት እስከ እኩለ ሌሊት በጸሎትና በንስሓ መንፈስ እንሰበሰባለን በዚህም እግዚአብሔር ለተወዳጅ ሲርያና ለሁሉም በግጭት እና በዓመጽ የሚገኙ የዓለም ክፍሎች ታላቁን ስጦታ ሰላምን እንዲሰጥ እንለምናለን፣ የሰው ልጅ ዘር ባጠቃላይ የሰላም ምልክቶች የተስፋና የሰላም ቃላት ሊሰማ ታላቅ ፍላጎት አለው፣ ሲሉ ከተማጠኑ በኋላ የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገዋል፣ ከጸሎቱ በኋላ ዛሬ ዕለት በቡካረስት ከተማ ሥርዓተ ብፅዕናው የሚፈጸም የእምነት ሰማዕት አባ ቭላድሚር ምሳሌ እንዲሆነን አሳስበዋል፣
ይህ በእንዲህ ሳለ ትዊተር በሚባለው የዘመናችን መገናኛ ብዙኃን “በመላው ዓለምና በየልቦቻችን ሰላም እንዲወርድ ስለሰላም እንጸልይ” ሲሉ አጭር መልእክት ጽፈዋል፣
All the contents on this site are copyrighted ©.