2013-08-16 19:03:19

እመቤታችን ድንግል ማርያም ዘወትር ከእኛ ጋር ናት! በሚያጋጥሙን ከባድ ፈተናዎች ከሰማይ ትደግፈናለች፣


ይህንን ያሉት ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍርናቸስኮስ ትናንትና በላቲኑ ሥርዓት ለተከበረው የእመቤታችን ድንግል ማርያም በሥጋዋና በነፍስዋ ወደ ሰማይ መፍለስዋን ለማክበር በካስተል ጋንደልፎ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባደረጉት ስብከት ነበር፣
እመቤታችን ድንግል ማርያም በክብር ወደ ልጅዋ ወደ ሰማያዊ ክብር በሥጋዋና በነፍስዋ ብትፈልስም ዘወትር በምናደርገው ትግል ከእኛ ጋር ናት፣ ሲሉ በካስተል ጋንደልፎ ሐዋርያዊ አደራሽ አከባቢ በሚገኘው አደባባይ በሜዳው ተሰብሰበው ላስቀደስ የአከባቢው ምእመናንና ከተለያዩ ክፍላተ ዓለማት ለመጡ ነጋድያን አስተምረዋል፣
እንደ ልማድ አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት አብዛኛውን ጊዜ በዚሁ ወቅት ለሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ የበጋ ወራት ዕረፍት በካስተንጋደልፎ ሐዋርያዊ አደራሽ ሲገኙ ቅዱስነታቸው ግን በሥራ ምክንያት በቫቲካን ስለሚገኙ ለቅዳሴው ትናንትና ጥዋት ነው ከመንበራቸው ወደዛ የሄዱት፣ ታንሹ የካስተልጋንደልፎ አደባባይ ልክ እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተለያዩ ባንዲራዎች በሚያውለበልቡ ም እመናንና ነጋድያን መልቶ ነበር፣ በዚሁ ወራት ቅዱስነታቸው በካስተልጋንደልፎ ሲገኙ የትናንትናው ለሁለተኛ ጊዜ ነበር፣ እ.አ.አ. ሓምሌ 14 ቀን የመል አከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ ለማድረግና ከም እመናኑና ከነጋድያኑ ጋር እንዲጸልዩ እዛ ተገኝተው ነበር፣ በትናንትናው ዕለት ሕዝባዊ በዓልም በመኖሩ ብዙ ቤተ ሰቦች ከልጆቻቸው ጋር በአደባባዩ ተገኝተው ነበር፣
ቅዱስነታቸው ስብከተቻውን ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ስለ ቤተ ክርስትያን ባቀረበው ሉመን ጀንስዩም ብርሃነ አሕዛብ በሚለው ሰንዱ ላይ ስለእመቤታችን ድንግል ማርያም በሥጋዋና በነፍስዋ ወደ ሰማይ መፍለስዋን የሚያስተምር አንቀጸ ሃይማኖት ጠቅሰው፣ ይህ የእመቤታችን ድንግል ማርያም ወደ ሰማይ መፍለስ የተፈራረቀ ስሜት ሊፈጥር እንደሚችል ለመግለጥም፣ በዕለቱ ቃለ እግዚአብሔር በዮሓንስ ራእይ ስለተጠቀሰችው ሴትና ዘንዶው ስላለው ትግል የሚገልጠው ማለት ጥቅሱ እንደሚሚለው “ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች። እርስዋም ፀንሳ ነበር፥ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጭንቃ ጮኸች። ሌላም ምልክት በሰማይ ታየ፤ እነሆም ታላቅ ቀይ ዘንዶ፤ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ነበሩት በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች ነበሩ፥ ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ።” (የዮሐ ራእ 12) ይህች ሴት ቤተ ክርስትያንን ስታመለክት ትግሉ ደግሞ ቤተ ክርስትያን ከጸላኤ ሠናያትና ጭፍሮቹ የምታደርገው ትግልን ያመለክታል፣ የፍልሰታ ሁኔታ ሁለት የቤተ ክርስትያን ገጽታዎች ያመልክታል፣ ባንዱ በኩል ሰማያዊትዋ ኢየሩሳሌም በመሆን በጌታ ትንሣኤ ድል የነሣች ሙሽራ ሆና ሰማያዊትና ድል የተጐናጸፈች በክብር ያሸብረቀች ስትሆን በሌላ በኩል ደግሞ በውግ ያና በትግል የምትኖር ማለትም በእግዚአብሔርና በጸላኤ ሰናያቱ ያለውን ትግል በፈተናና ተቋውሞ ስትጋፈጥ ያለች ቤተ ክርስትያንን እናያለን፣ ሆኖም ግን ይህንን ትግል ብቻችን እንደማንፈጸመውና ሰማያዊ ድጋፍ እንደለን እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣
“የክርስቶስ እናትና የቤተ ክርስትያን እናት የሆነቸው እመቤታችን ድንግል ማርያም ዘወትር ከእኛ ጋር ናት፣ ዘወትር ከእኛ ጋር ትጓዛለች፤ እመቤታችን ድንግል ማርያምም ይህንን የክብርና የትግል ሁኔታ ትሳተፈዋለች፣ እንደእውነቱ እርሷ ለአንዴና ለመጨረሻ በሰማያዊ ክብር ገብታለች፣ ሆኖም ግን ይህ ከእኛ እንደራቀች ወይንም እንደተለየች አያሰማም! ነገር ግን በምናደርገው ትግል ዘወትር ትሸኛናለች! ክርስትያኖች ከጠላት ኃይሎች ጋር በሚያደርጉት ውግያ ትደግፋቸዋለች፣ ስለዚህ ከእመቤታችን ጋር የምናደገው ጸሎት ማለትም ጸሎተ መቍጠርያ የዚሁ ውግያ ማለትም ከጸላኤ ሠናያት የሆነው የክፋት አባትና ጭፍሮቹ ጋር በምናደርገው ውግያ ይደግፈናል፣ ካሉ በኋላ በአደባባዩ ካሉ ም እመናን ጋር ለመወያየት እንዲህ ሲሉ ጠይቀዋል፣
“ለመሆኑ ትሰሙኛላችሁ ወይ! ጸሎተ መቍጠርያ ነው ያልኩት! እናንተ ጸሎተ መቍጠርያን በየዕለቱ ትደግሙታላችሁን? እኔ እንጃ.. በእርግጥ ትደግማላችሁ? ብለው ከጠየቁ በኋላ በሁለተኛው የዕለቱ ቃለ እግዚአብሔር መለስ በማለት ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች በጻፈው መል እክቱ ስለ ትንሣኤ ሌላ ን ኡስ አ ር እስት በመጀመር “ክርስትያን መሆን ማለት ክርስቶስ በእውነት ከሙታን ተለይቶ እንደተነሣ ማመን ነው፣ እምነታችን ሁሉ በዚሁ መሠረታው እውነት የሆነው ፍጻሜ ላይ ይመሠረታል፣ የእመቤታችን ወደ ሰማይ መፍለስም ከዚህ ጋር የተሳሰረ መሆኑንም እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣
“የእናት ሰብአዊ ባህርይ በሞት የሚሻገረው ልጅዋ ስበት ይሳባል፣ ኢየሱስ ለአንዴና ለመጨረሻ ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት የተሻገረው ያ ከእመቤታችን ድንግል ማርያም ከወሰደው ከሰብአዊ ባህርዩ ጋር ነው፣ በዚህም እናቱ የሆነችው እርሷም ልክ በሕይወቱ ሁሉ እንደተከተለችሁ በሙሉ ልብዋ ነው የተከተለችሁ! ከእርሱ ጋር ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት ገባች፣ ይህንን ሰማይ መንግሥተ ሰማይ ወይንም የአባት ቤት እንለዋልን፣ ይህ ሲሆን ግን በቀላሉ የተገኘ አይደለም፣ እመቤታችን ድንግል ማርያምም የመስቀሉ ሰማዕትነት የልብ ሰማዕትነት ታውቀዋለች፣ ከልጅዋ ጋር ቀመስችው፤ ልጅዋ ኢየሱስ በመስቀል ሲሰቃይ እርሷም በልቧ ከእርሱ ጋር ተሰቃየች፣
“ከርሱ ጋር በሞቱ በሙላት ተሳተፈች ስለዚህም የትንሣኤ ስጦታ ተቀበለች፣ ክርስቶስ የሙታን ሁሉ በኩር ነው! እመቤታችን ድንግል ማርያም ደግሞ የዳኑ አማኞች በኩር ናት! የክርስቶስ ከሆኑት አንደኛ ለማለት ነው፣ እናታችን ናት እንዲሁም ጠበቃችን ናት ለማለትም እንችላለን፣ እኅታችን ናት! በኵር እኅታችን አንደኛ እኅታችን! የዳኑ ሰዎች አንደኛ በመሆን ከሁሉ አስቀድማ ወደሰማይ ያረገችም ናት፣ በማለት ስለክብርዋ ካስተማሩ በኋላ ከእርስዋ የምንማረው ታላቅ ነገር ተስፋ መሆኑን ገልጠዋል፣ ተስፋ መልእልተ ባህርያዊ ጸጋ ሆነ! ይህንን ያገኘ ሰው በፈተናዎች ተከቦ በየዕለቱ በሞትና ሕይወት በመልካም ነገርና በክፋት እየተዋጋ በክርስቶስ ትንሣኤና በፍቅር ድል አድራጊነት የሚያሳምን ጸጋ ነው፣ ለዚህም እመቤታችን ድንግል ማርያም በደረሰችው ጸሎትዋ ተስፋ ታስተምራለች፤ ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር የሚለው ጸሎትዋ የተስፋ ማኅሌት ሆኖ ሕዝበ እግዚአብሔርም በጉዞው ዘወትር ይህንን ነው የሚዘምረው፣
“ይህ ማኅሌት የብዙ ቅዱሳንና ቅዱሳት ዜማ ነው፤ ከእነዚህ አንዳንዶቹን እናውቀዋቸዋለን አንዳንዶቹን እንዲያው አብዘኛዎቹን አናውቃቸውም ሆኖም ግን እግዚብሒር ጥሩ አድርጎ ያውቃቸዋል፣ እናቶች አባቶች የትምህርተ ክርስቶስ መምህራን ል ኡካነ ወንጌል ካህናት ደናግል ወጣቶች እንዲሁም ሕጻናት እና አያቶች ናቸው፣ እነኚህ የሕይወት ትግልን በመጋፈጥ በልቦቻቸው የትናንሽና የትሑታን ተስፋ ይዘው ተጉዘዋል፣
ይህ መዝሙር አሁንም ሳይቀር በተለይ ደግሞ በሥቃይ የምትገኘው የክርስቶስ አካል የሆነችው ቤተ ክርስትያን ገና ሕማማቱንና ሥቃዩን የምታጣጥም ትዘምረዋለች፣ እመቤታችን ድንግል ማርያምም በእነዚሁ ማኅበረ ክርስትያኖች ጐን በመቆም ከእነዚሁ ወንዶቻችን ጋር በመራመድ ከሳቸው ጋር ትሰቃያለች ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር የሚለው የተስፋ ማኅሌቱንም አብራዋቸው ትዘምራለች፣
“ለእኛ ክርስትያኖች መስቀል ባለበት ዘወትር ተስፋ አለ፣ ተስፋ ከሌለ ክርስትያኖች አይደለንም፣ ለዚህም ነው ዘወትር በንግግሬ ተስፋችሁን እንዳይሰቁባችሁ ተጠንቀቁ በማለት ደጋግሜ የምናገረው፣ የተስፋ ኃይል ጸጋ ስለሆነ የእግዚአብሔር ስጦታ ስለሆነ ሰማይን እየተመለክትን ወደፊት እንድንራመድ ስለሚረዳን እባካችሁ ተስፋችሁን እንዳይሰርቁዋችሁ፣
“ውድ ውንድሞችና እኅቶች! እኛ በሙሉ ልባችን በዚሁ ድል የተቀዳጀችውን ቤተ ክርስትያንና በዓለማችን እየታገለች ያለችውን ቤተ ክርስትያን እንዲሁም ምድርና ሰማይን ታሪካችንና ዘለዓለማዊነትን የሚያገናኝ የትዕግሥትና የድል የትግልና የደስታ የተስፋና የድል ማኅሌት ዜማ እንድንሳተፍ ይሁን፣








All the contents on this site are copyrighted ©.