2013-08-15 10:39:41

ር ሊ ጳ ፍራንሲስ የጣልያን እና አርጀንቲና የእግር ኳስ
ብሔራዊ ቡድኖች ተቀብለው አነጋግረዋል ፡



ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ትናትና ረፋድ ላይ የጣልያን እና የአርጀንቲና ብሔራውያን ቡድኖች ቫቲካን ውስጥ ተቀብለው አነጋገሩ ። የሁለቱ ሀገራት ብሔራውያን ቡድኖች ዛሬ ምሽት እዚህ ሮም ውስጥ በሚገኘው ኦሎምፒክ ስታድየም ርእሰ ሊቃነ ጵጵስና ፍራንሲስ በማሰብ የውድጅነት ግጥምያ እንደሚያደርጉ ታውቆዋል። ከቅድስት መንበር የተሰረጨ ዜና እንደሚያመለክተው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እግር ኳስ ይወዳሉ ። ይሁን እና የጣልያን እና የአርጀንቲና የእግር ኳስ ቡድኖች በአምበሎቻቸው እና አሰልጣኞቻቸው ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የተገናኙ ሲሆን ለተጨዋቾቹ ንግግር ሲደርጉ የተወደዳችሁ ስፕርት የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እና ሰብአውነት አዘውትሩ ብለዋል።በማያያዝ የወዳጅነት ግጥምያ በምታደርጉበ ግዜ ለጣልያን ወይስ ለአርጀንቲና ለማን እንደምደግፍ መወሰን ከባድ ነው ደግነቱ የወዳጅነት ግጥምያ ነው ብለዋል ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ። ቅድስነታቸው የአርጀንቲና ዜጋ መሆናቸው አይዘነጋም ። ቅድስነታቸው በአረጀንቲና ሳን ሎረንጾ የተባለ ቡድን ደጋፊ መሆናቸውጠቁመው ይህ ሆኖ ግን የእግር ኳስ ተጫዋቾች መሕበራዊ ሐላፊነት እንዲሰማቸው እንደሚያስፈልግ እና እግር ኳስ ስፖርት ከመሆን ሌላ ትርጉም እንዲሰጠው እንደማይስፈልግ አመልክተዋል።ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በማያያዝ የእግር ኳስ ፕሮፈሽናል ተጨዋቾች ብትሆንም በስፓርት እና ሕይወት ሰብአዊ መሆን እና ሰብአውነት የተላበሳችሁ ሁኑ ካሉ በኃላ ለስፓርት አስተዳደሮች ኳስ ጨዋታ ስፖርት መሆኑ ቀርቶ ንግድ እየሆነ መምጣቱ ጠቁመው የስፖርት ፀባዩ እንዳይጠፋ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ ተማጽነዋል።
የእግር ኳስ ውድድር ከዘር አድልዎ እና በደጋፊዎች መካከል ጠብ ጫሪ መሆን እንደማይገባ ፓፓ ፍራንቸኮ አሳስበዋል። በየእስፓኛ ቋንቃ ለአርጀንቲና ተጨዋቾች እዚህ መገናኘታችን በጣም ደስ ይለኛል ሆኖም ስፖርት የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑ መዘንጋት የለባችሁም
ሰብአዊ ማሕበራዊ እና ሞራላዊ ሐላፊነት እንዳላችሁ አትዘንጉ መልካም አርአያ መሆንም ይጠበቅባችሃል ብለዋቸዋል። የተሸከምኩት ሐላፊነት በሚገባ እና በመልካም አኳኅን እንድዋጣ ጸልዩልኝ ያሉት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን እንደሚያደንቁ ገልጠዋል። ቅድስነታቸው እና የጣልያን እና የአርጀንቲና ቡድኖች ስጦታ ተለዋውጠዋል ። በእስፓኛ የባርቸሎና ቡድን አባል እና የአለም ኮከብ ተጫዋጭ የአርጀንቲና ዜጋ መሲ ቅድስነታቸውን ማመስገኑ ተመልክተዋል።ከግንኝነቱ በኃላ የጣልያን ብሔራዊ ቡድብ አሰልጣኝ ቸሳረ ፕራንደሊ እንደገለጡት የፓፓ ፍርንሲስ ዓቢይ ሰብአውነት ለስፖርት እጂግ መልካም ነው ሲሉ ገልጠዋል።
አሁን ዝግጅታችን በሚሰራጭበት ግዜ የጣልያን እና አርጀንቲና ቡድኖች ግጥምያ ተጀምረዋል ግጥምያው ከተጀመረ 10 ደቂቃ ቢያልፍም ግብ ያስቆጠረ ቡድን እንደሌለ ተመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.