2013-08-13 19:21:52

ጸሎት ስለ መካከለኛው አፍሪቃ ሰላም:


ሰኞ ዕለት ስለ መካከለኛው አፍሪቃ ሰላም እንዲጸለይ የባንጉይ ሊቀ ጳጳሳት እና የሃገሩ የሃይማኖት መሪዎች አሳስበዋል፣ ይህ ሃገራዊ የጸሎት ቀን ስለ ሰላም ሲሆን የአገሪቱ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ መሆኑ ሊቀ ጳጳሱ ሲገልጡ በመውደም ላይ ያለች አገር ብለዋታል፣ ይህ የሆነው የአገሪቱ ፕረሲደንት የነበሩ ቦዚዘ በሰለካ ጥምረት ተገፍተው ከአገሩ ከወጡ በኋላ ነው፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደዘገበው ከሆኑ በሃገሪቱ ምንም ዓይነት ሕጋዊ አካል ይሁን የፖሊስ ሃይል እንዲሁም ምንም ዓይነት ማኅበራዊ አገልግሎት እንደሌለ ነው የሚገለጠው፣ ባለፉት ቀናት የድርጅቱ ዋና ጸሓፊ ባን ኪሙን ለጸጥታው ምክር ቤት በገንጣዮቹ ላይ ያቶከረ እገዳ እንዲደረግ ጠይቀው ነበር፣ የባንጉይ ሊቀ ጳጳስ ድየዶነ ንዛፓላዪንጋ ለቫቲካን ረድዮ በሰጡት መግለጫ ዋናው አሳሲቢው ጉዳይ ሰብአዊ ቀውስ መሆኑና ብዙ ሰዎች በደኖች ተደብቀው እንደሚገኙ የባሰው ደግሞ ብዙ በኤች አይ ቪ አይድስ የተጠቁ አለምንም መድኃኒት በበረሃው ስለሚገኙ ሕይወታቸው በአስጊ ሁኔታ ይገኛል፤ ምንም ምግብ ስለሌላቸውም ቅጠላቅጠልና ስራስር እየተመገቡ ናቸው፣ ብዙ ሰዎች እየሞቱ ነው፣ በመርዘኛ እባቦች ተነድፈው የሚሞቱም ጥቂት አይደሉም፣ በከተማውና በሆስፒታሎቹ ዋስትና ስለሌለ እስከዛ መሄድ አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ የመድኃኒት ዕጥረትም እንዳለ ገልጠዋል፣ ሌላው አሳሳቢ ነገር ደግሞ የትምህርት ጉዳይ ሲሆን ብዙ ወጣቶች ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ አይችሉም፣ ይህ በእንዲህ ሳለ ሌላው በዕንቅርት ላይ ጆሮደግፍ እንደሚሉ ባለፉት የኮንጎ ግጭት ብዙ ከደሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ ኮንጎ እንዲሁም ከሱዳን ተሰደው በቦታው ብዙ ጊዜ የተቀመጡ ስደተኞችም የባሰ ችግር ላይ ይገኛሉ፤ ሁሉም ትቶዋቸው ስለሸሹ በታላቅ ችግር ይገኛሉ፤ አንዳንዶቹ ያላቸውን ልብስና ቍሳቍስ እየሸጡ ዕለታዊ ምግብ በመግዛት እየታገሉ ናቸው፣ እነኚህ ስደተኞች መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች እየተረዱ ነው የቆዩት አሁን ግን ሁሉም ስለሸሹ ብቻቸው ተጥለው ቀርተዋል፣ ሲሉ ጸሎቱ እጅግ አስፈላጊ መሆኑና ይህንን የሚሰማ ሁሉ በጸሎት እንዲረዳቸው አሳስበዋል፣







All the contents on this site are copyrighted ©.