2013-08-13 19:23:57

የቅድስት ክያራ ዘአሲዚ ዝክረ በዓል


የቅድስት ክያራ ዘአሲዚ ዝክረ በዓል ባለፈው እሁድ በመላው የጣልያን ቍምስናዎች በታላቅ መንፈሳውነት እንደተዘከረ ተመልክተዋል፣ ከሁሉ በላይ ደግሞ ቅድስትዋ በ1194ዓም የተወለደችበት የኡምብርያ ከተማ አሲዚ ውስጥ ደማቅ ጸሎት አርገዋል፣ በአሲዚ ባዚሊካ ከሥርዓተ ዋዜማና ማኅሌት እስከ ቅዳሴ በታላቅ መንፈሳውነት ተደርገዋል፣ የአሲዚ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዶመኒኮ ሶረንቲኖ የማታውን ቅዳሴ ሲያሳርጉ የትናንትና እሁድ የጥዋት ቅዳሴ ግን በብፁዕ ካርዲናል ፓውሎ ሳንድሪ ነው ያረገው፣ ትናንትና ማምሻውን ያረገው ሌላ ቅዳሴ ደግሞ በን ኡሳን አኃው ካፑቺኒ ዋና ኃላፊ ጥቀ ክቡር አባ ብሩኖ ኦታቪ አርገዋል፣ በሁሉም ቅዳሴዎችና ጸሎትች በቅድስትዋ የተቋቋሙ የክላሪሰ ደናግል በመዝሙሮች በጸሎት በመሳተፍ ድምቀት ሰጥተውታል፣ ለሁሉም በዚሁ ታላቅ ብዓል እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፣ በተለይ ደግሞ በዚሁ የእምነት ዓመት ቅድስት ክያራ ወደ መሠረታውያን ዕሴቶች እንድንመለስ በሕይወትዋና በታማኝነትዋ ስለ እግዚአብሔር ዛሬም ትናገናራለች፣
ቅድስት ክያራ በ1253 ዓም ከዚህ ዓለም በሞት ከመለየትዋ በፊት የቅዱስ ቍርባን ስግደትና መለኮታዊ ምሕረት መንፈስ በሕይወትዋና በቃልዋ አስተምራለች፣








All the contents on this site are copyrighted ©.