2013-08-13 19:27:07

መዓርገ ጵጵስና :


ባለፈው ወርሀ ሰነ 28 ቀን ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ አባ የማሕበረ ልዑካን ማህበር አባል አባ ቫርገስ ቶታምካራ በደቡባዊ ምዕራምብ ኢትዮጵያ የነቀምቴ ረዳት ጳጳስ መሰየማቸው የሚታወስ ነው ።
አባ ቫርገስ ቶታምካራ እኤአ በ1959 በህንድ ቶትቫ በተባለ ቦታ መወለዳቸው እና በማሕበረ ልዕካን ጥምህርታቸው ካጠናቀቁ በኃላ በ1987 መዓርገ ክህነት መቀበላቸው ይታወቃል።
አባ ቫርገሰ ቶታምካራ ዛሬ ነሐሰ 13 ቀን እዚህ ሮም ውስጥ የማሕበረ ልዑካን በርካታ ካህናት እና ጥሪ የተደረገላቸው መንፈሳውያን ማሕበራት እና ምእመናን በተገኙበት በለኦንያኑም ቤተ ክርስትያን ከብጹዕ አቡነ ሉካ ብራንዶሊኒ እጅ ቅብአተ ጵጵስና ተቀብለዋል ።
በወቅቱ ብፁዕ አቡነ ተኦዶሩስ ቫን ሩይቨን የነቀምቴ ክልል ሐዋርያዊ መስተናብር መሆናቸው ይታወቃል። በነቀምቴ ዞን ሰባት ሚልዮን 241 ሺ ህዝብ እንደሚኖር እና ከዚህ 55 ሺ 453 ካቶሊካውያን እንደሆኑ በ28 ካህናት የሚገለገሉ 91 ቆምስናዎች 85 ደናግሎች 21 የዘርአ ክህነት ተማሪዎች እንደሚገኙበትም ተገልጸዋል።ዛሬ ጵጵስና መዓርግ የተቀበሉ አባ ቫርገስ ቶታምካራ በኢትዮጵያ ከአስር ዓመታት በላይ ሐዋርያዊ አገልግሎት መስጠታቸው ይታወቃል።









All the contents on this site are copyrighted ©.