2013-08-12 19:35:28

እውነተኛው መዝገባችን የእግዚአብሔር ፍቅር ነው! ክርስትያኖችና ሙስሊሞች አንዱ ሌላውን በማክበር ይኑሩ፣


RealAudioMP3
ይህንን ያሉት ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት የዕለቱ ቃለ ወንጌልን በመጥቀስና በቅርቡ ለተፈጸመው ጾመ ረሞዳንና ለተከበረው የሙስሊሞች ዒድ አልፈጥር በማስታወስ ነው፣ ቅዱስነታቸው የሰው ልጅ ሁሉ አንድያና እውነተኛ መዝገብ የእግዚአብሔር ፍቅር ሆኖ ይህም ቤተ ሰብን ጠምዶ በመያዝ ለኑሮ ትርጉም በመስጠትና የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች ለመጋፈጥ በመርዳት ነው፣ ለዚህም ምሳሌ የምትሆነን ቅድስት ክያራ ዘአሲዚ ስትሆን ቅድስትዋ ለክርስቶስ በድህነት ሙሉ ለሙሉ ለመቀደስ ሁሉን የመነነች ናት፣ ሲሉ አሳስበዋል፣
ቅዱስነታቸው የወንድማሞቻችን ሙስሊሞች ጾመ ረመዳን ማለት በጾም በጾሎትና በምግባረ ሠናይ ያሳለፉትን አንድ ወር እንደገና በማስታወስም ለመላው የዓለም ሙስሊሞች እንደገና ይህንን ብለዋል፣
“ለዚሁ አጋጣሚ በጻፍኩት መል እክቴ እንደገለጥሁት፤ ሁላቸው ክርስትያኖችና ሙስሊሞች አንዱ ሌልዋን የማክበር ኃላፊነት እንዲያዳብሩ በተለይ ደግሞ ለአዲሱ ትውልድ በሚደረገው የትምህርት ዕድገት እንዲተባበሩ አደራ፣ ብለዋል፣
ለመላው ዓለም ሙስሊሞች ሰላምታ ከማቅረባቸው በፊት ግን የዕለቱን ቃለ ወንጌል በመጥቀስ ኢየሱስ ከሐዋርያት ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ማለትም ወደ ሕማማቱ ሞቱና ትንሣኤው ሲገሰግስ ያመለክታል፣ በዚሁ ጉዞ ኢየሱስ ሐዋርያቱን ቀስ በቀስ በልቡ ያለውን ነገር ሲያካፍላቸው ማለት ስለ ሞቱና ሕማማቱ እንዲሁም በልቡ የሚሰማውን ነገር ይገልጥላቸዋል፣ ይህ የወንጌል ቃል ዛሬ እኛንም የሚለን መል እክት እንዳለውና “እያንዳንዱ ክርስትያን በልቡ ውስጥ ታላቅ ፍላንጎት እንዲያው ጥልቅ ጌታን የማግኘት ፍላጎት እንዳለው ይግለጥልናል ብለዋል፣
“ልብ ዘወትር በአንድ ነገር በማትኮር ልዩ ፍላጎት ያዳብራል ነገር እኛ ሁላችን አንድ ፍላጎት አለን! ፍላጎት የሌለው ሕዝብ እጅግ የሚያሳዝን ድኃ ነውና! እኛ ሁላችን ወደ አንድ ዓላማ ለመድረስ ወደ ፊት የመገስገስና የመራመድ ፍላጎት አለን፤ ለክትስትያኖች ይህ ዓላማ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር መገናኘት ነው! ምክንያቱም እርሱ ሕይወታችንና ደስታችን ስለሆነ ደስ ያሰኘናል፣
ቅዱስነታቸው በቅዱስ ጴጥሮስ ወደ ተሰበሰቡት መለስ በማለት በፍላጎት የሞላ ልብ ያላቸው መሆኑን ለማወቅ ሁለት ጥያቄዎች አቅርበዋል፣
“በፍላጎት የሚቃጠል ልብ ነው ያለህ ወይስ የተዘጋ ልብ! የሚያንቀላፋ ልብ! በግዝያዊ የኑሮ ሁኔታዎች የደነዘዘ ልብ ነው ያለህ! ይህ ፍላጎት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለማግኘት ወደ ፊት መገስገስ ነው፣ ሁለተኛው ጥያቄ ደግሞ አንተ የምትፈልገው መዝገብ የት አለ? የሚል ነው ምክንያቱም ኢየሱስ መዝገብህ ባለበት ቦታ ልብህ እዛ ይገኛል ብለዋልና! አሁን እኔ የምጠይቃችሁ ደግሞ መዝገብህ የት አለ? በማለት እያንዳንዳችሁን እጠይቃለሁ፣ በሕይወትህ ውስጥ እጅግ አስፈላጊ የሆነው ነገር! እጅግ የከበረውና ልብህን እንደ ማግኔት የሚስበው ነገር የትኛው ነው?
ብለው ለጥቂት አረፍ አሉና እንደገና ደግመው ልባችንን የሚስበው ነገር ምንድር ነው? ብለን የጠየቅን እንደሆነ የእግዚአብሔር ፍቅር ነው ለማለት እንችላለንን? ወይንም ለሌሎች መልካም ነገር የማድረግ ፍላጎት፧ ወይንም ለጌታ ኢየሱስና ለወንድሞቻችን ለመኖር እንፈልጋለን?
“ነገር ግን አንድ ሰው! አባ እኔ ሠራተኛ ነኝ! ቤተ ሰብ አለኝ! ለኔ እጅግ አስፈላጊ የሆነው ነገር ቤተ ሰብን መንከባከብ ነው፣ አዎ እውነት ነው ሥራ አስፈላጊ ነው! ሆኖም ግን ቤተሰብን አንድ አድርጎ የሚይዘው የትኛው ኃይል ነው? ፍቅር ነው! ይህንን ፍቅር በልባችን የሚዘራው ደግሞ እግዚአብሔር ነው! የእግዚአብሔር ፍቅር! ይህ የእግዚአብሔር ፍቅር ነው ለትናንሽ ዕለታዊ ተግባሮቻችን ትርጉም የሚሰጣቸውና የሚያጋጥሙንን ታላላቅ ፈተናዎች ለመጋፈጥም ይረዳናል፣ የሰው ልጅ እውነተኛ መዝገብ ይህ ነው! የእግዚአብሔር ፍቅር! በሕይወት ጉዞ ውስጥ በፍቅር ወደፊት መራመድ! ከእግዚአብሔር ፍቅር ማለትም ያ እግዚአብሔር በልባችን በዘራው ፍቅር መራመድ! ይህ ነው እውነተኛ መዝገብ፣ ይህ ነገር ይዘት የሌለው ማንኛ ሐሳብ ሳይሆን ስምና ገጽታ አለው! በሌላ አነጋገር የእግዚአብሔር ፍቅር የምንለው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፣ ስለዚህ እርሱን ማግኘት ለእርሱ ቅድምያ መስጠት ያስፈልጋል፣
“የእግዚአብሔር ፍቅር በኢየሱስ ክርስቶስ ይገልጣል፣ ምክንያቱም እኛ ዝም ብለን ንፋስን መውደድ አንችልምና! ንፋስን እንወዳለን እንዴ! የሆነውን ነገር እንፋቅራለን ወይ! አይደለም! እንዲህ ሊሆን አይችልም፣ እኛ የምናፈቅራቸው አካል ያላቸው ሰዎች ናቸው! የምናፈቅረው አካልም እግዚአብሔር አብ የሰጠን ኢየሱስ ክርስቶስን ነው፣ ይህ ፍቅር ለቀሪው ሁሉ ነገር ትርጉምና ጣዕብ የሚሰጥ! ለቤተሰብ ለሥራ ለጥናት ለጓደኝነት ለኪነ ጥበብና ለሁሉም የሰው ልጅ ተግባሮች ኃይል የሚሰጥ ፍቅር ነው፣
ይህንን ፍቅር ለመልካም ተመኵሮ ብቻ እንዳንወስነውም ከውድቀትም ትርጉም ሊያመጣ ይችላል ምክንያቱም ይህ ፍቅር ከዛ ባሻገር ስለሚጓዝ በመጥፎ ነገር ተጋርደን የውድቀት ተገዢዎች ሆነን እንዳንቀር ውድቀቱን እንድንሻገር ወደ ተሻለ እንድንሸጋገር ለተስፋ ክፍት ያደርገናል፣
“እየውላችሁ! ለተስፋ ክፍት የሚያደርገር የእግዚአብሔር ፍቅር በኢየሱስ ሲገለጥ ይህ ተስፋ ደግሞ ወደ የሕይወታችን ዓላማ የሆነው የጉዞ አችን ፍጻሜ ወደ ሆነው ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት ይመራናል፣ በዚህም በየዕለቱ የሚያጋጥሙን ድካምና ውድቀት ትርጉም ያገኛሉ፣ ኃጢአቶቻችንም ሳይቀሩ በእግዚአብሔር ፍቅር ፊት ትርጉም ያገኛሉ ምክንያቱም በኢየሱስ የተሰጠን የእግዚአብሔር ፍቅር ሁል ጊዜ ይምረናልና፣ በማለት የእግዚአብሔር ፍቅር ጥልቀትና ትርጉም ከገለጡ በኋላ፣ በዚሁ ዕለታት ክብረ በዓልዋ ለተስታወሰው ቅድስት ክ ያራ ዘአሲዚን በማስታወስ ደሞ ሁሉን በክርስቶስ ለመቀደስ በድህነት ለእግዚአብሔር የቀረበው ቅዱስ ፍራንቸስኮስን በመከተል ወደ ቅድስና መድረስዋን ገልጠዋል፣
“ቅድስት ክያራ የዛሬው ወንጌል ትርጓሜ ታስተምረናለች፤ ከእመቤታችን ድንግል ማርያም ጋር ሆና ይህንን ቃለ ወንጌል እያንዳንዳችን እንደ ጥርያችን መሠረት እተግባር ላይ እንድናውለው ትርዳን፣ ካሉ በኋላ የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳረገው እንደ ላቲኑ ሥር ዓተ አምልኮ እፊታችን የሚከበረውን በዓለ ፍልሠታ ለማርያም በማስታወስ “ወደ ኢየሱስ ልጅዋ ወደ ሰማይ ያረገችውን እናታችን ድንግል ማርያም በማሰብ በዓሉን እርስዋን ለማክበር እንድናደርገው ይሁን” በማለት ትምህርታቸውን ደምድመዋል፣
ይህ በእንዲህ ሳለ ዘወትር እንደሚያደርጉት የዘመናችን የአጫጭር መል እክቶች መገናኛ ትዊተር በመጠቀመም ክርስቶስን ከቤተ ክርስትያን መለየት እንደማይቻል እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፣ “ኢየሱስ ክርስቶስን ከቤተ ክርስትያን መለየት አይቻልም፣ በጥምቀት የተቀበልነው ጸጋ ክርስቶስን በቤተ ክርስትያን ውስጥና ከእርሷ ጋር ልንከተለው ደስታ ይሰጠናል” ሲሉ ከመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በኋላ ከ8 ሚልዮን በላይ ለሚሆኑ ደንበኞቻቸው እንደጻፉ ከቅድስት መንበር የወጣ ዜና አመልክተዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.