2013-08-08 12:10:47

የር.ሊ.ጳ የቪድዮ መል እክት ለቦነስ አየርስ ቅ.ጋይታኖ አክባሪዎች::


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በዛሬው ዕለት በቦነስ አየረስ ለሚከበረው የቅዱስ ጋይታኖ በአል አክባሪዎች በቅዱሱ መካነ ንግደት ለሚገኙና ለመላው የአርጀንቲና ሕዝብ የቪድዮ መል እክት አስተላልፈዋል፣
የቅዱስ ጋይታኖ መካነ ንግደት ከቦነስ አየረስ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው የሊንየርስ አከባቢ ይገኛል፣ የዛሬው ዕለት ቅዱሱ ከዚህ ዓለም ወደ ሰማያዊ ዓለም የተሸጋገሩበት ዕለት በመሆኑ ከመላው አርጀንቲና የተሰባሰቡ ምእመናን በየዓመቱ በዚሁ ዕለት በቦታው በመገኘት የቅዱሱ ዝክር ያደርጋሉ፣ በቦታው ለሚገኘው የቅዱሱ ሓውልት ለመሳለምም እጅግ ረዥም ሰልፍ ስለሚደረግ ም እመናኑ በማለዳው ተነስተው ወረፋ ስለሚይዙ ወረፋው እጅግ ረዥም ነው፣ ወደ ቦታው የሚያደርሱ አሥር የተለያዩ ጎዳናዎች ስላሉም እቦታው ደርሶ የቅዱሱን ሓውልት ለመሳለም እስከ አስር ሰዓት እንደሚፈጅ ከቦታው የሚደርሱ ዜናዎች ያመልክታሉ፣ ይህንን ለማቃለልና የሕዝቡ መፈሳዊነትም ለመመገብ በዓሉን ለማክበር ከሚያመለክተው ዋዜማ ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ በየሰዓቱ መስዋዕተ ቅዳሴ እንደሚያርግና ሕዝቡም በላቀ መንፈስ እንደሚሳተፈውም ተመልክተዋል፣ በዚሁ ዓመት ከቅዳሴዎቹ መካከላኛ ተብሎ የተገመተው በአገሩ ሰዓት አቆጣጠር አሥራ አንድ ሰዓት ላይ የሚያርገው መሥዋዕተ ቅዳሴ የሚመሩት የቦነስ አየርስ ሊቀ ጳጳስና የአርጀንትና ቀዳሜ የሆኑ ብፁዕ አቡነ ማርዮ አውረልዮ ፖሊ እንደሚያሳርጉትና በቅዳሴው ፍጻሜም ሊቀ ጳጳሳቱ ለነጋድያን ሰላምታ እንደሚያቀርቡም ተመልክተዋል፣ የዚሁ ዓመት የቅዱስ ጋይታኖ መካነ ንግደት መሪ ሓሳብ “ከኢየሱስና ከቅዱስ ጋይታኖ ጋር ብዙ አስፈላጊነት ላላቸው ድሆችን ለማግኘት እንሂድ” የሚል ነው፣ የዛሬው ዕለት ጸሎትና መሥዋዕተ ቅዳሴ ነገ ለሚከበረው የቅዱሱ ዋና ዕለት እንደ ዋዜማ የሚያገለግል ሆኖ በየዕለቱ ስለ ቤተሰብ ስለአስተዳዳሪዎች በስቃይ ስለሚገኙ ሕመምተኞች ስለሞቱት ሥራ ስላጡትና ለአጋርነት የተለያዩ ጸሎትች እንደሚቀርቡም ተገልጠዋል፣
ቅዱስ ጋይታኖ ዘትየን በ1480 በቪቸንሳ የተወለዱና የፍልስፍናና የተለግ ያ ጥናት ካጠናቀቁ በኋላ በሲቪላዊና የቤተ ክርስትያን ሕጎች ዶክተር ያሰኙ በመጨረሻም የጌታን ጥሪ በመቀበል ካህን የሆኑና በአርጀንቲና ድሆችን ለመርዳት ሁሉን መስ ዋዕት ያድረጉ የአርጀንቲና ሕዝባዊ ቅዱስ ናቸው፣ ብዙ ካገልገሉና ከደከሙ በኋላ በነሓሴ ወር 1547 ዓም ከዚህ ዓለም በሞት የተልዩና በ1671 ቅድስናቸው ታወጀ፣ በ1929 ዓም የምጣኔ ሃብት ቀውስ ካጋጠመ በኋላ የዳቦና የሥራ ቅዱስ ጠበቃ በመሆን ስለታወቁ እስከ ዛሬ ዕለት በዚሁ ቅድስና የሚያገልግሉ በተለይም በአርጀንቲና ሰራተኞች በጣም የተከበሩ ቅዱስ ናቸው፣
ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ይህንን ዕለት ምክንያት በማድረግ ለሚወድዋቸው የቦነስ አየርስ ሕዝብ የሚከትለውን የቪድዮ መል እክት አስተላልፈዋል፣
መላካም ምሽት ይሁላችሁ! ሁሌ እንደምናደርገው ወረፋውን ከጨረስኩ በኋላ ከእናንተ ጋር እናገራለሁኝ! በዛሬው ዕለት ወረፋውን በልቤ ነው ያደረግሁት! ጥቂት ከእናንተ ራቅ ብየ ስላለሁኝ ይህንን አስደናቂ ጊዜ ከእናንተ ጋር ልጋራው አልችልም፣ በዚሁ ሰዓት ወደ ቅዱስ ጋይታኖ ምስል ትጓዛላቸውሁ! ለምን ይሆን ብለን የጠየቅን እንደሆነ ከእርሱ ጋር እንትገናኙ ከጌታ ኢየሱስ ጋር እንድትገናኙ ነው! ሆኖም ግን በዘንድሮው መንፈሳዊ ንግደት በእናንተ የተመረጠው መሪ ቃል “ከኢየሱስና ከቅዱስ ጋይታኖ ጋር ችግረኞችን ለማግኘት እንሂድ” የሚል ነው፣ ይህ ማለትም ችግረኞችን ከሩቅ መመልከትና ከሩቅ መርዳት ተገቢ እንዳልሆነ ያስረዳናል፣ ይህ የሚያደርግ ክርስትያን ነው፣ ኢየሱስ የሚያስተምረንም ይህንን ነው፣
አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ለድኃ የሚረዱ መሆናቸውን እጠያቃለሁ፣ አዎ አባ ይሉኛል! ደግሜ እንዲህ ሲል እጠይቃለሁ! ለመሆኑ ለለማኙ ገንዘብ ስጥሰጠው ዓይን ዓይኑን ትመለከታለህ ወይ? ስላቸው! እኔ እንጃ አባ! እምብዛም አላስታውሰውም! ይሉኛል! አሃ! ስለዚህ አንተ ድኆችን አይደለም የረዳሀው! ገንዘቡን ጥለህ ነው የሄድከው! ስለዚህ ምፅዋት ስታበረክት ለምታበረክትለት ሰው እጁን መንካት አለብህ! አለበለዚያ አልነካሀውም ማለት ነው! እላቸዋለሁ፣
በሌላ አነጋገር ኢየሱስ የሚያስተምረን ነገር ድኆችን ማግኘት ከዛም በኋላ መርዳታቸውን ነው፣ ድኆች በሁሉም ቦታ ይገኛሉ! በቤተ ሰቦች! በሥራ ቦታዎች! እንዲሁም በተልያዩ ሁኔታዎች ይገኛሉ! በኣካል ሄዶ ድኆችን ማግኘትና መርዳት ያስፈላጋል፣ ስለዚህ በዛሬው ዕለት ጌታ ኢየሱስንና ቅዱስ ጋይታኖን ለማግኘት ወረፋ ይዘንበት በምንገኝበት ሰዓት ችግረኞች ወንድሞቻችንና እኅቶቻችንን ለማግኘትና ለመርዳት እንደዛው ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል፣
ስለምትሰሙኝ አመሰግናችኋለሁን! እስከዚህ በመምጣታችሁም አመስግናችኋለሁኝ! በልባችሁ ይዛችሁ በምትጓዙት ሁሉም አመሰግናችኋለሁኝ! ኢየሱስ እጅግ ያፈቅራችኋል! ቅዱስ ጋይታኖም ያፈቅራችኋል! አንድ ነገር ብቻ ልጠይቃችሁ እወዳለሁኝ! ችግረኞችን በያለበት ቦታ ሂዳችሁ እንድታገኝዋቸው! ሆኖም ግን እናንተ ብቻችሁ ሳይሆን ከኢየሱስ ክርስቶስና ከቅዱስ ጋይታኖ ጋር ሆናችሁ እንድትጎበኝዋቸው አደራ እላለሁ፣ ሲሉ መልእክታቸውን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.