2013-08-07 15:40:26

ኮሎምቢያ፦ ዓለም ዓቀፍ የመለኮታዊ ምኅረት ጉባኤ


RealAudioMP3 የቪየና ሊቀ ጳጳሳት የዓለም አቀፍ የመለኮታዊ ምኅረት ጉባኤ ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ክሮስቶፍ ሾንበርን እ.ኤ.አ. በ 2014 ዓ.ም. በኮሎምቢያ ቦጎታ የሚካሄደው ሦስተኛው ዓለም አቀፍ የመለኮታዊ ምኅረት ጉባኤ በላቲን አመሪካ ሲካሄድ ለምጀመሪያ ጊዜ እንደሚሆን የሚነገርለት ዓለም አቀፍ የመለኮታዊ ምህረት ጉባኤ ቅድመ ዝግጅት ታልሞ የሚካሄደው ስብሰባ ማስጀመራቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት ሲገለጥ፣ በኮሎምቢያ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ቅድመ ዝግጅቱ እያፋጠነች መሆንዋ የዜናው አገልግሎት አክሎ እየተካሄደ ያለው የጉባኤው ቅድመ ማዘጋጃ ስብሰባ ሥነ መለኮታዊ ምኅረትና የመለኮታዊ ምሥረት ቲዮሎጊያ ርእሰ ዙርያ ሰፊ ትምህርትና ውይይት በማካተት የመለኮታዊ ምኅረት ስነ መንፈሳዊነት ቲዮሎጊያዊ ትንተና መሠረት የሚጠናቀቅ መሆኑ ያመለክታል ይህ በእንዲህ እንዳለም የቅድስት ፋውስቲናና የር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የመለኮታዊ ምኅረት ሰቂለ ኅሊናና የመለኮታዊ ምኅረት ር.ሊ.ጳ. ተብለው የሚገለጡት የሁለቱ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ቅዱሳት ትሩፋት ለ 2014 ሦስተኛው ዓለም አቀፍ የመለኮታዊ ምኅረት ጉባኤ ምክንያት ለጸሎት እና ለስተንትኖ ወደ ቦጎታ እንደሚዛወር ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.